ከሰሎሞን ተሰማ ጂ.
(semnaworeq.blogspot.com)
(semnaworeq.blogspot.com)
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊውን የፍትሕ ጋዜጣ እንዳይሰራጭ አገደ፤” (www.fetehe.com እና በአዲስጉዳይ መጽሔት፣ ሐምሌ 2004 ዓ.ም)
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንዳይታተም ከለከለ፡፡” (www.fnotenetsanet.com እና amharic.voanews.com October 02, 2012/ መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም)
“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሪፖርተር ጋዜጣን ገጽ ቁጥር ገደበ፡፡” (ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም)
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በሁሉም ዜናዎች በበጎ ጎኑ አልተነሳም፡፡ “እንዳይሰራጭ አገደ!” “እንዳይታተም ከለከለ!” እና “ቁጥር ገደበ!” የሚሉት ሃረጎች የማተሚያ ቤቱን
ስምና ክብር የሚያጎድፉ ናቸው፡፡ ይህ ማተሚያ ተቋም፣ የዛሬዎቹ ሹመኞችና ባለሥላጣናቱ አወቁትም – አላወቁትም
ትልቅ ራዕይና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ነበር፡፡ እነዚህን ተልዕኮዎቹን ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል መስዋዕት
ማድረግ ግን ከተጠያቂነትና ከታሪክ-ሕሊና ተወቃሽነት አያድንም፡፡
“ብርሃንና ሰላም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ማተሚያ ቤት” በመስከረም 3 ቀን 1914 ዓ.ም በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ተቋቋመ፡፡ ይህ ማተሚያ ቤት በጥቃቅን
ፔዳሎች ማለትም በእግር በመርገጥ በሚንቀሳቀሱ የማተሚያ መኪናዎች ሥራውን የጀመረው ስድስት ኪሎ በሚገኘው የዛሬው
የቋንቋዎች አካዳሚ ሕንፃ ውስጥ ነበር፡፡