August 3, 2015
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለመሪዎቻቸው ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በብዛት በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ህወሀት/ወያኔ ዛሬ እንደፈረደባቸው ታውቋል፣ ከወደ አዲስ አበባ እንደተሰማው በአስራ ስምንቱ የሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ከሰባት ዓመት እስከ 22 ዓመት የሚደርስ ብይን ተወስኖባቸዋል።
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “ከወያኔ የካንጋሮ ፍርድ ቤት ከዚህ የተለየ ነገር አልጠበቅንም ነበር” ብለዋል።
የፍርዱን ሂደት ለመከታተል፣ ለመሪዎቻቸው ያላቸውን አክብሮት ለማሳየት እና አጋርነታቸውን ለመግለጽ ከወትሮው በተለየ መልኩ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት በርከት ብለው በፍርድ ቤቱ ተገኝተዋል።
“ከዝንብ ማር አንጠብቅም” እያሉ ያሉት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ወደፊትም በኢትዮጵያ የሐይማኖት ነጻነት እና እውነተኛ ዲሞክራሲ እስኪመጣ ድረስ ትግላችንን አናቆምም ብለዋል።
No comments:
Post a Comment