ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያን የማህበራትን የመደራጀት ነጻነት ከገደቡ ቀንደኛ 5 ሀገራት አንዷ መሆንዋን አስታወቀ።
ጄኔቫ
የሚገኘው አለም አቀፉ የሰራተኞች ማህበር ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳስታወቀው የመሰባሰብና የመደራጀት ነጻነት
ካፈኑና አደገኛና ፍጹም የሆነ ገደብ የጣሉ ሲል ካወጣቸው 32 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ካምቦዲያ፣ ፊጂ፣
አርጀንቲናና ፔሩ በዋነኝነት አስቅቀምጦቸዋል።
የአይ ኤል ኦ ሪፖርት እንዳመለከተው እነዚህ ሀገሮች ከአንድ
እስከ ሰላሳ ሁለት በሚደርስ የመሰባሰብና የመደራጀት ነጻነት አፋኝነት ያስቀመጠው የድርጅቱ የመደራጀት ነጻነት
ኮሚቴ / የየሀገሮቹ የአሰሪዎችና የንግድ ማህበር መብት ተሞጋች ድርጅቶችን የተመረጡ ጉዳዮችን በመመርመርና ማህበራዊ
ውይይት በማካሄድ መሆኑን አስታውቆል።
በዚህ መሰረት የሰራተኛ ማህበሩ / በኢትዮጵያ በማህበርነት ለመደራጀት ከአራት አመት በፊት ማመልከቻ ያቀረበው ብሄራዊ የመምህራን ህብረት እስካሁን በማህበርነት እንዳልተመዘገበ አመልክቶል።
የአለም
አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት በዚህ ሪፖርቱ ላይ የኤትዮጵያ መንግስት የሰራተኞችን የማህበራት አደረጃጀት መብትና
ነጻነት የመምህራኑን ጨምሮ እንዲጠበቅ የብሄራዊ መምህራን ህብረትን ማመልከቻ ተቀብሎ ህጋዊ እንዲያደርገው መንግስትን
በጽኑ አስተንቅቆል።
አይ ኤል ኦ በዚህ ጥነቱ በአርጀቲና ስለተገደሉ 4 ሰራተኞችና ስለቆሰሉ ሁለት ሰዎች
ጉዳይ ምርመራ አድርጎ ዝርዝሩን ያቀረበ ሲሆን የአርጀንቲና መንግስት ከቤታቸው ያፈናቀአልቸው 500 ሰራተኞች
የመኖሪያ ቤት ጥያቄ በማቅረባቸው ግድያውን መፈጸሙን በመጥቀስ አርጀንቲናን ከኢትዮጵያ ጋራ መደራጀትን በጽኑ
በሚገድቡ ሀገራት ተርታ መድቦታል
No comments:
Post a Comment