Thursday, 8 November 2012

እነ አቶ በቀለ ገርባ ጥፋተኛ ተባሉ

ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

የኢትዩጵያ መንግስት አሸባሪ ሲል ክስ የመሰረተባቸው የመድረክ ስራ አስፈጽሚና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የውጭ ቋንቋ መምህር አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች 8 ሰወች በተከሰሱበት አሽባሪነት ክስ ጥፋተኛ ተባሉ።

ከሁለት አመት በፊት የፊደራል አቃቢ ህግ አሽባሪ ሲል ክስ የመሰረተባቸው አቶ በቀ ለገርባ እና አቶ አልባማ ሌሊሳ ኦፍዴንና ኦህኮን ሽፋን በማድረግ ለኦነግ እንዲሰሩ ወጣቶችን መልምለው አሰማርተዋል በሚል መሆኑ ይታወቃል።
የኦነግ አባል በመሆንም ወጣቶችን በመመልመል እንዲረብሹ አድርገዋል።ኬኒያ ድረስም በመላክ በህቡ በማሰልጠን ወጣቶችን አሰማርተዋል ተብለው የፊደራል አቃቢ ህግ ክስ የመሰረተባችው ወልቤካ ለሜ፤አደም ቡሳ፤ ሀዋ ዋቆ መሀመድ ሙሉ፤ ደረጀ ከተማ፤አዲሱ ሞንክሬ እና ገልገሎ ጉፋ የአሸባሪነቱ ክስ መከላከል አትችሉም ተብለው ጥፋተኛ ተሰኝተዋል።

ፍርድቤቱ የቅጣት ማቅለያ ሀሳብ ካላቸሁ አቅርቡ ሲል ለጠየቀው ጥያቄ አቶ በቀለ ገርባ ህይወቴን በሙሉ አድሎን ኢፍታሀዊነትንና ዘረኝነትን
በመቃወሜ በፈቃዴ ሳይሆን በፈጣሪ ትዛዝ ለኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲና ሰባአዊ መብቶች መከበር በመታገሌ አና መስዋት በመሆኔ አኮራለሁ ብለዋል ሳላጠፋ የፈረደብኝን ፍርድ ቤት ቅጣቴን ያቅልልኝ ብዩ ይቅርታ መጠየቅ ባለመፈለጌ አዝናለሁ ሲሉም አክለዋል አቶ በቀለ ገርባ እሳቸውን ያሰረው  መንግስት ባለቤታቸውን ከስራ አባሮ ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ያለገቢ በማስቀረት የፈጸመውን የበቀነኝነት እርምጃ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባ ማለሊሳ የአምንስቲ የልኡካን ቡድን ካናገራቸው በሆላ መንግስት የልኡካን ቡድኑ ተልኮውን ሳይጨርስ ካገር
በማስወጣት እነሱን ወደ እስር ቤት ያስገባቸው የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ነበር።

No comments:

Post a Comment