ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት በሰሜን ወሎ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉት ክፍሎች ውስጥ 44 ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው
ወደ አረብ አገራት ሄደዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ
ፓስፖርት በማውጣት ጉዞአቸውን እየተጠባበቁ ነው። መምህራንም እንደ ተማሪዎች የሚሰደዱ መሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ
አድርጎታል። መንግስት መምህራንን በመሰብሰብ ለማወያየት ሙከራ አድርጓል።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን በየመን የባህር ሰላጤ እንዲሁም በሰሀራ በረሀ የውሀ ሽታ ሆነው መቅረታቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በተደጋጋሚ መዘገባቸው ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment