መቀሌ ውስጥ አንድ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ እንግዳ ተክለፃዲቅ እና በዚህ ሳምንት
“መቀሌን በ24 ሰዓት ለቀህ ውጣ” ተብሎ የነበረው የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ የማነህ አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ
በፖሊስ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡
መቀሌን በ24 ሰዓት ለቀህ ውጣ? ? ?
በአንድ ወቅት የትግራይ ልማት ማህበር የህወሀት ንብረት እንደሆነ በመጻፌ ከአንድ ካድሬ የጅል ክርክር ገጥሞኝ ነበር።
የትልማ አመራር ሳይቀሩ የህወሀት ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸው እና ማህበሩ እየሠራ ያለው ተግባር ምን እንደሆነ በግልጽ ቢታወቅም፤ ካድሬው፡- ‘ትልማን እንዴት የህወሀት ትለዋለህ? ገለልተኛ ማህበር ነው’በሚል ነበር ሲሞግተኝ የነበረው-ልክ በዚያ ሰሞን “ራዲዮ ፋና እና ዋልታ የግል ናቸው” ብለው የሚሊኒየሙን አስቂኝ ቀልድ እንደነገሩን ሰውዬ ማለት ነው።

በጣም የሚያስቀው ነገር ታዲያ፦ ትልማን ገለልተኛ ነው በማለት ለመሞገት የሚሞክሩት ህወሀታውያን ፦”የትግራይ ህዝብ የህወሀት ብቻ ነው” ብለው ማሰባቸው ነው።የህወሀት ቡድናዊ(የጅምላ) አስተሣሰብ አልተመቸንም ያሉ የትግራይ ተወላጆች(የ አካባቢው ነዋሪዎች) ምን እንደሚደርስባቸው ብዙዎቻችን እናውቀዋለን። በ2002ቱ ምርጫ የ አረና አባል የነበረው አረጋዊ ዮሐንስ ህይወቱን ያጣው ሌላ ወንጀል በመስራቱ ሳይሆን -የአረና ለትግራይ አባል በመሆኑ ነው።ወንጀሉ-የህወሀት መሆን አልፈልግም ማለቱ ነው። በአቶ አስገደ ገብረስልሴ ለጆች በቅርቡ የተፈፀመው ገፍም የዚሁ አደገኛ አሰተሣሰብ ቅጥያ ነው፡፡እነሆ ከሰሞኑ ደግሞ አንድነት ፓርቲ በመቀሌ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ከመዘጋጀቱ ጋር ተያይዞ አስቂኝ ነገር እየሰማን ነው።
ፍኖተ-ነፃነት እንደጠቆመን በመቀሌ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር
የሆኑት አቶ እንግዳ ተክለፃዲቅ እና በዚህ ሳምንት “መቀሌን በ24 ሰዓት ለቀህ ውጣ” ተብሎ የነበረው የአንድነት
ፓርቲ አባል አቶ የማነህ አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል።
እስሩስ ተለምዷል እንበል። ለአቶ የማነ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ግን እስኪ በድጋሚ እዩት፦“መቀሌን በ24 ሰ ዓት ለቀህ ውጣ!?” ለወትሮው አንድ የውጪ ዜጋ በስለላ ስራ ተሰማርቶ ሲገኝ ነበር የዚህ ዓይነት እርምጃ የሚወሰደው።ይህ ምን የሚሉት ማስጠንቀቂያ ነው?አረ ወዴት እየተሄደ ነው?
“አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል” አለ ቴዲ?

No comments:
Post a Comment