Wednesday, 7 August 2013

ሰባር ዜና-አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ ከአገር ሸሽተው ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ገቡ!

August 6, 2013

ማክሰኞ ሐምሌ 30/2005
‹‹ህሊናዬ የማያምንበትን እንድሰራ ተገድጃለሁ›› አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ
የመንግስት ክስ መጨረሻው በውል እንኳ አልታወቀም፤ ቀጠሮውም ም እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም!
የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን፣ አሊሞችንና ዳኢዎችን መንግስት በሀሰት በሽብር ወንጀል ጠርጠሮ ከከሰሳቸዉ አንድ አመት ቢያልፍም እስካሁን እልባት ላይ አለመደረሱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ክስ ውስጥ ከከሳሽ መንግስት አቃቢያን ህግ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ቴድሮስ ባህሩ ‹‹ህሊናየ የማያምንበትን እንድሰራ ተገድጃለሁ›› በማለት አገራቸውንና ስራቸዉን ጥለዉ ከአገር ሸሽተው ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ መግባታቸው ተረጋገጠ፡፡ አቃቤ ሕግ ቴዎድሮስ ባህሩ ሲሰሩ የነበረበትን የስራ ጉዳይ ሰነድ እንኳን ሳያስረክቡ ጥገኝነት ጠይቀዉ ከነቤተሰባቸዉ አሜሪካ እንደገቡ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

Ethiopian Musilms
እንደ ታማኝ ምንጫችን ገለፃ ከመጀመሪያዉ የክስ ምስረታ ጊዜ ጀምሮ በተለይ የማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ፖሊሶች በሙያቸዉ ጣልቃ እየገቡባቸዉ ብዙ አቃቢያን ህግ ባለሙያዎች ከፍተኛ ምሬት እንዳለባቸው አስታውሶ፤ የአሁኑ የአቶ ቴዎድሮስ ሙያቸዉን ለቀዉ ከሀገር እንዲሰደዱ ያደረጋቸዉ ዋናዉ ምክንያትም እንደሚታወቀዉ ለረጅም ጊዜ በተጠርጣሪ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላቶች ላይ ስልጠና የተሰጣቸው ሰዎች የሀሰት የሰዉ ምስክርነት ጋዜጠኛም ሆነ ቤተሰብ እንዲገባ ባልተፈቀደበት ሁኔታ በዝግ ችሎት ሲሰማ የቆየ ሲሆን ይህም ተጠናቆ የቪዲዮ መረጃ መቅረብ ተጀምሮ ነበር፡፡

ለጥቂት ቀናት የታየዉ ቪዲዮ መረጃ ለረጂም ጊዜ ሲሰማ የነበረዉን የሀሰት የሰዉ ምሰክርነት ሙሉ በሙሉ ከንቱ ስላስቀረባቸዉ በአቃቢያን ህግ፣ በደህንነትና በፖሊስ መካካከል ከፍተኛ ዉጥረት ተፈጥሯል፡፡ ለዚህም ይመስላል የፍርድ ቤት ቀጠሮዉ አለመከበሩ ብቻ ሳይሆን ለመቼ እንኳ እንደሚቀጥል ሳይታወቅ ሂደቱ ሁን ተንጠልጥሎ የቀረዉ፡፡ አቶ ቴድሮስ ካሉበት ሁነው ሙሉ የነበረዉን ሂደትና መረጃዉን ለህዝብና ሚዲያ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment