Friday, 30 August 2013

የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን በቁጥጥር ስራ ዋለ!! አብርሃ ደስታ


ህወሓት በሁለት ቡድኖች መከፈሉ ይታወቃል። የደህንነት ሓላፊዎችም እንዲሁ በሁለት የተከፈሉ ናቸው። ሁለቱ የደህንነት ሓላፊዎች አቶ ጌታቸው አሰፋና አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ናቸው። በሁለቱም ከፍተኛ ጠብ አለ። አቶ ጌታቸው የነ አርከበ ቡድን ሲሆን አቶ ወልደስላሴ ግን የነ አባይ ወልዱ ሁኖ የወይዘሮ አዜብ መስፍን የቀኝ እጅ ነው።

ሁለቱም የደህንነት ተጠሪዎች በደም የሚፈላለጉ ናቸው። ባለፈው የህወሓት ጉባኤ አቶ ወልደስላሴ ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተጠቁሞ አቶ ጌታቸው ጠንከር ያለ ትችት በማቅረቡ ሳይሳካለት ቀርተዋል። መለስ በህይወት እያለ (በአዜብ ምክር መሰረት) አቶ ጌታቸውን በአቶ ወልደስላሴ ለመተካት አቅዶ ነበር (ሞት ቀደመው እንጂ)።


አቶ ጌታቸው ለመለስ ከማይታዘዙ የህወሓት መሪዎች አንዱና ዋነኛው ነው። ከመለስ ጋር በብዙ ነጥቦች ላይ አይስማሙም፤ የተባለውን ሁሉ የሚሰማ አይደለም። ጠንካራ ነው። ከሙስና የፀዳ የህወሓት ባለስልጣን አቶ ጌታቸው አሰፋ ነው።

የትግራይ ቡድን የአዲስ አበባውን ለማሸነፍ በመለስ ራእይ ስም ከህዝብ መነጠል ችላል። የአዲስ አበባው ደግሞ በሙስና ሰበብ የትግራይ ቡድኑን እያሰረ ይገኛል።

ዛሬ የኢህአዴጉ ሚድያ 'ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት' የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነግሮናል። ጥሩ መጠላለፍ መሆኑ ነው። አቶ ወልደስላሴ የነ አቶ ገብረዋህድ ጓደኛ ነው። አቶ ወልደስላሴ ከታሰረ ወይዘሮ አዜብ መስፍንስ?

ለማንኛውም ቸር ያሰማን!

No comments:

Post a Comment