Wednesday, 23 January 2013

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ ኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቀ

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በኢትዮጵያና በዛምቢያ መካከል  ትናንት ምሽት የተደረገውን እግር ኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን  ከማሰራጫ ቻናል  በድብቅ በመውሰድ ማስላለፉን ደርሸበታለሁ ሲል የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን(ካፍ)  መግለጹን ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ዘገበ
እንደ ዘገባው  የ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን  ሌሎች የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያሰራጩትን ጨዋታ በመስረቅ ጫዋታውን እንዳስተላለፈ የተደረሰበት በእረፍት ሰዓት የጨዋታው ስፖንሰር እንደሆኑ አድርጎ የበርካታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ ሢሰራ ነው።
በካፍ መግለጫ መሰረት የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፈጸመው ማጭበርበር ሁለት  መልክ ያለው ነው።


አንዱ ማጭበርበር ጫዋታውን ክፍያ ሳይፈጽም በድብቅ ማስተላለፉ ሲሆን፤ሁለተኛው ደግሞ በዚያው በተሰረቀ  የ አየር ሰ ዓት <<ይህን ጨዋታ  ስፖንሰር በመሆን ያስተላለፉላችሁ እነ እገሌ ናቸው” እያለ የበርካታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ መሥራቱ ነው።
ይህ የ ኢቲቪ ድርጊትም  በሁለተኛው ግማሽ  በጨዋታው ኮሜንታተር ሁለት ጊዜ   ተጋልጧል እንደ ጋዜጣው ዘገባ ።
ጨዋታውን ለማስተላለፍ ፈቃድ ያለው የቴሌቪዥን ጣቢያም በቸዋታው መሀል በፃፈው <<ቴክስት>> የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ድርጅት  ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይፈጽም ጨዋታውን  እያስተላለፈ ነው።>> በማለት ድርጅቱ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አሣስቧል።

የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ 31 ዓመት በሁዋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ቢያልፍም፤ መንግስት  ለቴሌቪዥን ስርጭት ከፍተኛ ገንዘብ ተጠይቄያለሁ፤ ይህም ዋጋ በጣም ተወዶብኛል>> በማለት ላለማስተላለፍ  መወሰኑ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ በዘርፈ-ብዙ ሙስና በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ብር የሚዘረፍባትና  ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው  ግለሰቦች ሳይቀሩ በሆነ ባልሆነው  ከፍተኛ ገንዘብ የሚያፈሱባት አገር መሆኗን የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ቀደም ካሉት ቀናት አንስቶ አስተያዬት ሢሰጡ የነበሩ ሰዎች፡<<  18 ሚሊዮን ብር እንኳን ለመንግስት ለዘመኑ ባለሀብቶች ቀላል ነው፤ በዚያ ላይ ሁሉንም ባይሆን የተወሰነውን ከ አገር ውስጥ ማስታወቂያ መሸፈን ይቻላል።መንግስት ማሳዬት ያልፈለገው በ እርግጥ ገንዘብ አጥቶ ነው?ወይስ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄድን ተቃውሞ በመፍራት ነው?>>በማለት ሲጠይቁ ነበር።

ለኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ የተመለከቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን፦<< በልጆቻችን በኮራንበት ቀን ለማይረባ ገንዘብ  ሲል ተራ ማጭበርበር ውስጥ በገባው መንግስት አፈርን፤ ግለሰብ ቢሰርቅ በህግ ይጠየቅ እንል ነበር። የሰረቀው <<ሌባ መቀጣት አለበት>>የሚል ህግ የፃፈው መንግስት ነው ሲባል ግን ከማፈር በስተቀር ምን እንላለን?>> ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ መንግስት የሰጠው አስተያየት የለም።

No comments:

Post a Comment