ሥርጉተ ሥላሴ 23.01.2013
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
የጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደስአለኝ ካቢኔ ገና በማለደው ከደም፤ ከግፍ፤ ከአድሎ፤ ነፃነትን ከማፈን ጋር መቆራኘቱ የተጠበቀ ነበር ማለት ይቻላል። በሦስት ምርኩዝ ተደግፎ በመወዛወዝ ላይ የሚገኘው የጠ/ሚኒስተሩ አማራር በሁሉም ዘርፍ አፈናውን መቀጠሉ „ጉልቻ ቢለዋወጥ.. „ የሚለውን የቀደመ ብሂል ተግባራዊነት ያረጋገጠ ሀቅ ነው።
እናትነት
ልዩ የሆነውን ሀገርን ይወክላል። እናትነት የቀደመው፤ የዛሬውን፤ ሆነ የነገው ትውልድ ፍጹም መሰረት ነው።
እናትነት የሴቶች ብቻ ጸጋ ነው። ይህ ዓለማቀፋዊ ሥያሜ የቋንቋዎች ሁሉ መጠሪያም ነው። እናትንት የከበረና እጅግ
የሚወደድ ፍጹም የሆነ የተግባር ማርዳ ነው።
እናትነት የመቻል፤ የርህርህና፤ የአጉራሽነት፤ የእራህብ
መዳህኒትነትን፤ የምህረትና የእርቅ ፤ የቤተሰብ ኃላፊነትን በብቃት በመቀበል የመወጣት ሰንደቅ ነው። በሌላ በኩል
ፍቅር ከነህግጋቱ የሚከትመው በእምየዋ በእናትዬና በማልያ ብቻ ነው። እናትነት ሚስትነትን፤ እህትነትን፤
አክስትነትን፤ አያትነትን፤ ጓደኝነት፤ አማካሪነት፤ አስተዳዳሪነት፤ መምህርትነትን በቅንብር አሟልቱ የሚገኝ ወርቅ
የተግባር ማሳ ነው። እናትነት የሰማይ ፍጹም ጸጋዊ ስጦታም ነው።
ታዲያ ምን ይሆናል፧ የእምነት ነፃነታችን
ተነፈገ ብለው ለወጡ እናቶች፤ አህቶች፤ እርግጫ፤ ድብደባ፤ መገፋት፤ መረገጥ ደረሰባቸው። በእናት ሀገራችን
ኢትዮጵያ ረጅም የሰላማዊ ትግል ሪከርድ የሰበረው የኢትዮጵያ የእስልማና እንቅስቃሴ የተለመደ ተግባሩንና ተልዕኮውን
ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ የፆታ፤ የዕድሜ፤ የሙያ፤ የዕውቀት፤ የብሄረሰብ፤ የቋንቋ መስፈርትን ሳይጠይቅ የዕምነት
ነፃነት ፍለጋ ዓርማው በማደረግ ነበር።
ከዕለት ዕለት የትግሉ ስልቱና መጠኑ እየሰፋና እያደገ መሄዱ
ያሰገው ወያኔ መራሹ አስተዳደር እጅግ በሚያሳዝንና በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ባለፈው ሳምንት … እናቶቻችን፤ እህቶቻችን፤
በእብሪትና በማናለብኝነት ጠቀጥቀ፤ ረገጠ፤ ደበደበ። በግፍ ከተጠቀጠቁት እናቶች ውስጥ ነፍሰጡሮች፤ ጤናቸውም
የተዛባ፤ አንጀታቸው በራህብ የታጠፈ፤ ረዳት የሌላቸው ሴቶች መኖራቸውም አያጠራጥርም። ድርጊቱ ማህጸንን ደም
ያስለቅሳል። እናት መከበር ሲጋበት እንዲህ … በዛ ግፉ በጣም በዛ ….
የእስልማና እህቶቻችንና አናቶቻችን
የድብደባ አሳዛኝ ድራማ የወያኔ መራሹ አስተዳደር ምን ያህል ከሰብዕዊነት የራቀ ስለመሆኑ ማረጋጋጫ ሲሆን ቀደም
ባለው ጊዜ „ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፈርኃ እግዚአብሄር ያላቸው ናቸው“ እዬተባለ ስነሰበክ የነበረውን መና
አድርጎታል። ስው የጠባውን ጡቱን እንዴት በሰደፍ ይቀጠቅጣል?!
እንዴት እናት ትደበደባልች? እንዴትስ
እናት ትረገጣለች? እንዴትስ እኛን የፈጠረ ማህጸን በግፍ ይጠቀጠቃል? አይደለም ድርጊቱ „እናትን መደብደብ“
የሚለው ቃል እራሱ በአንደበት ለመግለጽ እንኳን ይሰቀጥጣል። ወያኔ ግን ፈጸመው። ወሸኔ ብሎ ዓወጀ። ማለፊያ ብሎ
ቀጠለበት።
ይህ የሴት እህቶቻችን ግፋዊ ድብደባ ተሸክሞ የፊታችን የካቲት 29 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን
አያፍር ወያኔ! ዓይኑን በጥረጨው ያሸ ፈጣጣ አይደል? አከበርኩ ይለን ይሆናል። እኮ! በጠራራ ጸሐይ እዬገደለ፤
እያሰረ አይደል „እንባ ጠባቂ“ ድርጅት ያቋቋመው። ይሉንታ ያልፈጠረለት ዓይን አውጣው ጉድ …
መቼ?
ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ቢቸግርም ወያኔን ከሥረ መሰረቱ ለመንቀል የነፃነት ትግሉን በሁሉም መስክ አጠንክሮ
መቀጠሎ የተገባ ነው። መቼ? ለሚለው ጥያቄም ምላሽ ሰጩ ይኽው ነው። የምናፋጥነውም፤ የምናዘገየውም እኛው እራሳችን
ነን። ሁልጊዜም ወያኔ እያደባ ጥቃቱን ለሁሉ አዳረሰ። የሁሉንም ደጅ አንኳኳ። ከእንግዲህ ምን ይጠበቃል?! ከዚህስ
በላይ ምን አለና? እናት – ሚስት – እህት – አክሰት – አያት ከመደብደብ በላይ … ይጎርብጠን … ይቆጥቁጠን
.. ያንገብግበን …
እርግጥ ነው ወያኔ በእናቶቻችንና በእህቶቻችን የፈጸመው ግፍ እንደ እኔ የበለጠ ኃይል
ፈጥሮ፤ አዲስ ጉልበት ለትግሉ እንደሚያጎናጽፈው እርግጠኛ ነኝ። ይህ ግፍ፤ ይህ በደል፤ ይህ በሀገር ላይ ባይተዋር
መሆን፤ ይህ በእናት ምድር ላይ መሰደድ። ይህ በትርፍ ዜግነት መዋረድ የሚያከትመው ግን በሁለገቡ የነፃነት ትግል
ብቻ ነው። መፍትሄው ይህ ብቻ ነው።
ሥርዓቱ ሲነቀል፤ ሥርዓቱ ሲንጠለጠል — በህዝብ ፍላጎት የጸደቀ
የተወደደ ሕገ መንግስት ሲኖረን፤ ህዝብ እራሱ መምረጥ ብቻ ሳይሆን የመረጠውን አልተመቸህኝም ብሎ ማውረድ የመቻል
መብት ሲኖረው። ማለትም በአፈሙዝ ያልተሰነገ ሙሉ ሥልጣና ሰፊው ህዝብ ሲኖረው ፤ ከዘመኑ ጋር ሊሄድ የሚችል
ዓለምዓቀፍ – አህጉር ዓቀፍ – እንዲሁም ሀገራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ የሰከነ፤ የሰለጠነ የዴሞክራሲ ሥርዓት
ሲሰፍን ብቻ ከምጥ መጋላገል ይቻላል … በስተቀር ግን የማይወለድ ልጅ አርግዞ እንዲህ መገፈተር … እያሉ አለመኖር …
መተንፈሻ ቧንቧን አዘግቶ ማቃተት …
እንደ ማሰረጊያ … የዚህ ዓመት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን መከበር
ያለበት „በድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ“ ሲሰተፉ ግፍ ለተፈጸመባቸው እህቶቻችን፤ በደራ ወራዳ በሚዘገንን ሁኔታ የግፍ
ድርብ ለተፈጸመባት ፅንሷም ሳያሰበው ከሰላማዊው አንባው ወጥቶ አፈር ለገባው ዕንቡጥ እናት፤ እንዲሁም በእስር ላይ
ለሚማቅቁት ግን መንፈሳቸው ጎመራዊ የጽናት ሞገድ ለሆነው እንደ ጋዜጠኛ ርእዮት ዓለሙ ያሉትን እህቶቻችን በማሰብ
ቢሆን መልካም ነው።
እልፍ ነንና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
No comments:
Post a Comment