አንጋፋዉ የህወሀት መስራችና መሪ ስብሐት ነጋ የመለስ ራዕይ የሚባለው ነገር ትክክል እንዳልሆነና የወያኔ ራዕይ
የጋራ ራዕይ መሆኑን በያዝነዉ ሳምንት አጋማሽ አዲስ አበባ ዉስጥ ለንባብ ለበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጠዉ ቃለ
ምልልስ መናገሩን የአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ። ስብሐት ነጋ ይህንን የተናገረዉ ብዙዎችን ግራ
ያጋባዉንና በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔ አገዛዝ የሰጠዉን የሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት አስመልከቶ
የቀረበለተን ጥያቄ ሲመልስ ነዉ። ስብሐት ነጋ እሱ እራሱ በፈጠረዉ ህወሀት ዉስጥ ይህ ነዉ ተብሎ የሚነገር ስልጣን
ባይኖረዉም ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ግን ህወሀት ዉስት በተፈጠረዉ የመሪ እጦትና አለመተማማን የተነሳ ተደማጭነቱ
እየጎላ መጥቷል። በቅርቡ በየመገናኛ አዉታሩ አንደተስተዋለዉ ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በነበሩት ሁለትና
ሦስት ወራት ከፍተኛ ተሰሚነት ነበረዉ በረከት ስምኦን ድምጹ እየጠፋ ስብሐት ነጋ የኮከብ ተዋናይነቱን ቦታ እየያዘ
መምጣቱ ይታወቃል።
አንጋፋዉ የህወሀት አባል ስብሐት ነጋ ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮችን መሾም ሕገ-መንግስቱን አይጥስም ወይ ተብሎ
የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመለስ. . . . የሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሾም ያስፈለገው ክፍት የአመራር ቦታ
ስለነበር እንደሆነ ተናግሮ ሹመቱ መደረግ የነበረበት ነገር ነዉ ካለ በኋላ መልሱን በመቀጠል እኔ የማውቀው ነገር
የለም ሆኖም ሕገ-መንግስቱ ተጥሷል ከተባለ ያለው አማራጩ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ወይንም ሌላ አማራጭ መፈለግ ነዉ
እንጂ አዲሱ አደረጃጀት መቀጠል አለበት የሚልና የህወሀትን ህገወጥነትና ጋጠወጥነት በግልጽ የሚያሳይ አስነዋሪ መልስ
ሰጥቷል። ስብሐት ነጋም ሀነ ሦስቱን ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች የሾሙት የህወሀት ባለስልጣኖች አሁን ተፈጠረ የተባለዉ
የአመራር ክፍተት አንዴት በመለስ ዜናዊ የሃያ አንድ የልጣን ዘመን እንዳልተፈጠረ ከህዝብ የቀረበላቸዉን ጥያቄ
ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ስብሐት ነጋ የፈጠረዉና ለረጂም ግዜ የመራዉ ህወሀት ህገ መንግስቱን በጣሰ መልኩ ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒሰትሮችን
መሾሙ በግልጽ እየታወቀና ሰብሐት ነጋ እራሱም ይህንን ትልቅ ስህተት ለማረም ህገ መንግስቱን እናሻሽላለን እያለ
“እኔ ሥርዓት ከጣስኩ ከግንቦት 7፤ ከኦብነግና ከኦነግ በምን እለያለሁ” ብሎ መናገሩ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስርዐት
የሚጥሰዉ ወያኔ አንጂ ስብሐት ነጋ በስም የጠቀሳቸዉ ድረጅቶች አይደሉም ሲሉ ብዙዎች አስተያት በመስጠት ላይ
መሆናቸዉን የአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን አክለዉ በላኩልን ዜና ገልጸዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ “ራዕይህን እናሳካለን”፣ “አባይን የደፈረ መሪ”፣ “ቃልህን እንጠብቃለን” እና የመሳሰሉ
የውዳሴ ቃላት ጋር የመለስን ምስል የያዙና በውድ ዋጋ የተሰሩ ፖስተሮች አዲስአበባ ከተማን ጨምሮ ክልሎችን
ከማጥለቅለቃቸው ጋር ተያይዞ ግንባሩ ባልተለመደ ሁኔታ ግለሰብ ወደማምለክ ደረጃ ማሽቆልቆሉ በራሱ አባላት ጭምር
ከፍተኛ ትችትን አስከትሎበታል ሲል የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቮዥን ኢሳት ዘገበ።
እንደ ኢሳት ዘገባ ሰሞኑን በአዲስአበባ በተለይ ከኡራኤል ቤ/ክ እስከ ፍትህ ሚኒስቴር የመኪና መንገድ አካፋይ
መሃል ላይ በግምት በ30 ሜትር ልዩነት ተደርድረው የነበሩ የዘረኛው መለስ ፖስተሮች እንዲነሱ ተደርጓል።
ስለጉዳዩ አስተያየት የተጠየቀ አንድ የአዲስአበባ ነዋሪ ኢህአዴግ በተለይ የመለስ ራዕይ በሚባለው ጉዳይ እጅግ
ተጃጅሎ ከርሟል፡፡ ስንትና ስንት ችግር ባለበት ደሃ አገር በሚሊየን የሚቆጠር ብር ለመፈክር መጻፊያ ፖስተር
የመንግስትና የሕዝብ ገንዘብ ሲባክን መክረሙ እጅግ የሚያሰዝንና የሚያሳፍር ነው ማለቱን ኢሳት ዘግቡአል።
የፖስተሮቹ መነሳት፣አለመነሳት ለእኔ ትርጉም የለውም የሚለው አስተያየት ሰጪው የግንባሩ ካድሬዎች ቀድሞውንም
መፈክር በመጻፍ ሥራ የተጠመዱት የሕዝብ ድጋፍ ያገኙ መስሎአቸው የነበረ ሲሆን ሕዝቡ ግን በአድራጎታቸው ማፈሩን
ሲረዱ ከፍተኛ ገንዘብ ያወጡበትን ምስል በሚያዋርድ መልኩ እየነቀሉ ለመጣል አላመነቱም ሲል ትዝብቱን መግለጹን ኢሳት
አያይዞ ዘግቡአል።
No comments:
Post a Comment