Tuesday, 16 April 2013

ጋዜጠኛ እና መመህርት ርዮት አለሙ የ 2013 UNESCO / Guillermo Cano World Press Freedom Prize ተሸላሚ ሆና ተመረጠች- አቤ ቶክቻው!

ጋዜጠኛ እና መመህርት ርዮት አለሙ የ 2013 UNESCO / Guillermo Cano World Press Freedom Prize ተሸላሚ ሆና ተመረጠች፡፡ የሽልማቱ ስነስረዓት በዓለም የህትመት ነፃነት ቀን (World Press Freedom Day, on 3 May 2013) ማለትም ሚያዚያ 24 ቀን 2005ዓ.ም ይከናወናል፡፡

ርዮት ከዚህ በፊት IWMF (ኢንተርናሽናል ውመንስ ሚዲያ ፋውንዴሽን) ከተባለ አለም አቀፍ ድርጅት ስለ ፅናቷ የተሸለመች ሲሆን ይህኛው ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡

ጋዜጠኛይቱ በቅርቡ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የስነምግባር ጉድለት አሳይተሸል በሚል ክስ የፈፀመባት ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ቅጣቱ ተግባራዊ እንዳልተደረገባት ውስጥ አዋቂ ነገርኛል፡፡
ግጥም የሚመስል ነገር፤

መንግስቴ ሲቃጣው በቅጣት ላይ ቅጣት፣

አለም በአድናቆት ደጋግሞ ሸለማት

ማነው የሚፈታው እንዲህ ያለን ቅኔ…

አለም ታሟል ልበል ወይ አብዷል ወገኔ

(ወገኔ የተባለው ቤት እንዲመታ ብዬ እንጂ ገዢው ፓርቲን ለማለት ነው፡፡ በርግጥ “ወያኔ” ብለው በደንብ አድርጎ ቤት ይመታልኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ከመላው ኢህአዴግ ወያኔን ብቻ ገዢ ፓርቲ አድርጎ መሾም ለሚጢጢዋ ቡድን የልብ ልብ መስጠት ነው ብዬ በማሰብ ትቼዋለሁ… !)

No comments:

Post a Comment