Thursday, 7 March 2013

በባለፈው አመት የአሳሳ ግርግር የታሰሩ ከ45 በላይ ሙስሊሞች ተፈረደባቸው፡፡

ድምፃችን ይሰማ
ፍርዱ ከሁለት አመት እስከ አስራ አንድ አመት ይዘልቃል፡፡
በባለፈው አመት የአሳሳ ግርግር የታሰሩ ከ45 በላይ ሙስሊሞች ተፈረደባቸው፡፡ባለፈው ዓመት በኦሮሚያዋ አርሲ ዞን አሳሳ ከተማ ፖሊስ በመስጊድ ውስጥ ባስነሳው ግርግር ታስረው የነበሩ ወደ 48 የሚደርሱ የከተማዋ ሙስሊሞች ከፍተኛ ፍርድ ተፈረደባቸው፡፡ ውሳኔው የመንግስትን ጸረ ሙስሊም እንቅስቃሴ ገላጭ ተብሎለታል፡፡ በወቅቱ በተነሳው ግርግር የአራት ንጹሀን ሰዎች ሕይወት በፖሊስ ጥይት መጥፋቱ የሚታወስ ሲሆን በግርግሩ ሰበብም የታሰሩ ሴቶችን ጨምሮ ወደ 53 የሚጠጉ ሙስሊሞችም በሻሸመኔ ወህኒ ቤት የይስሙላውን ፍ/ቤት ጉዳይ ሲከታተሉ ቆተው ዛሬ የመጨረሻ ፍርድ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ 


በዚህም መሰረት ከ53 ታሳሪዎች 2 ሴት እና 3 ወንዶች በጥቅሉ 5 ሰዎች ከአንድ አመት እስር በኋላ በነጻ ሲሰናበቱ የጠቀሩት 48 ሙስሊሞች ከሁለት አመት እስከ አስራ አንድ አመት በሚዘልቅ እስር ብይን ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ፖሊስ ግርግሩ እንዲነሳ ምክንያት አድርጎ የጠቀሳቸውና የህጻናት የቁርአን አስተማሪ የሆኑት ሼኸ ስኡድ ይህ ነው በማይባል ማስረጃ አስራ አንድ አመት ከሦስት ወር የተፈረደባቸው ሲሆን፣ ሼኸ አብደላ ኪኒሶ ሶስት አመት ከስድስት ወር፣ ሼኸ ሁሴን ሶስት አመት ከስድስት ወር የተፈረደባቸው ሲሆን የተቀሩት 45 ሙስሊሞች እያንዳንዳቸው የሁለት አመት ከሶስት ወር እስር ተበይኖባቸዋል፡፡ የዛሬውን ችሎት ለመታደም በሻሸመኔና ዙሪያዋ የሚገኙ በርካታ ሰዎች የተገኙ ሲሆን የፍ/ቤቱ ውሳኔ ሲሰማም በአካባቢው ከፍተኛ የሀዘን ድባብ ተፈጥሮ እንደነበር ተሰምቷል፡፡
በፎቶው ላይ የሚታዩት በዛሬው እለት ብይን የተሰጠባቸው የአሳሳ ሙስሊሞች ናቸው፡፡
 
አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment