Sunday, 10 March 2013

‹‹በአማርኛ ተናጋሪነታችን ሠርተን የመኖር ልጆቻችንን የማሳደግ ህልውና ያጣን ነን፡፡››

‹‹በአማርኛ ተናጋሪነታችን ሠርተን የመኖር ልጆቻችንን የማሳደግ ህልውና ያጣን ነን፡፡›› የሚሉት እነዚህ ዜጎች “በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረብን ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ ከኖርንበት መሬት ተፈናቅለናል፡፡ ከአውሬ ጋር እየታገልን ያለማነውን መሬት ተነጥቀናል፡፡ እነሱ የሚሉን እናንተ አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል መኖር አትችሉም፡፡ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ይሉናል፡፡ አማራ ክልልን እንኳን ሰርተን የምንበላበት መሬት ቀርቶ ጎጆ ቀልሰን የምንኖርበት ቦታ ሊሰጡን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡” ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ፡፡

ተፈናቃዮቹም በመቀጠል ‹‹በቀበሌና በወረዳ ደረጃ የሚፈጸሙብንን ወንጀሎች ለዞንና ለክልል ብናመለክት እኛን ወንጀለኛ አድርገው ጥፋተኞቹን ያበረታታሉ፡፡ በፌዴራል ደረጃ ያሉ ባለስልጣናትም አንድም የሚሰጡት መፍትሄ የለም፡፡ ከላይ እስከ ታች ያሉት በጠቅላላው የሚሰሩት ወንጀል ተመሳሳይ ነው፡፡ ስለዚህ ከእንግዲህ መፍትሄ እናገኛለን ብለን አንጠብቅም፡፡›› በማለት ተስፋ መቁረጣቸውን ይናገራሉ፡፡

በመጨረሻም እነዚህ ተፈናቃዮች በቅሬታ የሚጠይቁት ቤት የሌለው መቆሚያና ማረፊያ የሌለው ሰው ቤተሰብ መስርቶ ልጅ ማሳደግ ንብረት ማፍራት አይችልም፡፡ እኛ ከእንግዲህ እንደሆንን እንሆናለን፡፡ ልጆቻችን ግን ማደግ አለባቸው፡፡ በማያውቁት ነገር ሊሰቃዩ አይገባም፡፡ ስለዚህ የአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ጉዲፈቻ የሚያሳድጉ ድርጅቶች እንዲወስዱልን እንፈልጋለን፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከደቡብ ክልላዊ መንግስት ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በመፈናቀል ላይ ያሉ ዜጎች ልጆቻቸውን በጉዲፈቻ የሚወስድላቸው አካል እንደሚፈልጉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታወቁ፡፡
‹‹በአማርኛ ተናጋሪነታችን ሠርተን የመኖር ልጆቻችንን የማሳደግ ህልውና ያጣን ነን፡፡›› የሚሉት እነዚህ ዜጎች “በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረብን ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ ከኖርንበት መሬት ተፈናቅለናል፡፡ ከአውሬ ጋር እየታገልን ያለማነውን መሬት ተነጥቀናል፡፡ እነሱ የሚሉን እናንተ አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል መኖር አትችሉም፡፡ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ይሉናል፡፡ አማራ ክልልን እንኳን ሰርተን የምንበላበት መሬት ቀርቶ ጎጆ ቀልሰን የምንኖርበት ቦታ ሊሰጡን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡” ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ፡፡

ተፈናቃዮቹም በመቀጠል ‹‹በቀበሌና በወረዳ ደረጃ የሚፈጸሙብንን ወንጀሎች ለዞንና ለክልል ብናመለክት እኛን ወንጀለኛ አድርገው ጥፋተኞቹን ያበረታታሉ፡፡ በፌዴራል ደረጃ ያሉ ባለስልጣናትም አንድም የሚሰጡት መፍትሄ የለም፡፡ ከላይ እስከ ታች ያሉት በጠቅላላው የሚሰሩት ወንጀል ተመሳሳይ ነው፡፡ ስለዚህ ከእንግዲህ መፍትሄ እናገኛለን ብለን አንጠብቅም፡፡›› በማለት ተስፋ መቁረጣቸውን ይናገራሉ፡፡
በመጨረሻም እነዚህ ተፈናቃዮች በቅሬታ የሚጠይቁት ቤት የሌለው መቆሚያና ማረፊያ የሌለው ሰው ቤተሰብ መስርቶ ልጅ ማሳደግ ንብረት ማፍራት አይችልም፡፡ እኛ ከእንግዲህ እንደሆንን እንሆናለን፡፡ ልጆቻችን ግን ማደግ አለባቸው፡፡ በማያውቁት ነገር ሊሰቃዩ አይገባም፡፡ ስለዚህ የአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ጉዲፈቻ የሚያሳድጉ ድርጅቶች እንዲወስዱልን እንፈልጋለን፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ፎቶ ፍኖተ ነጻነት
ምንጭ ፍኖተ ነጻነት

No comments:

Post a Comment