Wednesday, 20 March 2013

በለው ! ማስፈራራት ተጀመረ …..! አብርሃ ደስታ

Abraha Desta

ይሄው ሓሳባችንን በገለፅን ፌስቡካችንን (ኣፋችን) ለመዝጋት ተረባረቡ። ተሳካላቸው። ፌስቡካችን DISABLED ሆነ። ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር ገዢዎቻችን በፌስቡክ ፅሑፎቻችን መሸበራቸው ነው። የኔ ፌስቡክ መዝጋት መፍትሔ የሚሆን ኣይመስለኝም። (ፓስፖርቴን በመላክ በራሴ ስም እንደምጠቀም ለማስረዳት ሞክርያለሁ። እንደሚከፈትልኝ ተስፋ ኣለኝ። )

በዚሁ ኣላቆሙም። እየደወሉም …….. ማስፈራራት ተያይዘውታል።

በትግራይ የሚከናወኑ የፍትሕ ችግሮችና ሙስና ባጋለጥኩበት ፅሑፌ ብዙ ማስፈራርያዎች እየደረሱኝ ነው። የትግራይ ህዝብ ተጨቁኖ ሲያበቃ ጭቆናውን እንዳይጋላጥ መታፈን ኣለበት እንዴ??? ቢቻል ቢቻል ……. ህዝብ መጨቆን ተገቢ ኣይደለም፤ መቆም ኣለበት። ካልሆነ ግን በህወሓት መጨቆናችንና መታፈናችን ሌሎች ወንድሞቻችን ቢያውቁልን ምንድነው ችግሩ???

ህወሓት ድጋፍ እንዳያጣ ተብሎ እኛ እንሰቃይ? የትግራይን ህዝብ የፍትሕ ጉድለቶች ማጋለጥ ማንነት መለወጥ ኣይደለም። እንደኔ እንደኔ የህዝብ ዓፈናዎች ማጋለጥ ለህዝብ ነፃነት መቆም እንጂ የህዝብ ጠላት መሆን ኣይደለም። የህዝብን ጠላትነት የሚገለፀው ህዝብን በመጨቆን እንጂ የህዝብን በደል በማጋለጥ ኣይደለም።

ማስፈራርያው ……. (ከተወሰነ ውይይት በኋላ ችግር መነሩ ኣምኖ) “ምስጢራችንን እያጋለጥክ ለጠላቶቻችን መሳርያ እየሆንክ ነው (ምሽጥርና እናቃላዕኻ ኣደዳ ፀላእትና ኣይትግበረና)።” የህዝብ ‘ጠላቶች’ መኖራቸው እርግጠኛ ኣይደለሁም (የገዢው ፓርቲ ጠላቶች ሊኖሩ ይችላሉ)።

ደግሞ ቢኖሩስ??? ‘ጠላቶች’ እንዳይሰሙ፣ ገመናችን እንዳያውቁ ተብሎ ይበልጥ መታፈን ኣለብን? መሪዎቻችን እንደፈለጉ ይጫወቱብን? ጠላቶች እንዳይሰሙ ተብሎ ህወሓቶች እንደፈለጉ ይጨቁኑን??? በዚ ኣልስማማም።

ገመናቹ እንዳይጋለጥ ከፈለጋቹ ጥሩ መስራት ኣለባቹ፤ ፍትሕ ማስፈን ይጠበቅባችኋል፣ ለሰዎች ነፃነት መፍቀድ ይኖርባችኋል። ለችግሩ መፍትሔ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንጂ ዓፈናን የሚያጋልጡ መረጃዎች እንዳይወጡ ማፈን ኣይደለም። ዜጎች መጨቆን ብሎም ጭቆናውን እንዳይጋለጥ ማፈን ችግሩን ማባባስ ነው።

ጭቆናን ስላጋለጥኩ የህዝብ ጠላት ተባልኩ፤ ህዝብን የሚጨቁኑ ደግሞ የህዝብ ወዳጆች ተባሉ። እንዴት ነው ነገሩ??? ህዝብን የበለጠ ለመጨቆን (በስልጣን ለመቆየት) ድጋፍን ያሰባስባሉ። ድጋፍ ኣግኝቶ የስልጣን ዕድሜ ማራዘም የኣንድ ህዝብ የህልውና (በነፃነት የመኖር) ዋስትና ሊሆን ኣይችልም። የህዝብ ዋስትና ፍትሕ ማስፈን ነው። ፍትሕ ለማስፈን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል። ነፃ፣ ገለልተኛና ጠንካራ የመንግስት የፍትሕ ተቋማት መዘርጋት ኣለባቸው።

እንደውጤቱም የህዝብ መብት ይከበራል፤ ሰው ለነፃነቱና ህልውናው ዋስትና ያገኛል። ኣሁንም ኣልመሸም። ችግሩን ማቃለል እንጂ ሓሳባቸው በነፃነት ለሚገልፁ ዜጎች ማስፈራራት ግን መፍትሔ ሊሆን ኣይችልም። እኔ ስላስፈራራቺሁኝ መፃፌን ባቆም ችግሩ ኣቆመ ማለት ኣይደለም። እኔ ባልኖር ሌሎች ይፅፉታል።

It is so!!!

No comments:

Post a Comment