(ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በአዲስ አበባ አድርገውት የነበረው የመጨረሻ ለሊት ስብሰባ፤ እንዲሁም የስብሰባውን ቃለ
ጉባዔ ሙሉ ቃል እነሆ ይፋ አድርገናል። ስብሰባው የተደረገው ጠቅላይ ሚንስትሩ በአሜሪካ ቆይታቸው ወቅት አበበ ገላው
በተቃውሞ ካስደነገጣቸው አስራ አምስት ቀናት በኋላ፤ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 15 ቀን፣ 2004 ዓ.ም.
በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ነው። የመነጋገሪያ አጀንዳው በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ የተነሳውን ተቃውሞ አስመልክቶ
ሲሆን፤ በዝርዝሩ ውስጥ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የተሰጠውን ማብራሪያ ተካቷል። ስብሰባው ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ላይ
ሲጠናቀቅ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለአስቸኳይ ህክምና ወደ ውጭ አገር እንደሚሄዱ እና ከህክምናቸው በኋላ ውሳኔውን
ለመተግበር እንደሚሰሩ ቀጠሮ ተይዞ ነበር። ነገር ግን የታሰበው ሳይሳካ ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደወጡ ቀሩ፤ በዚያው
ሞቱ።
No comments:
Post a Comment