Tuesday, 5 March 2013

እናላችሁ… ምን ላይ ነበር ያቆምነው…አቤ ቶክቻው!!

የፌስ ቡክ ወዳጃችን … ህይወት እምሻውን አልቻልናትም፡፡ ትላንት የሸረሪት እና መሰል ነፍሳትን ፍቅር ከፍቅሩም ለጥቆ መጣፋትን፤ ዛሬ ደግሞ የእኛ የሰዎቹን ፍቅር… በተለይ ስራችንን ከሰራን በኋላ የምንኳሆነውን እያነሳች ነቁራናለች፡፡ ነቋሪውን ይያዝልሽ ብለን እንመርቃት…
ታድያ እዝችው ላይ አቶ ጁነዲን ሳዶ እንዴት እንደሁ እንጃ ትዝ አይሉኝም መሰልዎ… አቶ ጁነዲን ሆዬ ሞትኩልሽ አበድኩልሽ ሲሏት የከረሟትን ሚስታቸውን እስር ቤት አአስወርውረው ሲያበቁ፤ እርሳቸው ኬኒያዎችን “አባሪያኮ” ብለው ጥገኝነት ጠየቁ መባሉን ሰማን አይደል እንዴ…!

እኛ ቀድሞውንም አስመልክቶን ተናግረናል… “አብዮታዊ ዴሞክራሲ ልጆቿን እየበላች ነው…” ብለናል፡፡ አሁንም ቅም ያላት አይመስለኝም ገና ገና ገና ትበላለች ገና…! (ብዬ እጠረጥራለሁ…) ይሄኔ ተመስገን ማለት ነው እስከዛሬ እኛን ምስኪኖቹን ቁርጥምጥም አድርጋ ስትበላ የነበረች አብዮታዊ ዴሞክራሰሲ ዛሬ የገዛ ልጆቿን ብቻ ሳይሆን የገዛ ጥርሶቿን መብላት መጀመሯ ትንሽ ትንሽም ቢሆን ለእኛ እፎይታ ነው፡፡

የምር ግን ኢህአዴግዬ አቶ ጁነዲንን የመሰሰለ ጥርሷን ቁርጥምጥም አድርጋ ልትበላ መከጀሏ ምን ያህል ቢርባት ነው…! አያሰኝም… (ጥያቄ ምልክት) ቀላል ያሰኛል… (ቃል አጋኖ)
ኦቦ ጁነዲን በተሾሙባቸው መስሪያ ቤቶች በርካቶችን ሲናከሱ የነበሩ እንደነበሩ እያነሱ የሚወነጅሏቸው በርካቶች ናቸው፡፡ (ስማቸውን ዘርዝር ብለው ጉድ እንዳያደርጉኝ እንጂ…) የምሬን እኮ ነው ለምሳሌ በአንድ ወቅት እርሳቸው የበላይ በነበሩበት ዩንቨርስቲ ወደ ሶስት መቶ የሚጠጉ ምስኪን ተማሪዎች ከዩንቨርስቲ ተባረው እየዬ ሲሉ እርሳቸው “ስታለቅሺ ደስ አልሽኝ” የሚለውን እየዘፈኑ “ላሽ” አሉ እንጂ ስራይ መፍትሄ አላመጡም፡፡

አሁን አቶ ጁነዲን ሳዶ በተራቸው እያለቀሱ ሳይሆን እንደማይይቀር ይጠረጠራል፡፡ እኛ ግን ስታለቅሢ ደስ አልሽኝ አንላቸውም፡፡ “ወንድ ልጅ አይደሉም እንዴ…! ቆፍጠን ይበሉ እንጂ…!” እንላቸዋለን እንጂ!

እናላችሁ ትንላንት ህይወት እምሻው ምን ነገረችን አንዲት ሸረሪት አለች አለችን እሺ አልናት… ሸረሪቷ ሆዬ ፍቅር ሊሰሩ የሚመጡትን ሁሉ እልል ብላ ትቀበልና የልቧን ካደረሱላት በኋላ ኩርሽምሽም አድርጋ ትበላቸዋለች አለችን። እኛም ተገርመን ተገርመን… ሳናበቃ ጆሯችንን ወደ ምስራቅ ጣል ስናደርግ ኢህአዴግዬ የፍቅር አጋሮቿን ስትኮረሽም ሰማንና ወይ መመሳሰል ብለን እስካሁንም እየተገረምን ነው፡፡

በመጨረሻም 1

አቶ ጁነዲን ሆይ ወቅቱ የኬኒያ ምርጫ የሚከናወንበት ወቅት ነውና ከቻሉ ምርጫ እንዴት መከናወን እንደሌለበት የኢተያ ልምድዎን አውስተው ቢነግራቸው ኬኒያዎች “አሳንቴ!” ብለው ያመሰግንዎታል፡፡

በመጨረሻም 2

የኢህአዴግ ፍቅረኞች በሙሉ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍቅሯን ስትጨርስ ልትጨርሳችሁ እንደምትችል ከዚህ የበለጠ ማስረጃ የለም እና ሳያልቁ የለቀቁ ብሉሃን ናቸው እንዲል የአራዳ ልጅ ነገሩን ታንሰላስሉት ዘንድ እመክራለሁ!

No comments:

Post a Comment