Friday, 21 June 2013

Obang Metho’s Testimony before the Subcommittee on Africa

June 20, 2013

Testimony before the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and International Organizations. Given by: Mr. Obang O. Metho, Executive Director Solidarity Movement for a New Ethiopia


ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ስራቸውን እየሰሩ ነው ማለት ነው! አቤ ቶክቻው


June21,2013
ሰሞኑን ከኢህአዴግ ጋር የስጋ ዝምድና አላቸው እየተባሉ የሚጠረጠሩ ወዳጆቻችን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከአንዳች ሀይል ኢህአዴግን ለመገዳደሪያ የሚሆን ገንዘብ እንዳገኙ የሚያሰማ ድምፅ አጋርተውናል፡፡ 

ቡልቻ ደመቅሳ፡- ‹አንድነት› ፓርቲ የገዢዎች ልጆች ናቸው

* ዶ/ር ነጋሶ….. <አማራም ቢሆኑ ውስጡ ገብቼ አንድነትን አጠናክራለው> የሚል አቋም አላቸው።

Bulcha Demeksa - frm. Chair of Oromo Federalist Democratic Movement - Ethiopia* አፄ ኃይለስላሴ ኦሮሞነት አለባቸው ይባላል። ኦሮሞነት ስላላቸው የኦሮሞን ታሪክና ባህል አላቸው ማለት ግን አይደለም…..
* ቡልቻ “አማራ” የሚለውን ቃል ተጠቀመ ብለው [አንድነቶች] ሊከፋቸው አይገባም። ታዲያ እኔ ምን ብዬ ልግለጣቸው? እዛ ያሉትን እኔ የማውቃቸው በአማራነታቸው ነው።
* በአንድነት ውስጥ ያሉ አማራዎች ግን የጀነራል፣ የሀገረ ገዢ፣ የአምባሳደር የአስተማሪና የሲቪል ሰርቪስ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።

ግብፅ የህዳሴውን ግድብ በአየር ማጥቃት የሚያስችል አቅም የላትም ስትራትፎር


ግብፅ የኢትዮጵያን ሕዳሴ ግድብ በአየር ለማጥቃት ከኢትዮጵያ ያላት የአየር ርቀት ይገድባታል ሲል ስትራትፎር የተባለው መሠረቱን በአሜሪካ አገር ያደረገ ጂኦፖለቲካ እና ሴኩሪቲ ምርምርና ጥናት የሚያደርግ ተቋም በድረ ገጽ አስነብቧል።

ተቋሙ ባሰራጨው ትንታኔ ላይ እንዳሰፈረው፤ “በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው የአየር ርቀት ለግብፅ ጦር ሰራዊት ሁኔታዎችን አስቸጋሪ ያደርገዋል” ብሏል። ተቋሙ አያይዞም፤ “ግብፅ አየር በአየር ነዳጅ የሚቀባበሉ ተዋጊ የጦር ጀቶች ባለቤት ለመሆን ያደረገችው የአቅም ግንባታ የለም። 

Sunday, 16 June 2013

Subcommittee Hearing: Ethiopia After Meles

June 15, 2013

Subcommittee Hearing: Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights

Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations | 2172 House Rayburn Office Building Washington, DC 20515 | Jun 20, 2013 10:00am

ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

June 16, 2013

ከኢየሩሳሌም አርአያ

የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ «..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል… የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል… ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል።…

Saturday, 15 June 2013

አንለያይም! I am Proud of my people, the Ethiopians!

June 11, 2013by Teshome Debalke
Ethiopians are extremely modest beyond believe
I always wonder how people with such political turmoil and economic hardship ruled under a hollow ethnic tyranny as Woyane behave in exceptionally high standard of civility, discipline and impeccable class and unity never seen in the human experience.

አምባሳደሩ የግብፅን መንግስት አቋም አላብራሩም


የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አካል የሆነው የአባይ ወንዝ አቅጣጫ የማስቀየር ስራ መከናወኑንና በግብፅ በሱዳን እና በኢትዮጵያ የተቋቋመው የኤክስፐርቶች ቡድንን ሪፖርት ይፋ መደረግን ተከትሎ ከግብፅ በኩል እየተሰሙ ያሉ ጉዳዮችን በሚመለከት የመንግስታቸውን አቋም እንዲያብራሩ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ የቀረበላቸው በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደር እስከአሁን ማብራሪያቸውን አላቀረቡም፡፡ 

Friday, 14 June 2013

ፍርድ ቤት የባንክ ሂሳባቸውን ያገደባቸው የመንግስት ባለስልጣናትና ባለሀብቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ

ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቁጥር የኮ/መ/ቁ 134048 ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 429 የመንግሥት ኃላፊዎችና ባለሃብቶች በመንግሥትና በግል ባንኮች ያላቸው ገንዘብ የታገደባቸው መሆኑን ፣ የአንዳንዶች ደግሞ የድርጅታቸው የባንክ ሂሳብና መኪኖቻቸው እንዲታገድባቸው ትእዛዝ አስተላልፎአል።

የአባይ ፍጥጫን በተመለከተ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

June 14, 2013

እነሱ ከአባቶቻቸው አይበልጡም እኛም ከአባቶቻችን አናንስም!

ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ወረራና ደባ መፈፀም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ከመነሳቷ እጅግ በርካታ አመታት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ ሀገራችን ከግብፅም ሆነ ከሌሎች የተቃጣባትን ተደጋጋሚ ወረራዎች በመመከትና ጠላቶቿንም ድባቅ በመምታት ነፃነቷን ጠብቃ መኖሯ ለጠላቶቿ መራር የሆነ እውነት ነው፡፡ በተለይም ከጥንት ጀምሮ የአባይን ምንጭ ለመቆጣጠር ጥልቅ ምኞት የነበራት ግብፅ በሃገራችን ላይ የፈፀመችውን ግልፅና ድብቅ ወረራ በመመከት ተደጋጋሚ ሽንፈትን አከናንበን መልሰናታል፡፡

President Museveni has warned the Egyptian government!!

President Yoweri Museveni has sternly warned the Egyptian “government and other groups” against making “chauvinist and irrational statements” in the wake of Ethiopia’s decision to construct a multi-billion dollar electricity dam, Chimp Corps report.
 
Museveni writes a condolence message at the funeral ceremony of departed Ethiopia President Meles Zenawi. Museveni maintains close ties with Ethiopia (INTERNET PHOTO)

በወገኖቻችን ስደት ላይ ስለሚሰማው የሰሞኑ ፌዝና ቧልት ጥቂት ስለማለት

June 13, 2013

ዶ/ር ዘላለም ተክሉ
በሰሞኑ ከዓባይ ተፋሰስ ፖለቲካ ቀጥሎ ታላቁ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ  ከሃገራችን በመቶ ሺዎች ተሰደው ስለሚወጡ ወገኖቻችን መሆኑ ይገነዘቧል:: ከ”መለስ ራዕይ” አስፈጻሚው “ጠ/ ሚንስትር” በተዋረድ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ እንደ ገደል ማሚቶ  በሚስተጋባው ዘገባ፣ ወገኖቻችን ከአረብ ሃገራት እስከ ደቡብ አፍሪካ፣አውሮጳና አሜሪካ ድረስ ህጋዊና ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ተሰደው የሚኮበልሉት “ባደገችው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያሉትን የስራና የንግድ ዕድሎች አሟጠው ሳይገነዘቡና ሳይሞክሩ” እንደሆነ እየተነገረ መሆኑ ሁላችንን እያስስገረመን እያስደመመን ይገኛል::

ከአረብ ሃገራት ሰማይ እስከ ሚሊንየም አዳራሽ! እኔን ያስፈራኝ ጎርበጥባጣው መንገድ…

ከአረብ ሃገራት ሰማይ እስከ ሚሊንየም አዳራሽ! እኔን ያስፈራኝ ጎርበጥባጣው መንገድ…

ይድረስ ለአባይ ባለበት… (ከአቤ ቶኪቻው)

June 13, 2013

አቤ ቶኪቻው
ጉዳዩ፤ በጣም አበዛኸው…!
Abe Tokichaw's letter to Abbay (Nile) River.
ይቺ ለአባይ የተፃፈች ደብዳቤ ናት፡፡ አፃፃፏ “ስዲ ወ ግጥሚ” አይነት ናት፡፡ ትንፋሽ ያለው ሰው እንደ ግጥም ቢወርዳት ግጥም ግጥም ትመስላለች፡፡ ትንፋሽ የሌለው ሰው ደግሞ እንዲሁ ቢዘልቃት ስድ ንባብ ትሆናለች፡፡ እስቲ እንደዚህ አዳዲስ ፈጣራዎችን እናስተዋውቅ… ብዬ አካብጄ በአዲስ መስመር እጀምራታለሁ ትድላችሁ…!!

Who Will Win Over Nile, Egypt or Ethiopia?

June 13, 2013by Seyoum Teshome Akele
The Nile case has again started becoming hot among riparian nations, particularly Egypt and Ethiopia, and somehow Sudan, too. This is not the first time we (Ethiopians) happened to witness this kind of superfluous confrontation as well as naïve ownership claim, especially by Egypt, not fully understanding yet the nature and complexity of River Nile, like any other shared international rivers. The first being some 8 or so years back. 

Thursday, 13 June 2013

ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ የቁንጅና ፈቃድ ቢሮ ሃላፊ


ፋሲል አ.

ሰሞኑን ቤቴልሄም አበራ(ቤቲ) የተባለች ወጣት ኢትዮጵያዊት በቢግ ብራዘር አፍሪካ  ትእይንት (show) ላይ ከሴራሊዮኑ ቦልት ጋር ፈጸመችው ስለተባለው ወሲብ በተለየዩ  ማህበራዊ ድረ-ገጾች እና መገናኛ ብዙሃን የሚሰጠው አስተያየት እንደቀጠለ ነው::በዚህ የቢግ ብራዘር ትእይንት ላይ ከዚህ በፊት በተደረጉ ውድድሮች ላይ የተለያዩ ጥንዶች እንደዚህ አይነት የወሲብ ድርጊት መፈጸማቸው የተዘገበ ሲሆን ይህ የቢግ ብራዘር ትእይንት በባህሪው ለእንደዚህ አይነት ድርጊቶች የተጋለጠ ለመሆኑ ከዚህ ቀደምም ሆነ አሁን የተደረጉት ድርጊቶች በቂ ማሳያ ናቸው :: 

Tuesday, 11 June 2013

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እኔ እንደማውቀው

ስመኝ ከፒያሣ
http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/06/eskindir.jpg
የኢትዮጵያ ፕሬስ የሚታወሰው ወይም የሚነሳበት ዘመን ቢኖር ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ ኢህአዴግ መላ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረበት ከግንቦት 20/1983 ዓ.ም እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ ምንም ያደረገው ነገር አልነበረም፡፡ ፀጥታ የነገሰበት ጊዜ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ማለትም 1985 ዓ.ም ላይ የኤርትራ ሪፈረንደም የተፈቀደበት ጊዜ ነበር፡፡
ከዛ በኋላ ደግሞ በሙሉ ነፃነት ነገሮችን መግለፅ ተጀመረ፡፡


ዓባይን በራሳችን መገደብ አንችልም፤ እስካሁን የተሰበሰበው ገንዘብ ገና 6 በመቶ ያህሉ ነው አምባሳደር ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ!!


   ኢሳት ዜና -ህዳሴውን ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዋጮ ብቻ መሸፈን ወይም ዳር ማድረስ እንደማይቻል አምባሳደር ኃይሉ፡- ወልደጊዮርጊስ ገለጹ።

በሥራ ዓለም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት በተለያዩ ኃላፊነቶች የሠሩት፣ የፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉትና በአሁኑ ጊዜ በዐባይ ዙሪያ መንግስትን እያማከሩ ያሉት አምባሳደር ሀይሉ ወልደጊዮርጊስ ይህን የገለጹት፤ እሁድ ለህትመት ከበቃው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር በዓባይ ግድብ ዙሪያ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው።

Monday, 10 June 2013

Ethiopians stormed a downtown hotel in Calgary, Canada

A CPS member observes the demonstration outside of the Ramada Calgary Downtown hotelA gathering of hundreds of noisy demonstrators mobbed a downtown hotel Sunday afternoon to protest dictatorial conditions in Ethiopia.
A meeting of the Etho-Abay Association of Calgary was being held at the Ramada Downtown Calgary Hotel on 8 Ave. 

Ethiopia: Rise of the Blue Cheetahs!

Monday commentary: 6/9/2013
by Alemayehu G. Mariam


Just feeling proud and blue all over
“Everyday, everyday I have the blues” sang B.B. King on his faithful guitar Lucille. Everyday, everyday for the last eight years I’ve had the blues, the “193/763 Blues”. “Ain’t gonna stop until the twenty-fifth hour, ‘Cause now I’m living on blues power,” belted out Eric Clapton. I am feeling blue power too!

አንድ ብስጭት፤ ጉድ በል ሰላሌ ኢትዮጵያ አይደለህም ተባልክ…አቤ ቶክቻው!!!

http://www.abetokichaw.com/wp-content/uploads/2013/06/946655_4270475898383_1063122582_n.jpg
አበበ ቶላ ፈይሳ እባላለሁ፡፡ አባቴ አቶ ቶላ ፈይሳ ልጅነቱን በኦሮምኛ ቋንቋ ተረት እየሰማ፤ ወጣትነቱን በኦሮምኛ ቋንቋ እያዜመ፤ ጉልምስናውን በኦሮምኛ እየፎከረ፤ እርጅናውን በኦሮምኛ እየመከረ የኖረ ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ አባቴ የአባት እና እናቱ ቋንቋ ኦሮምኛን አጥብቆ እንደሚወደው ያህል እኔ ልጁን እና እናት ሀገሩ ኢትዮጵያንም ከመውደድ በላይ ይወደናል፡፡

Sunday, 9 June 2013

ድንቁርና የሚድንም የማይድንም ሕመም ሊሆን ይችላል (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
Prof. Mesfin Woldemariam
ከጥቂት ቀናት በፊት አንዳንድ ሰዎች በዓባይ ጉዳይ ቀረርቶና ሽለላ ማሰማት ሲጀምሩ ከባድ የሆነ የመረጃ እጥረት መኖሩን ስለተገነዘብሁ ስለግብጽ የኃይል ሚዛን ደረቅ መረጃ የጦርነትን መጥፎ መልክ ከሚገልጽ አስተያየት ጋር አቀረብሁ፤ የወያኔ ሎሌዎች ወዲያው በእኔ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ከፈቱ፤ ድንቁርናው ከዚህ ይጀምራል፤ ማሪዮ ፊልሞና ብሩኖ ‹‹በአፍራሽ አስተሳሰባቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዛሬም የግብጽን ጦር ገና ከሩቁ እንድንገብርለት ጉትጎታ ይዘዋል፡፡››

አርዐያ ተስፋማርያም፣ ሰሜናዊው ኮከብ

Ethiopian Journalist Araya Tesfamariam
ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም

ቴድሮስ ሃይሌ (tadyha@gmail.com)

አርዐያን የማውቀው በሃገራችን ይታተሙ ከነበሩት ነጻ ጋዜጦች በሲሳይ አጌና ባለቤትነት ይተዳደር በነበረው ስመ ጥሩው ኢትዮጽ ጋዜጣ ላይ በተመስጦ እከታተለው ከነበረው የጋዜጣው አምዶች ውስጥ ከህወሐት መንደር በሚል አብይ ርዕስ ስር በተከታታይ ይቀርብ የነበረው የወያኔን ገበና ገላጭ ጽሑፍ እየሩሳሌም አርዐያ በሚል የብዕር ስም ይጽፍ የነበረው ብርቱው ጋዜጠኛ አርዐያ ተስፋማርያም ምንም ቅርርብ ኖሮን ባያውቅም የጽሁፉ እድምተኛ በመሆን ብዙ ቁም ነገር የቀሰምኩበት በመሆኑ በቅርብ የማውቀው ያህል የሚሰማኝ ከመሆኑም በላይ የደረሰበት ግፍና በደል ከእርሱ አልፎ ቤተሰቡን ጭምር ችግር ላይ መጣሉን ስከታተለው የነበረ ሲሆን እንዲህ አይነቱን በዚህ በኔ ትውልድ ውስጥ በብርሃን ተፈልጎ የማይገኙ ጥቂቶች ብቻ ጥቅምና ምቾትን ንቀው መስሎ በማደርና ሕሊናን በመሸጥ ከሚገኝ የተደላደለ ህይወት ትቶ ላመነበትና አላማ ጸንቶ ለተሰለፈበት ሙያ ተግቶ በቆራጥነት የሚቆም ዜጋ ተምሳሌትነቱ ለትውልድ ጠቃሚ በመሆኑ አንድ ነገር ለማለት ሳመነታ ሰሞኑን በአጋጣሚ ይህን ጎበዝ ጋዜጠኛ የተመለከተ ስብሰባ መኖሩን ስመለከት ሳስበው የቆየሁትን ለመተንፈስ አጋጣሚው መልካም ከመሆኑም በላይ የዝግጅቱ ማስታወቂያ ላይም ያለኝን ቅሬታ ለወገን ለማካፈል ፈለግሁ።

አቶ ማርክነህ የቀበሩት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተያዘ

የገቢዎችና ጉምሩክ ዓቃቤ ህግምክትል ዳይሬክተር የነበሩትአቶ ማርክነህ አለማዮሁ አሸሽተውት የነበረው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ መያዙን የምርምራ ቡድኑ አስታወቀ።
የምርመራ ቡድኑ እንዳስታወቀው አቶ ማርክነህ አለማሁበወንድማቸው አማካይነት ለመሰወርአቅደው የቀበሩት አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ሺህ ብር የተገኘው
ግንቦት 30/2005 በወላይታ ሶዶ ዙርያ ወረዳ ወራንዛላሸ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።

ግብፅ በቅድመ ሁኔታ የታጠረ የድርድር ጥያቄ አቀረበች -ኢትዮጵያ ቅድመ ሁኔታውን አልተቀበለችም


ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለመጀመር የዓባይን ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ በጊዜያዊነት ከቀየረች በኋላ፣ ግብፅ የፈጠረችው ፖለቲካዊ ውጥረት ባለፈው ሳምንት የተለየ መልክ ይዟል፡፡
ሱዳን በግድቡ ላይ ተቃውሞ እንደሌላት በመግለጽ ግብፅን ብቸኛዋ ተቃዋሚ አገር እንድትሆን አድርጋታለች፡፡ በሌላ በኩል ግብፅ በጉዳዩ ላይ የተለሳለሰ የሚመስል አቋም በማሳየት በቅድመ ሁኔታ የታጠረ የድርድር ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቅርባለች፡፡

Saturday, 8 June 2013

June 5th, 2013: Ethiopian Canadians Held a Protest Rally in Ottawa

by Mintesnot Zewde Berhane, Toronto, Canada
Toronto demonstration against tyrant government of Ethiopia.
 Ethiopian Canadians gathered in the early morning of June 5th, 2013 from the two ends of the City of Toronto to join their compatriots in Ottawa in hundreds to protest against the series of human rights violation by the ever increasingly tyrant government of Ethiopia.

Friday, 7 June 2013

The Anguish of Higher Education Students in Ethiopia

by Zelalem Abate
E-mail: zelalem.abate1@gmail.com


Addis Ababa University (formerly Haile Selassie I University) is a university in Ethiopia.Academic activities such as studying, teaching, inventing, leading, administrating and other responsibilities in a university or college require at a minimum academic freedom. Unfortunately, however, academic freedom in higher education institutions of Ethiopia is drier than the Sahara desert. 

አርበኞች ግንባር በሁመራ አካባቢ በወያኔ 35ኛ ክፍለጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ

ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሉግዲና በበረከት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

Ethiopian People Patriotic Frontነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ከወያኔ መከላከያ ጋር በሉግዲ ባካሔደው ውጊያ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።
በግንቦት 25-2005 ዓ.ም በቀጠለው ውጊያ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት በተሰኘ ስፍራ ከአምባገነኑ አገዛዝ 35ኛ ክፍለጦር እና ከሚሊሻ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ በተከታታይ በስምንት/8/ ዙር ፋታ የለሽና እልህ አስጨራሽ ውጊያ 148 ሙት፣ 374 ቁስለኛ፣ 31 ክላሽንኮፍ፣ጠመንጃ 47 የእጅ ቦንብ ፣2 ስናይፐር፣ 3 መትረየስና የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርኳል።

Thursday, 6 June 2013

The WHY question: The battle for freedom from Woyane tyranny

The battle for freedom in Ethiopia is a struggle to get the answer for the WHY questions. It is a war between tyranny and freedom movements to keep the people ignorant or enlightened respectively, noting more or less to it. Which sides of the battle we choose to be determines freedom and the fate of our people. Those that skirt the WHY question to fit their agenda are parasites that live off the blood and sweat of our people; expanding the grips and extending the life of tyranny. They are the living dead, noting more or less to them.

SEMAYAWI PARTY HAS BROKEN THE SPELL

Semayawi (Blue) Party at last a light has appeared at the end of tunnelImru Zelleke (Ambassador)

Thanks to the Semayawi (Blue) Party at last a light has appeared at the end of tunnel that leads to freedom. Those that have to be congratulated the most are the Ethiopian People at large who responded to the appeal in massive numbers with enthusiasm and dignity. They expressed clearly and without ambiguity their demands and aspirations.

አገዛዙ ለሰላማዊ ሰልፉ ዕውቅና የሰጠው ፈጽሞ አማራጭ ስላልነበረው ነው – በእኔ አመለካከት!

ECADF Statment regarding Addis Ababa's demonstration

ክብሩ ደመቀ
ሕወሓት/ኢህአዴግ በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት የተካሄደውን ሰላማዊ ዕውቅና የሰጠው ወድዶና ፈቅዶ ወይም ሕገ-መንግሥቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከትቶት አልነበረም። ይልቅስ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ሁለት ነገሮች ናቸው ፡-
1ኛ – ወቅታዊነት! በወቅቱ የሚካሄደውን ርዕሰ-ሃገራትና ከፍተኛ የዓለም ባለሥልጣናት (እንደ ጆን ኬሪ እና ባንኪ ሙን) በተገኙበት እንዲሁም በዓለም መገናኛ ብዙሃን እየተዘገበ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት ጉባዔ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና መጠየቁ፣

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ (መንግስት ለሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም እንጠይቃለን!)

Blue Party Ethiopia

ሰማያዊ ፓርቲ

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ደማቅ ሆኖ ተካሂዷል፡፡ ለዚህ ሰልፍ መሳካት ከፍተኛ ድጋፍና አስተዋፅኦ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙኃንና በሰልፉ ለተሳተፉ ዜጎች እንዲሁም ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለረዱ የፀጥታ ኃይሎች ፓርቲያችን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

We need justice and freedom!

http://ethiopia.ecadf.netdna-cdn.com/articles/wp-content/uploads/2013/06/semyawi-demo.jpgby Abebe kassa
We need justice and freedom was one of the main slogans demonstrators held on June 2 peaceful demonstration in Addis Abeba. Peaceful demonstrations were de facto banned by the regime since the aftermath of 2005 elections. 

Wednesday, 5 June 2013

Egypt President politicians plotting against Ethiopia's dam English su...

Aigaforum editor to appear in a California court over defamation

By Hilina Dawit
June 4, 2013


Isayas Atsbeha
Isayas Atsbeha
SAN JOSE, California -- The controversial publisher and editor of Aigaforum.com, widely known among exiled Ethiopians as the “voice of tyranny”, has been sued in the Superior Court of Santa Clara, California, for deliberately spreading politically-motivated defamation and inciting hatred and violence. 
 

ሰበር ዜና – ኢትዮጵያ ለግብፅ ምላሽ ሰጠች- ”ግብፅ የቀን ሕልም ላይ ነች” አቶ ጌታቸው ረዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ

ሰበር ዜና

ኢትዮጵያ ለግብፅ ምላሽ ሰጠች- ”ግብፅ የቀን ሕልም ላይ ነች” አቶ ጌታቸው ረዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ
”አህራም ኦን ላይን” የተሰኘው የግብፅ ድህረ ገፅ ጋዜጣ በዛሬው ግንቦት 28፣2005 ዓም ባወጣው ዘገባ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ብዙ ያልተሳካ  ሙከራ ማድረጓን መግለፃቸውን እና  አሁን ”በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ማድረግ እና ሴራ ማድረግ” የሚሉ አስተያየቶች ጊዜ ያለፈባቸው የከሸፉ ሃሳቦች  ”old failed concept.” እና የቀን ሕልም ”day dreaming.” ከመሆን ያልዘለለ መሆኑን አክለው መናገራቸውን ዘግ ቧል።

Breaking News: Armoured Vehicles Surround Ethiopian Embassy In Cairo

 
Awramba Times – The Ethiopian embassy in Cairo is surrounded by heavily armed personnel and armoured vehicles. Ethiopian citizens, both refugees and Ethiopian-passport holders, are savagely harassed and beaten by ordinary Egyptians and the police everywhere they move. 

Semayawi Party Demonstration, Addis Ababa (video)

The call for demonstration by Semayawi Party (Blue Party) answered by thousands of Ethiopians. Tens of thousands march in Addis Ababa today June 2nd 2013 and chanted slogans denouncing the dictatorial TPLF regime.

“Aneleyayem” We are Inseparable!


by Tedla Asfaw
The Ethiopian Muslims and Christians says "We are inseparable".
“Anelayayem Egna”, “We are inseparable”. Who are We? The Ethiopian Muslims and Christians. This rally cry had indeed worried the Ethiopian regime cadres after a quarter million people went out to streets of Addis Ababa this past Sunday, June 2, 2013. The response from the regime for we are inseparable is that you are separable.

Tuesday, 4 June 2013

ፕሮፌሰር መስፍን ይናገራሉ፦


Imageጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመጭም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ? 

ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ መንግስት የሰጠውን ማስፈራሪያ አመራሮች እና የህግ ባለሙያዎች ውድቅ አደረጉት

march in the streets of Addis Ababa.ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት25 ከፍተኛ ህዝብ የተገኘበትን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ የኢህአዴግ የጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሬዲዮ ፋና ሲናገሩ ” የሃይማኖት አክራሪነትን አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው ዛሬ በጠራው ሰልፍ ተጋልጧል ” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ተነስታለች ! (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

The long youth march to freedom and dignity has begun in Ethiopia. It is beautiful. 
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ግንቦት 20 1983 መለስ ዜናዊና ሽምቅ ተዋጊዎቹ ከላሽኒኮቭ ደግነው የጅ ቦንቦች ታጥቀው አዲስ አበባን ወረው ገቡባት፡፡

Egyptian politicians suggest attacking Ethiopia over Nile dam

Politicians meeting with Egypt’s president proposed hostile acts against Ethiopia to stop it from building a massive dam on the Nile River upstream. Some didn’t seem to know they were on live TV at the time.
 
Ethiopia has begun diverting the Blue Nile, a major tributary to the Nile, as part of a giant dam project, sparking unease in downstream Egypt. Some Egyptian politicians in a meeting Monday proposed hostile acts against Ethiopia to halt the $4.2 billion Nile dam.
WILLIAM LLOYD-GEORGE / AFP/GETTY IMAGES
Ethiopia has begun diverting the Blue Nile, a major tributary to the Nile, as part of a giant dam project, sparking unease in downstream Egypt. Some Egyptian politicians in a meeting Monday proposed hostile acts against Ethiopia to halt the $4.2 billion Nile dam.

Monday, 3 June 2013

ESAT Wazana Kum Neger Ethiopia

New Video: Semaywi Party Demonstration -- Addis Ababa

አዲስ አበባ ልጆች አኮራችሁኝ!

እንደልቡ (ዳግም)

“ወጣቱ እንዲህ ሆንዋል እንዲያም ሆንዋል…” ወጣቱን ከማያውቁት ሰዎች የምሰማው የዘወትር መዝሙር ነበር። ወጣቱ ግን ማን እንደሆነ ባገኘው አጋጣሚ አስመሰከረ!!! ነጻነት የሌለው ህዝብ በበረት ዉስጥ እንደታጎረ እንስሳ ነው፣ ይህም ከፍተኛ የመዋረድ ስሜት ይፈጥርና አምሮን ይጎዳል፣ በሞራል ላይ ተመርኮዘን ማድረግ ከሚገቡን ነገሮች ሳናውቅ እንቆጠባለን፣ ውሸታም እና አስመሳይም እንሆናለን… ስለዚህ ነጻነታችንን ማስመለስና በራሳችን የምንተማመን ኩሩ ዜጋ መሆናችንን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ምከረው ምከረው እምቢ ካለ ሞክረው…አቤ ቶክቻው!!

እኔ እኮ ሁልጊዜ ግራ የሚገባኝ አቶ ሽመልስ ከማልን በእንዲህ ያለው ጉዳ ላይ ለምን እንደሚያጋፍጧቸው ነው፡፡ እርሳቸውስ ቢሆኑ አሁንስ አበዛችሁት ራሳችሁ ተናገሩ አይሉም እንዴ…!
ውይ የኔ ነገር ቆይማ ነገርን ከስሩ እንዲሉ ለወጋችን ትንሽ መሰረት ብጤ እንጣልላት፡፡

Ethiopia Watch Out the Wordings: The International Panel of Experts on the Nile and its Final Report

International-Panel-of-Experts-on-Renaissance-Dam
June 2, 2013
Zerihun Abebe Yigzaw

The International Panel of Experts (IPoE) on the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) has submitted its final report to the governments of the three riparian states-Ethiopia, Egypt and the Sudan. Ethiopia in good faith called the two riparian states to form the international panel of experts so as to investigate if the GERD will cause any significant negative effect to the downstream states. 

Sunday, 2 June 2013

የፍርሀት ጭጋግን የገፈፈው ታሪካዊ ሰልፍ (ልዩ ጥንቅር)

የፍርሀት ጭጋግን የገፈፈው ታሪካዊ ሰልፍ
                                          (ልዩ ጥንቅር)
(ኢሳት)ሰማያዊ ፓርቲ  በዛሬው ዕለት የጠራው ሰልፍ እጅግ በደመቀ ሁኔታ  ተካሂዶ  በስኬትና በሰላም ተጠናቋል።

ከስምንት ኣመታት በሁዋላ የ አዲስ አበባ ጎዳናዎች  ነፃነትንና ፍትህን በናፈቁ ሰልፈኞች ተጥለቅልቀዋል-ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት።
 ሰማያዊ ፓርቲ  በጠራው ሰልፍ ላይ ለመገኘት  በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ግንፍሌ ወደሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት ያመሩት ገና ከማለዳ አንስቶ ነበር።
ረፋዱ ላይ  የሰው ጎርፍ ከየ አቅጣጫው  ወደ ጥሪው ቦታ በመትመም  እንደረጋ ውሀ ቆመ። ሰዓቱ ሲደርስ  ጎርፉ በአራት ኪሎና በቸርችል ጎዳና በማድረግ ቴዎድሮስ አደባባይን አካልሎ ቁልቁል ወደ ኢትየ- ኩባ አደባባይ ፈሰሰ።
በርካታ ሙስሊም ወጣቶችም ከመርካቶና ከተለያዩ አካባቢዎች መፈክር እያሰሙ በመምጣት ሰልፉን ተቀላቀሉ።
ገዥው ፓርቲ  በትናንትናው ዕለት  ከኮንዶሚኒየም ቤት ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡን  በየቀበሌዎች አማካይነት  ማስጠንቀቂያ በታከለበት  ማሣሰቢያ  -ለዛሬ ስብሰባ  መጥራቱ ይታወሳል።
ይሁንና  እንደ ኢሳት ወኪሎች መረጃ፤ ህብረተሰቡ ማልዶ ይተም የነበረው ወደሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ እንጂ ወደ ቀበሌዎች አልነበረም።
ሰልፈኞቹ   ሲያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል ፦”ጭቆና ይጥፋ!ፍትህና ነፃነት እንሻለን!፣ እኛ ኢትዮጵያውያን አንለያይም!የህሊና እስረኞች ይፈቱ! ዜጎችን ከይዞታቸው ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ነው!መንግስት በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አጥብቀን እንቃወማለን! እና ዜጎች በፍርሀት የሞኖሩበት ዘመን ያብቃ!” የሚሉት ይገኙበታል።
እንዲሁም “ መማር ያስከብራል፣አገርን ያኮራል! ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ” የተሰኙት  ህዝባዊ ዘፈኖች በሰልፉ  ጎልተው ከተስተጋቡት  ዜማዎች ጥቂቶቹ ናቸው። 
በሰልፉ ላይ ንግግር ካደረጉት  ተጋባዦች መካከል ታዋቂው የህግ ባለሙያ ዶክተር ያዕቆብ ሀይለማርያም፦ አንድ ህዝብ  የሚገባውን መንግስት ነው የሚያገኘው በማለት -የመንግስትን ሁኔታ የሚወስነው የህዝቡ ጥንካሬና  ድክመት  እንደሆነ ጠቁመዋል።
ዶክተር ያዕቆብ በዚሁ ንግግራቸው ፦” በርከክ በርከክ ስል ፈሪ መሰልኳቸው፤ከሰው መፈጠሬን ማን በነገራቸው።” የሚለውን አገርኛ ግጥም በመጥቀስ-ትዕግስትና አርቆ ማሰብ ከፍርሀት መቆጠር እንደሌለበት የሚጠቁም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከዚህም በላይ ወጣቱ ትውልድ የ አባቶቹን እምነትና አደራ እንዲጠብቅ  አደራዊ መልእክት አስተላልፈዋል- ዶክተር ያዕቆብ ሀይለማርያም።
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የቤንሻንጉል ጉሙዝ  ብሔራዊ ክልል ተፈናቃዮችን  የወከሉት ተጋባዥ  እንግዳ ሲሆኑ፤ በ እርሳቸውና በወገኖቻቸው ላይ የደረሱባቸውን በደሎች  ለሰልፈኛው አሰምተዋል።
ሌላው በሰልፉ ተጋባዥ ተናጋሪ የነበሩት  የህሊና እስረኛዋ የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ አባት ናቸው።
አቶ ዓለሙ በንግግራቸው በግፍ ከታሰረችውና  በህመም እየተሰቃየች ከምትገኘው  ልጃቸው በበለጠ መልኩ ስለ ሌሎች የህሊና እስረኞች ጉዳይ በማውሳት ትኩረት ማድረጋቸው የብዙዎችን  ልብ የነካ ነበር።
የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው እስር ቤት የተወረወሩት የሙስሊም መሪዎች ሊፈቱ እንደሚገባ -የርዕዮት አባት  በዚሁ ንግግራቸው ተማጽነዋል።
 በሰልፉ  ሌላው ተናጋሪ የሆኑት የሙስሊሙ ህብረተሰብ  ተወካይ በበኩላቸው   ያለ አግባብ የታሰሩት የህሊና እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ  በ አጽንኦት ጠይቀዋል።
በስተመጨረሻ ንግግር ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ናቸው።
ኢንጂነር ይልቃል  ባደረጉት  በዚሁ ንግግር ጥያቄዎቻችን እስካልተመለሱ ድረስ  ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አቶ ይልቃል አክለውም ለውጥና ነፃነት የሚሻው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በድርጅት  ታቅፎ መታገል እንዳለበት አስምረውበታል።
እንደ ዘጋቢዎቻችን ሪፖርት የዚህ ታሪካዊ ሰልፍ አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ወጣቶችና ሴቶች  ናቸው።

በ አመዛኙ በወጣቶችና በሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ ከስምንት ዓመታት በሁዋላ  የጠራው ይህ ሰልፍ በብዙዎች  እንደተጠበቀው እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ተከናውኗል።
ህብረተሰቡ በሚከፍለው ግብር የሚተዳደሩት የመንግስት ብዙሀን መገናኛዎች-  በቀጥታ ሊያስተላልፉት ስለሚገባው ስለዚህ አስደማሚ ሰልፍ በቀትር የዜና እወጃ ሰ ኣታቸው  ምንም አላሉም።
ኢቲቪ፦ስለሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን በምሽት የዜና ክፍለ ጌዜያችን እናቀርባለን” በማለት ነው ያለፈው።
(ኢሳት)ሰማያዊ ፓርቲ በዛሬው ዕለት የጠራው ሰልፍ እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዶ በስኬትና በሰላም ተጠናቋል።

ከስምንት ኣመታት በሁዋላ የ አዲስ አበባ ጎዳናዎች ነፃነትንና ፍትህን በናፈቁ ሰልፈኞች ተጥለቅልቀዋል-ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት።
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ ለመገኘት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ግንፍሌ ወደሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት ያመሩት ገና ከማለዳ አንስቶ ነበር።

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊው ሰልፍ - 3 በዘር አንለያይም!!!

ሰላማዊ ሰልፉን በርካቶች እየተቀላቀሉት ጉዞው ቀጥሏል፡፡ አቤ ቶክቻው!!

945572_464808363610792_1068741911_n ሰላማዊ ሰልፉን በርካቶች እየተቀላቀሉት ጉዞው ቀጥሏል፡፡
መንግስታችን ይህንን ሰልፍ ዕውቅና የሰጠው ሰማያዊዎቹ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ እንደዛቱት ያደርጉትና አልተኩስ ነገር እንግዳ አለ አላስር ነገር ስንቱን አስሬ ብሎ ሰግቶ መሆኑ ይጠረጠራል፡፡
የሆነ ሆኖ ዛሬ በመንግስት ዕውቅና ያገኘ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊው ሰልፍ - 2 ዛሬ በአዲስ አበባ መማር ያስከብራል

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊው ሰልፍ ዛሬ በአዲስ አበባ