Sunday, 2 June 2013

የፍርሀት ጭጋግን የገፈፈው ታሪካዊ ሰልፍ (ልዩ ጥንቅር)

የፍርሀት ጭጋግን የገፈፈው ታሪካዊ ሰልፍ
                                          (ልዩ ጥንቅር)
(ኢሳት)ሰማያዊ ፓርቲ  በዛሬው ዕለት የጠራው ሰልፍ እጅግ በደመቀ ሁኔታ  ተካሂዶ  በስኬትና በሰላም ተጠናቋል።

ከስምንት ኣመታት በሁዋላ የ አዲስ አበባ ጎዳናዎች  ነፃነትንና ፍትህን በናፈቁ ሰልፈኞች ተጥለቅልቀዋል-ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት።
 ሰማያዊ ፓርቲ  በጠራው ሰልፍ ላይ ለመገኘት  በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ግንፍሌ ወደሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት ያመሩት ገና ከማለዳ አንስቶ ነበር።
ረፋዱ ላይ  የሰው ጎርፍ ከየ አቅጣጫው  ወደ ጥሪው ቦታ በመትመም  እንደረጋ ውሀ ቆመ። ሰዓቱ ሲደርስ  ጎርፉ በአራት ኪሎና በቸርችል ጎዳና በማድረግ ቴዎድሮስ አደባባይን አካልሎ ቁልቁል ወደ ኢትየ- ኩባ አደባባይ ፈሰሰ።
በርካታ ሙስሊም ወጣቶችም ከመርካቶና ከተለያዩ አካባቢዎች መፈክር እያሰሙ በመምጣት ሰልፉን ተቀላቀሉ።
ገዥው ፓርቲ  በትናንትናው ዕለት  ከኮንዶሚኒየም ቤት ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡን  በየቀበሌዎች አማካይነት  ማስጠንቀቂያ በታከለበት  ማሣሰቢያ  -ለዛሬ ስብሰባ  መጥራቱ ይታወሳል።
ይሁንና  እንደ ኢሳት ወኪሎች መረጃ፤ ህብረተሰቡ ማልዶ ይተም የነበረው ወደሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ እንጂ ወደ ቀበሌዎች አልነበረም።
ሰልፈኞቹ   ሲያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል ፦”ጭቆና ይጥፋ!ፍትህና ነፃነት እንሻለን!፣ እኛ ኢትዮጵያውያን አንለያይም!የህሊና እስረኞች ይፈቱ! ዜጎችን ከይዞታቸው ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ነው!መንግስት በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አጥብቀን እንቃወማለን! እና ዜጎች በፍርሀት የሞኖሩበት ዘመን ያብቃ!” የሚሉት ይገኙበታል።
እንዲሁም “ መማር ያስከብራል፣አገርን ያኮራል! ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ” የተሰኙት  ህዝባዊ ዘፈኖች በሰልፉ  ጎልተው ከተስተጋቡት  ዜማዎች ጥቂቶቹ ናቸው። 
በሰልፉ ላይ ንግግር ካደረጉት  ተጋባዦች መካከል ታዋቂው የህግ ባለሙያ ዶክተር ያዕቆብ ሀይለማርያም፦ አንድ ህዝብ  የሚገባውን መንግስት ነው የሚያገኘው በማለት -የመንግስትን ሁኔታ የሚወስነው የህዝቡ ጥንካሬና  ድክመት  እንደሆነ ጠቁመዋል።
ዶክተር ያዕቆብ በዚሁ ንግግራቸው ፦” በርከክ በርከክ ስል ፈሪ መሰልኳቸው፤ከሰው መፈጠሬን ማን በነገራቸው።” የሚለውን አገርኛ ግጥም በመጥቀስ-ትዕግስትና አርቆ ማሰብ ከፍርሀት መቆጠር እንደሌለበት የሚጠቁም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከዚህም በላይ ወጣቱ ትውልድ የ አባቶቹን እምነትና አደራ እንዲጠብቅ  አደራዊ መልእክት አስተላልፈዋል- ዶክተር ያዕቆብ ሀይለማርያም።
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የቤንሻንጉል ጉሙዝ  ብሔራዊ ክልል ተፈናቃዮችን  የወከሉት ተጋባዥ  እንግዳ ሲሆኑ፤ በ እርሳቸውና በወገኖቻቸው ላይ የደረሱባቸውን በደሎች  ለሰልፈኛው አሰምተዋል።
ሌላው በሰልፉ ተጋባዥ ተናጋሪ የነበሩት  የህሊና እስረኛዋ የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ አባት ናቸው።
አቶ ዓለሙ በንግግራቸው በግፍ ከታሰረችውና  በህመም እየተሰቃየች ከምትገኘው  ልጃቸው በበለጠ መልኩ ስለ ሌሎች የህሊና እስረኞች ጉዳይ በማውሳት ትኩረት ማድረጋቸው የብዙዎችን  ልብ የነካ ነበር።
የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው እስር ቤት የተወረወሩት የሙስሊም መሪዎች ሊፈቱ እንደሚገባ -የርዕዮት አባት  በዚሁ ንግግራቸው ተማጽነዋል።
 በሰልፉ  ሌላው ተናጋሪ የሆኑት የሙስሊሙ ህብረተሰብ  ተወካይ በበኩላቸው   ያለ አግባብ የታሰሩት የህሊና እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ  በ አጽንኦት ጠይቀዋል።
በስተመጨረሻ ንግግር ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ናቸው።
ኢንጂነር ይልቃል  ባደረጉት  በዚሁ ንግግር ጥያቄዎቻችን እስካልተመለሱ ድረስ  ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አቶ ይልቃል አክለውም ለውጥና ነፃነት የሚሻው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በድርጅት  ታቅፎ መታገል እንዳለበት አስምረውበታል።
እንደ ዘጋቢዎቻችን ሪፖርት የዚህ ታሪካዊ ሰልፍ አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ወጣቶችና ሴቶች  ናቸው።

በ አመዛኙ በወጣቶችና በሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ ከስምንት ዓመታት በሁዋላ  የጠራው ይህ ሰልፍ በብዙዎች  እንደተጠበቀው እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ተከናውኗል።
ህብረተሰቡ በሚከፍለው ግብር የሚተዳደሩት የመንግስት ብዙሀን መገናኛዎች-  በቀጥታ ሊያስተላልፉት ስለሚገባው ስለዚህ አስደማሚ ሰልፍ በቀትር የዜና እወጃ ሰ ኣታቸው  ምንም አላሉም።
ኢቲቪ፦ስለሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን በምሽት የዜና ክፍለ ጌዜያችን እናቀርባለን” በማለት ነው ያለፈው።

No comments:

Post a Comment