የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 5ኛ ፓትሪያርክ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ በኋላ፤ ቤተ
ክርስቲያኒቱ ያለ ፓትሪያርክ ላለፉት ስድስት ወራት ቆይታለች። በዛሬው እለት ግን ምርጫው ተጠናቆ አቡነ ማትያስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛ ፓትሪያርክ መሆናቸው ተገልጿል።
በተባለው የምርጫ ቆጠራ መሰረት፤ 806 መራጮች ከጳጳሳት፣ ከገዳማት፣ ከአብያተ ቤተ ክርስቲያናት ተመዝግበው
የነበረ ሲሆን፤ በምርጫው ውጤት መሰረት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – 39 ድምፅ፤ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – 70 ድምፅ፤
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – 98 ድምፅ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – 98 ድምፅ አግኝተዋል።
ሆኖም ብፁዕ አቡነ ማትያስ –
በ500 ድምፅ፤ ከሌሎቹ የላቀ ውጤት በማግኘት የተመረጡ መሆናቸው ተገልጿል።
ከ806 መራጮች ውስጥ አንድ የድምፅ መስጫ ወረቀት፤ ምርጫ ሳይደረግበት ባዶውን ስለተገኘ፤ ከቆጠራው ውጪ ሆኗል። ፡
ተመራጩ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስም ከምርጫው ሂደት በኋላ፤ የምርጫውን ውጤት እና ሲመቱን የሚቀበሉ
መሆናቸውን፤ እንዲህ በማለት አጭር ንግግር አድርገዋል። ‹‹ከእግዚአብሔርና ከሕዝበ ክርስቲያኑ የተሰጠኝን አደራ
ለመወጣት ከብፁዓን አባቶች፣ ካህናትና ከምእመናን ጋራ አብረን ስንለምንሠራ ሥራው የቀለለ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፤››
ብለዋል፡፡
እሁድ በዓለ ሲመቱ ከተፈጸመ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ተመልክቷል፡፡
ለምርጫው በአጠቃላይ ብር 3,650,000 ወጪ መደረጉን የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ተናግረዋል፡፡
አስመራጭ ኮሚቴው አራት ንኡሳን ክፍሎች ነበሩት – የመራጮች ምዝገባና ቁጥጥር፤ የሕዝብ ግንኙነት ንኡስ ክፍል፤ የሎጅስትክ ንኡስ ክፍል፤ የሒሳብና በጀት ንኡስ ክፍል ነበሩ።፡
ከግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተሳተፉት መራጮች፡- ብፁዕ አቡነ ጳኩሚስ፣ ብፁዕ አቡነ ራፋኤል፣ ብፁዕ
አቡነ ቢነም፣ ብፁዕ አቡነ ቢሾይ፣ ብፁዕ አቡነ ሂድራ ሲኾን በታዛቢነት የተወከሉት ካሚል ሚሸል ናቸው፡፡ የኮፕት
ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ጣቢያ(ሲቲቪ) የምርጫ ውሎውን በቀጥታ ሥርጭት አስተላልፏል፤ ለበዓለ ሢመቱም
ተመሳሳይ ሽፋን እንደሚሰጥ ተገልጧል፡፡
ራሳቸውን ከምርጫው ሂደት አግልለው የቆዩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በምርጫው የቀትር በኋላ ውሎ ተገኝተዋል፡፡
በሌላ ማስታወሻ:
እ.ኢ.አ በ1993 ዓ.ም. ምኒሊክ መጽሄት ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸው ነበር። በቃለ ምልልሱ መጨረሻ ላይ
“ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስተላልፉት መልእክት ካለ?” የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸው ሲመልሱ እንዲህ ብለው ነበር።
አቡነ ማቲያስ፡- እኔ በእውነቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የማስተላልፈው መልዕክት ጥንታዊ ፤ ታሪካዊ እና መሰረታዊ የሆነው ታሪካችንን መጠበቅ አለብን ፡፡ ሰው ኃላፊ ነው ፤ በስልጣን ላይ የሚወጣ ሰው ለዘላለም አይኖርም ፤ ታሪክ ግን ዘላለማዊ ነው ፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰላም ሀገር የአንድነት የሕብረት ሀገር መሆን ይኖርባታል፡፡ እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ሁሉ ኢትዮጵያም አንዲት ናት ብለን ነው እኛ የምናምነው ፡፡ ስለዚህ ስለ አንድነቱ እና ስለህብረቱ ማሰብ አለበት ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ሁሉ ነገር ሃላፊ ነው ፡፡ ነገር ግን ታሪካችን የሚቆይና የነበረ ስለሆነ ታሪካችንን መጠበቅ ይገባናል፡፡ ተባብረን ተስማምተን ተፈቃቅረን ተረዳድተን እገሌ እገሌ ሳንባባል በቋንቋ ፤ በጎሳ ፤ በወንዝ ፤ በሸንተረር ሳንለያይ ህብረታችንን ጠብቀን መኖር አለብን፡፡ የፖለቲካ ጉዳይ እንደሆነ ተለዋዋጭ ነው፡፡ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ የሚካሄድ ነገር ነው፡፡ ያለውን ችግር ተደጋግፈን አንድ ላይ ሆነን ነው እንጂ ልናስወግድ የምንችለው በጎሳና በቋንቋ ተለያይተን ምንም የምናስወግደው ችግር አይኖርም፡፡ ተባብረን ችግራችንን ፤ ርሀቡን ፤ ድንቁርናውን በሽታውን ጦርነቱን ቸነፈሩን የምናስወግድበትን መንገድ ነው መፍጠር ያለብን ፡፡ በድህነታችን ላይ እርስ በእርሳችን ስንጣላ ተጨማሪ አጥፊ የሆነ ነገር ነው የምንገዛው ፡፡ ልጆቻችን መጥፎ ነገር እንዳይማሩ ፤ መለያየት እንዳይወርሱ ፤ ለእነርሱ መልካም የሆነውን ነገር እንድናወርስ ድሮ አባቶቻችን ያቆዩልንን እንድናስረክባቸው አደራ እላለሁ ፡፡ ሀገራችን አንድነትና ሰላም የሚመጣበት ጊዜ ይኖራል፡፡

No comments:
Post a Comment