Thursday 15 August 2013

የሃዘን እንጉርጉሮ … ለግብፅ አቤ ቶክቻው!!!

2013814143731829665_8
ግብጽ ሆይ እንዴት አለሽ አልልሽም ከቶ… ነገርሽን እያየሁ ዜና ላይ ተሰጥቶ… እኔ ልሰጣልሽ ብዬም ባልልሽ… ሀዘንሽን አዘንኩት ተሰማኝ ልቅሶሽ… እሳት ሲቀጣጠል ሰው ሲጠበስ ለጉድ… ግንቡ ቤተ አምልኮሽ ሲቀየር ወደ አመድ…

ምን ርግማን ይሆን ምንስ ያገር ጣጣ… በሌሎች ሲፈራ ዛሬ ባንቺ መጣ፤
ያኔ…

እኛ በወር እቁብ እንኳን መጣል ሲቸግረን፤ በአስራ ስምት ቀናት አምባ ገነን ጥለሽ እንዳላስቀናሽን፣ ከዛም በድጋሚ ጥቂትም ሳትቆዬ ህዝብሽ ግራ እና ቀኝ ሁለት ወገን ተሰልፎ… አንዱ ወታደሩን አንዱ ህጉን አቅፎ ግልበጣ አይሉት ልወጣ ግራ የሚያጋባ በእውኑ፣ ፕረዘዳንት ሲወርድ እንደዋዛ ከዙፋኑ፣ “የማናት ቀልባጣ የማን ተሸቀርቃሪ እንደ አልባሶቿ ምትለዋውጥ መሪ” ብለን ስንደነቅ በሰራሽው ስራ፤ እሱን ተከተሎ መጣብሽ መከራ…

ግብፅ ሆይ አሳዘንሽኝ አንጀቴን በላሽው ፉከራሽ ተሻለኝ በእኛው ላይ የዛትሽው… “አንዲት ጠብታ ውሃ ትነኩና ያልሽው… ”
ግብፅ ሆይ አሳዘንሽኝ…ሰላምሽ ናፈቀኝ፤ እሳት ሲነድብሽ ደም ጎርፍ ሲፈስብሽ የሚገድበ ጠፍቶ ሺ ሰው ሲሞትብሽ ሲገርመን የመቶ… የገዳቢ ያለህ ስትዬ ታየሽኝ ግብፅ ሆይ አሳዘንሽኝ!

No comments:

Post a Comment