Sunday 30 December 2012

Ethiopia: TPLF Inc. as a ‘silent killer’ By Aklog Birara, PhD

(indepthafrica) Aklog Birara, PhD –

Have you ever wondered, as I have, why Ethiopia and the Ethiopian people are caught in a vicious cycle of disillusionment, dispossession and disempowerment? Have you pondered, as I have, the simple truth that the vast majority of the Ethiopian people have less say and thus less power over their political and economic affairs in their own country compared to a few ethnic elites and foreign investors such as Saudi Star and Karuturi? Have reflected on the implications for this and the coming generation of the virtual control of the pillars of the Ethiopian economy by foreign entities, and a few ethnic elites allied to TPLF Inc.? 

ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ያደረጉት ንግግር ቪድዮ ``ጊዜው የወጣቶች ነው``

ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ያደረጉት ንግግር ቪድዮ ``ጊዜው የወጣቶች ነው``

የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው ሰነዱን ምዕራባውያን፣ የስለላና የመብት ተቋማት ተርጉመውታል

insa ethiopia
አዲሱ ቴሌ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ኢንሳ” በሚል ርዕስ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት የታላላቅ አገር የስለላ ተቋማት፣ ለጉዳዩ አግባብ ያላቸው መምሪያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትኩረት መሳቡ ታወቀ። ሪፖርቱን አገራቱ በራሳቸው ቋንቋ በመተርጎም የህወሃት/ኢህአዴግን የስለላ መረብ ከተለያየ አቅጣጫ እየመረመሩት ነው።

ሰንበት ምሳ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው!? አቤ ቶክቻው


ዛሬም “ለአዲስ ታይምስ” (ፍትህ) አዲሳባ ተልካ የነበረችቱን ወግ ለሰንበት ምሳ እዚህ ተለጥፋለች፤ ይቋደሱልኝ እውነት ግን የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው!?
ሰላም ወዳጄ እንዴት ሰነበቱ…
የመንገድ ቁፋሮው ነገር እንዴት አድርጎታል? በአሁኑ ሰዓት አዲሳባ ውስጥ ትራንስፖርት ከማግኘት “ፖርት” ማግኘት ይቀላል ሲሉ የሚያሽሟጥጡ ሰዎች መበራከታቸውን እየሰማን ነው።

ኧረ “ፖርት” ብል ጊዜ ምን ትዝ አለኝ፤ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ አዲስ ወደብ ግንባታ እያደረገችላት መሆኑን ሰምተን ደስታችን ጨምሯል። እሰይ እንዲህ ነው እንጂ ልግስና! በዚሁ አይነት ፤ ሌሎቹ ጎረቤቶቻችንም እንዳይቀየሙ ብንገነባላቸው ምን አለበት…? ለነ ሱዳን ፤ለነ ሱማሌ ኤርትራዬ እና ኬኒያስ ቢሆኑ ካለኛ ማን አላቸው…? እና ይታሰብበት… “ያስቀኛል ገንፎ ከራቴ ላይ ተርፎ” አሉ አበው!
እና ታድያ የትራንስፖርቱ ነገር እንዴት አደርጎታል? እንደውም እንደሰማሁት ከሆነማ “ፒያሳ መሀሙድጋ ጠብቂኝ” ከሚለው የታላቁ ወዳጃችን መሃመድ ሰልማን መፅሐፍ በኋላ “ቦሌ ፒኮክ ጋ ጠብቂኝ” “መርካቶ ምዕራብ ሆቴል ጋ ጠብቂኝ” የሚሉ ተደጋጋሚ የቀጠሮ ፅሁፎች ሲወጡ የነበረውን ያህል… አሁን በቅርቡ ከወዳጆቻችን እንደ አንዱ የሆነው በሀይሉ ገብረ እግዚአብሔር “የትም አትጠብቂኝ” ብሎ መፃፉን ሰምተናል።

Saturday 29 December 2012

Gen Samora Yenus is dying…

The Horn Times Newsletter, 28 December 2012
by Getahune Bekele

The unschooled and uncultured top war criminal Gen Samora is dying…

A poor peasant and a primary school dropout, who was described by senior political commentator as cold bloodedThe unschooled and uncultured top war criminal Gen Samora is dying murderer with thinking and reasoning capacity of a dinosaur, Gen Samora is dying…
According to a sensitive document leaked to the Horn Times from Bella military referral hospital in Addis Ababa, the frail TPLF army chief-of-staff and top November criminal, the dastardly Gen Samora Yenus Mohamedfereja, has less than a year to live.

በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ

ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

Ethiopians forced to buy magazine glorifying Meles

ESAT News The ruling Ethiopian People Revolutionary Democratic Party (EPRDF) has reportedly forced ordinary citizens to buy a special edition of a party organ, Addis Raey, for a whopping 100 birr. The magazine devoted cover to cover homage to the late Prime Minister Meles Zenawi, whom it tried to characterize as a patriotic visionary leader who was committed to the development, justice and democracy.

``ግንቦት 7 ሃይል የኛ አካል አይደለም ግን አላማቸውን እደግፋለሁ`` ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

መንግሰት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ



ኢሳት ዜና:-አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና
ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡
ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት
አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገር
ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም
የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች
ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
“የሃይማኖት አክራሪነት አንድ ስጋት ነው፡፡ከዚያ አልፎ ሽብርተኝነት አለ፡፡ሕዝቡ በስነልቦና እንዲሸበር
ፍርሃት፣ጭንቀት፣አለመተማመን እንዲሰፋ፣ ወጣቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ እንዳይገባ የሚያደርጉ
ኃይሎች አሉ ” ያሉት ብ/ጄኔራሉ  ”ይህን ለመቆጣጠር ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የመከላከያ አቅም መገንባት
ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
 
ብ/ጄኔራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው መረር ብለው “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን
የመቆጣጠር አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁ ይህ ነው፡፡ለኀብረተሰቡ የሰላምና የልማት አጀንዳ እንቅፋት ሊሆኑ
የሚችሉ የመቆጣጠር ብቃት አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡
 
“ስርዓት ያልተበጀለት ኢንተርኔት ጉዳቱ ሰፊ ነው” የሚሉት ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን “ሕገመንግስቱን ም ሆነ የሕዝቡን ሰላም
የሚጻረሩ እንቅስቃሴዎች ሊፈቀድላቸው አይገባም” ብሎ አስቀምጧል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጽያ መንግስት በኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች ላይ አፈና በማድረግ የዜጎችን ኀሳብን በነጻ የመግለጽ
ነጻነት የሚጻረሩ ሕገወጥ እርምጃዎችን ይወስዳል በሚል የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ክሶች፤ መሰረተ ቢስ ናቸው በሚል
ሲያጣጥል መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

Thursday 27 December 2012

ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል “[ሙስና] የስርዓቱ አደጋ ነው” ርምጃ ግን የለም!!

corruption fight
ሙስና በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ኢህአዴግ አይክድም። ኢህአዴግ ባለስልጣኖቹ በሙስና ስለመዘፈቃቸው ማመኑን የገለጸው “የመንግስት ሌቦች አስቸገሩኝ” በሚል ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ “በሙስና የተለከፉ ዋጋቸውን ያገኛሉ” ሲሉ ስልጣን በያዙ ማግስት መዛታቸውን የሚያስታውሱ በስተመጨረሻ “ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል” የሚል ድምዳሜ ላይ ነው።
“ትልቅ ጫካ ሰርታችሁ የኛንም የናንተንም ሌቦች መደበቅ በመቻላችሁ ሁሉንም መመንጠር ስላልቻልን እየተተራመስን ነው” በማለት ጣታቸውን ወደ ነጋዴው ህብረተሰብ በመቀሰር ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአገሪቱ ያለውን ሙስና አስከፊነት በገለጹበት መድረክ “ስልጣን የመክበሪያ ብቸኛው መንገድ በሆነበት አገር ዘላቂ ሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው። በኪራይ ሰብሳቢነት እንደ መንግስትም፣ እንደ ባለሃብትም መቀጠል አንችልም። እንደ ሶማሌ ነው የምንሆነው። እንተራመሳለን። በድጎማ እየኖርን ሙስናው ከከፋ አገር የሌለው ባይተዋር እንሆናለን” ሲሉ የጉዳዩን አሳሳቢነትና በኢህአዴግ ስሌት ሙስናው የሚያስከትለውን የመጨረሻ ጣጣ አመላክተው ነበር።

Civilized people uncivilized regime: how did it happen?

by Teshome Debalke
Everybody is wondering how did such civilized people as Ethiopians ended up under the rule of uncivilized regime like Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) “Woyane”?
Before I go on exploring about how the uncivilized regime remained in power it is appropriate to explain what civilized society means, so that the ‘uncivilized’ understand not to divert us from the main question.

Ethiopia: Wild celebrations in South Africa

The Horn Times Breaking News
by Getahune Bekele, Johannesburg

Wild celebrations as news of the formation of a crack guerrilla group reach South Africa!

“Tekebresh yenorshiw babatochachin dem,”
Enat Ethiopia yedeferesh yewdem,”
The patriotic song made famous by the incomparable Ethiopian singer Shambel Belayneh was on everyone’s lips on
GPF, Ginbot 7 popular Force fighters on the move.
GPF, Ginbot 7 popular Force fighters on the move…
Saturday morning 21 December 2012, when the Horn Times visited the bustling GP street in central Johannesburg where Ethiopian refugees usually gather in large numbers.
“President Jacob Zuma, it is time to return the favor, help our freedom fighters…” an excited Ethiopian refugee shouted at a passing police van while his friendswhistle and scream “freedom! Freedom!”
“The day 90 million Ethiopians patiently waited for has finally arrived.

መምህራን ተማሪዎችን ፈርመው እንዲረከቡ የሚያደርግ መመሪያ ተዘጋጀ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
 
ኢሳት ዜና:-ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች መጨመራቸውን ተከትሎ ፣ በአማራ ክልል የሚያስተምሩ መምህራን ተማሪዎችን በሰሚስተሩ መጀመሪያ ላይ ቆጥረው ተረክበው፣ በሰሚስተሩ መጨረሻ ላይ ቆጥረው እንዲያስረክቡ የሚያደርግ መመሪያ ወጥቶ ለውይይት ቢቀርብም፣ መምህራን ግን አጥብቀው ተቃውመውታል።

በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ መምህሩ ቆጥሮ ከተረከባቸው ተማሪዎች መካከል ከ2 ተኩል በመቶ በላይ ተማሪዎች ቢያቋርጡ፣ መምህሩ በጥፋተኝነት የሚመዘገብ ሲሆን፣ አስፈላጊውን እድገትም አያገኝም።
በክልሉ የሚማሩ ተማሪዎች በብዛት ወደ አረብ አገራት በስደት መልክ እንደሚሄዱ መዘገባችንን ተከትሎ እንዲህ አይነት መመሪያ መተላላፉ ታውቋል።

መንግስት በየጊዜው የሚያወጣቸው መመሪያዎች መምህራን ተስፋ እንዲቆርጡ እያደረጋቸው መሆኑን መምህሩ ተናግረዋል።

Ginbot 7 announces formation of armed wing

Dec. 25 (ESAT News)—A group called Ginbot 7 Popular Force has announced the launching of armed resistance against the TPLF-led regime that it characterized as oppressive and tyrannical.
The spokesperson of the group told ESAT that it has laid the foundation to collaborate with other armed groups such as the Tigray People’s Democratic Movement, Ethiopian People’s Patriotic Force, Gambella People Liberation Movement, Benishangul Liberation Movement.

Two Arena Tigray members arrested

ESAT News (Dec. 25)–Two members of Arena Tigray, a party that aspires to liberate Tigrians from the grip of the TPLF, have been detained in Mekele while distributing the party’s publication. Arena said the duo remain in custody despite informing the police that they were the party’s members.

Arena’s Mekele branch representative Sultan Hihshe told ESAT that Ayalew Beyene and Tekalign Tadesse were detained under the pretext that they did not carry ID cards identifying them as members of a legally registered political party.

ያለው አማራጭ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ብቻ ነው ሲሉ አንጋፋው የሕውሀት ታጋይ አቶ ስብሐት ነጋ ገለጹ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሐት ነጋ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ከተማ ለንባብ ለበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ የመለስ ራዕይ የሚባለው ነገር ትክክል እንደማይመስላቸውና ያለው የጋራ ራዕይ መሆኑን ገልጠዋል::
ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሾም ያስፈለገው ክፍት የአመራር ቦታ ስለነበር እንደሆነ ያወሱት አቶ ስብሐት ነጋ: መደረግ የነበረበት ነገር መከናወኑን አስረድተዋል::
ይህ እርምጃ ሕገ-መንግስቱን ይጥሳል በሚል የሚነሳውን ተቃውሞ በተመለከተ እኔ የማውቀው ነገር የለም ያሉት አቶ ስብሐት ነጋ ሕገ-መንግስቱ ከተጣሰም ያለው አማራጭ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ወይንም ሌላ አማራጭ መፈለግ እንጂ አዲሱ አደረጃጀት መቀጠል አለበት ብለዋል::

 ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕውሀት)ን ከ1971 እስከ1981 በመሪነት ያገለገሉትና አሁን ይፋዊ የሆነ የፓርቲ አመራር ስፍራ የሌላቸው አቶ ስብሐት ነጋ በሐገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኗቸው የጎላ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል:: በተለይ የአቶ በረከት ሥምዖን ሚና ከቀነሰ ወዲህ ይበልጥ እያንሰራሩ መሆናቸው የተገለጸው አቶ ስብሐት ነጋ በዚህ ረገድ ለተነሳባቸው ጥያቄ እኔ ተራ አባል ነኝ ያለ ሃላፊነቴ ምንም የምሰራው ነገር ያለም ብለዋል::
እኔ ሥርዓት ከጣስኩ ከግንቦት 7: ኦብነግ እና ኦነግ በምን እለያለሁ:: በማለት ጠይቀው ምንም ሚና የለኝም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል::
የአቶ መለስ ራዕይ በሚል የሚነሳውን በተመለከተም “በግለሰብ ብቻ የተቀመጠ ራዕይ ሳይሆን የሁላችንም ዕሴት የሆነ የጋራ ራዕይ ነው” በሚል ምላሽ ሰጥተዋል:: ሆኖም አቶ መለስ ወሳኝ ሰው እንደነበሩ በቃለ ምልልሱ አንስተዋል::

በድርጅቱ ውስጥ ክፍፍል ስለመፈጠሩ ለተነሳባቸው ጥያቄ “እስከአሁን በኢሕአዲግ ውስጥ ይሁን በአባል ድርጅቶቹ መከፋፈል የሚባል ነገር  ገጥሞ አያውቅም:: በዚህ ሂደት በተለያዩ መለኪያዎች ለኢሕአዲግ ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ተባረዋል ወይንም በራሳቸው ለቀው ወደ ሚመጥናቸው ድርጅት ሔደው ይወድቃሉ” ያሉት አቶ ስብሐት ነጋ “አሁን በኢሕአዲግ ውስጥ የሚታይ የሚሰማ የፖለቲካ ጥያቄ ያለ አይመስለኝም ብለዋል:: ካለም እንዳለፈው ጸጋ ነው:: በአፈጻጸም ዙሪያም ጥያቄዎች ሊኖሩ ይችላሉ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል::

Wednesday 26 December 2012

ሰብአዊ መብትና: መንግሥታዊ ግፊት በኢትዮጵያ (2012)

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም                                                                                                                     ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በዲሴምበር 2008 ላይ በኢትዮጵያ የ‹‹ለውጥ የሌሽ ዓመት›› በማለት እንጉርጉሮ መሰል መልእክት ጽፌ ነበር፡፡
2008 የ2007፤2006፤2005፤2004 ቅጂ ነበር… በየቀኑ ኢትዮጵያዊያን ሲነቁ ልክ እንደተሰበረ የሙዚቃ ሸክላ ባለፈው የሕይወት ስቃያቸው ድግግሞሽ መከራ ውስጥ በመዳከር ነበር የሚገኙት፡፡ እያንዳንዱ አዲስ ቀን ካለፈው የወረሰውን ይዞ ነበር የሚመጣው፡፡ ጫና፤ ማስፈራራት፤ ንቅዘት፤እስራት፤ ማጭበርበር… ጭካኔና የሰብአዊ መብት ገፈፋ… ከዚህ ክፉ ከሆነው የስቃይ፤ የጣረሞት ግርዶሽ፤ አዙሪት፤ የተስፋ እጦት፤ ውጣ ውረድ መከራ እንዴት እንደሚገላገሉ መንገዱን አያውቁትም፡፡ ስለዚህም ከዚህ መዓት ለመገላገል ያላቸው አንድ ተስፋ መጸለይ፤ መጸለይ፤ ደሞ መጸለይ ብቻ ነበር::

ENTC to convene its general assembly on Feb. 22 in Washington DC

The Ethiopian National Transitional Council (ENTC) announced that it will hold its mid-term general assembly in Washington DC from Feb. 22 – 24, 2013. The meeting will evaluate ENTC’s activities of the past six months and will make necessary adjustments, its news release said.
Representatives of ENTC chapters and local councils from several cities and countries around the world are expected to participate in the 3-day meeting that will be held inside its headquarters in Washington DC.

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ም/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ በፊታችን የካቲት (ፌብሪዋሪ) ወር ይከናወናል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት ላለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናዉን ቆይቷል። ከም/ቤቱ ምስረታ በኋላ የአካባቢ ምክር ቤቶችን (ቻፕተሮችን) በተለያዩ አገሮች በማቋቋም፤ ድርጅታዊ አቅምን በማጎልበት፤ የትግል ሂደት አቅጣጫን በመቀየስ፤ ከሌሎች ድርጅቶች ጋረ ትብብር በመፍጠርና እንዲሁም አቅሙንና የትኩረት አቅጣጫውን ኢትዮጵያ ውስጥ በማድረግ በርካታ ስራዎችን አከናውኗል። የም/ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ በዳላስ ቴክሳስ የምስረታ ስብሰባው ላይ በወሰነው መሰረት የስድስት ወራቱን የስራ እንቅስቃሴ ለመገምገምና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቀጣይ እቅዶችን ለመንደፍ በአሜሪካን ዋና ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ከፌብርዋሪ 22 እስከ 24 ቀን 2013 እኤአ ያካሂዳል። በተለያዩ ሀገሮችና ከተማዎች ቀደም ብለው የተቋቋሙና በመቋቋም ላይ ያሉ የአካባቢ ምክርቤቶች (ቻፕተሮች) ተወካዮች በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ይሳተፋሉ። ስብሰባውም በስድስት ወራቱ ውስጥ የታዩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመገምገም የሚቀጥሉት ስድስት ወራት አካሄድን በተመለከተ የተለያዩ የፖሊሲና የተግባር ውሳኔዎችን ያስተላልፋል። በስብሰባውም መዝጊያ ዕለት በፌብርዋሪ 24 ቀን 2013 (እኤአ) ህዝባዊ ስብሰባ በማዘጋጀት በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይና መወሰድ ስለሚገባቸው ፈጣን እርምጃዎች ህዝባዊ ውይይት ያደርጋል። በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ሁሉ እንዲገኙ እየጋበዝን ወደፊት ስለስብሰባው ቦታና ፕሮግራም ዝርዝር መረጃዎችን የምናወጣ መሆኑን እንገልጻለን።
የሽግግር ም/ቤቱ አመራር

Monday 24 December 2012

የሚያስቅና የሚያሳቅቅ የፍርድ ቤት ውሎ

 

ዕለቱ “በእነ ኤልያስ ክፍሌ የፍርድ መዝገብ” ምስክርነት ይሰጣል የተባለበት ዕለት ነበር። በዚህ መዝገብ ውብሸት ታዬ፣ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር፣ ሂሩት ክፍሌ እና ርዮት አለሙ ክስ ተመስርቶባቸዋል።
እነ ውብሸት ታዬ መጀመሪያ ሲታሰሩ በቴሌቪዥን የሰማነው “የቴሌ እና የመብራት ሃይል ተቋማትን ማፈራረስ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ መሞከር” የሚል ነበር። ከዛ እያደር እያደር አቃቤ ህግ በምን እንደከሰሳቸው ረሳው መሰለኝ፤ ለምስክርነት በሄድንበት ጊዜ የሰማነው አንድም ከመብራት ሃይልና ቴሌኮሚዩኒኬሽን ጋር የሚያያዝ ነገር አልነበረውም። አረ ልብ ብለን ካየነውማ ከህገ መንግስቱም ጋር የሚጋጭ ነገር አላየንበትም።  

ኢሳት በናይል ሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያሰራጨው ስርጭቱ ቢቋረጥም፣ ስርጭቱን በአሞስ ሳተላይት እያስተላለፈ ነው



ኢሳት ዜና:-ኢሳት ላለፉት ሶስት ወራት ስርጭቱን በ ናይልሳት ሲያሰራጭ ከቆየ በሁዋላ የኢትዮጵያ መንግስት ስርጭቱን ከማፈን አልፎ ባደረገው ከፍተኛ የሎቢንግ ዘመቻ የኢሳት ስርጭት እንዲቋረጥ አድርጓል።

በመላው አገሪቱ ኢሳት ቁጥር አንድ ተመራጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ በመሆን የሰፊውን ህዝብ የመረጃ ጥማት ለማርካት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ለገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ራስ ምታት ሆኖበት እንደነበር ኢሳት የኢትዮጵያ ወኪል ገልጿል።

ምንም እንኳ ኢሳት የናይል ሳት ስርጭቱ ቢቋረጥም፣ በአሞስ 5 የሚያካሂደው ስርጭቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ኢሳት በቅርቡ ተጨማሪ ቻናል ለማስተዋወቅ በዝግጅት ላይ ነው።

ኢሳት በናይል ሳት የሚያሰራጨው የራዲዮ ዝግጅቱ፣ አዲስ የጀመረው በአረብሳት የ ሚያስተላልፈው ራዲዮ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ኢሳት Amos 5 KU 17 Degrees East Downlink: 10961.200 V Symbol Rate 2.200 FEC: 1/2 እንደሚተላለፍ ለማስታወስ እንወዳለን።

PUBLIC FORUM: Carl Bernstein & Liev Schreiber on Eskinder Nega

Ethiopia 2012: Human Rights and Government Wrong by Prof. Alemayehu G Mariams

Another Groundhog Year



It was a repetition of 2007, 2006, 2005, 2004… Everyday millions of Ethiopians woke up only to find themselves trapped in a time loop where their lives replayed like a broken record. Each “new” day is the same as the one before it: Repression, intimidation, corruption, incarceration, deception, brutalization and human rights violation… They have no idea how to get out of this awful cycle of misery, agony, despair and tribulation. So, they pray and pray and pray and pray… for deliverance from Evil!


PM Hailemariam Desalegn expresses frustration to close confidants

Ethiopia’s new prime minister, Hailemariam Desalegn, has expressed frustration with the Tigrean People Liberation Front (TPLF) to a group of close friends he recently met. One long time friend of the prime minister (who wants to remain anonymous) told Ethiopian Review today that Hailemariam is finding it impossible to get cooperation from the TPLF members who are dominating the bureaucracy and military on a number of issues, most particularly making personnel decisions. TPLF officials also keep him in the dark on national security matters and he doesn’t get timely reports as a commander-in-chief.

Sunday 23 December 2012

Writers Honored for Commitment to Free Expression

(New York) - Forty-one writers from 19 countries have received 2012 Hellman/Hammett grants for their commitment to free expression and their courage in the face of persecution.
The award-winners have faced persecution for their work, generally by government authorities seeking to prevent them from publishing information and opinions.  Those honored include journalists, bloggers, essayists, novelists, poets, and playwrights. They also represent numerous other writers worldwide whose personal and professional lives are disrupted by repressive policies to control speech and publications.

Saturday 22 December 2012

General Tsadkan warns Ethiopian refugees against wagging armed insurrection

The Horn Times Newsletter 20 December 2012

by Getahune Bekele

The most pre-eminent among hordes of loathsome TPLF warlords, he became famous after threatening the entire Eritrean population with genocide during the 1998 – 2000 boarder war.
However, when he later turned his anger on the late despot Meles Zenawi for bringing the war to an abrupt end without his consent, and threatened him with a coup, the General lost his job as the army’s chief – of – staff.

HISTORIC SPEECH BY ABEBE GELAW

Parties accuse electoral board of squandering funds

ESAT News (Dec. 20)—Thirty-three political parties have urged the National Electoral Board not to waste public funds under the pretext of holding elections. The joint statement issued by the parties criticized the regime for squandering public resources to organize inconsequential elections.

They mentioned a recent forum held at the Executive Hotel in Adama which was aimed at discussing the forthcoming local elections .  The parties complained that the board ignored a petition they submitted demanding the electoral body to convene a discussion on the overall environment and constricted political space that has made it impossible for them to have a level playing field. They also accused the board of sidelining more serious issues and calling them for a meeting to discuss issues related only to gender and elections.

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በዋሺንግተን ዲሲ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ም/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ በፊታችን የካቲት (ፌብሪዋሪ) ወር ይከናወናል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት ላለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናዉን ቆይቷል። ከም/ቤቱ ምስረታ በኋላ የአካባቢ ምክር ቤቶችን (ቻፕተሮችን) በተለያዩ አገሮች በማቋቋም፤ ድርጅታዊ አቅምን በማጎልበት፤ የትግል ሂደት አቅጣጫን በመቀየስ፤ ከሌሎች ድርጅቶች ጋረ ትብብር በመፍጠርና እንዲሁም አቅሙንና የትኩረት አቅጣጫውን ኢትዮጵያ ውስጥ በማድረግ በርካታ ስራዎችን አከናውኗል። የም/ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ በዳላስ ቴክሳስ የምስረታ ስብሰባው ላይ በወሰነው መሰረት የስድስት ወራቱን የስራ እንቅስቃሴ ለመገምገምና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቀጣይ እቅዶችን ለመንደፍ በአሜሪካን ዋና ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ከፌብርዋሪ 22 እስከ 24 ቀን 2013 እኤአ ያካሂዳል። 

በተለያዩ ሀገሮችና ከተማዎች ቀደም ብለው የተቋቋሙና በመቋቋም ላይ ያሉ የአካባቢ ምክርቤቶች (ቻፕተሮች) ተወካዮች በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ይሳተፋሉ። ስብሰባውም በስድስት ወራቱ ውስጥ የታዩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመገምገም የሚቀጥሉት ስድስት ወራት አካሄድን በተመለከተ የተለያዩ የፖሊሲና የተግባር ውሳኔዎችን ያስተላልፋል። በስብሰባውም መዝጊያ ዕለት በፌብርዋሪ 24 ቀን 2013 (እኤአ) ህዝባዊ ስብሰባ በማዘጋጀት በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይና መወሰድ ስለሚገባቸው ፈጣን እርምጃዎች ህዝባዊ ውይይት ያደርጋል። በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ሁሉ እንዲገኙ እየጋበዝን ወደፊት ስለስብሰባው ቦታና ፕሮግራም ዝርዝር መረጃዎችን የምናወጣ መሆኑን እንገልጻለን።

የሽግግር ም/ቤቱ አመራር

ከሶማሊያውያን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን ተሰደዋል

ኦሮሞ፣ ኦጋዴን፣ አማራና ትግራይ በደረጃ ተቀምጠዋል
 
immigrants
የአራት ዓመት ማነጻጸሪያ የቀረበበትን የሪፖርቱ አንያንዳንዱ ክፍል ያስገርማል። የማነጻጸሪያው ማሳረጊያ አስደንጋጭ ነው። መረጃው በአሃዝ፣ በኩኔታ፣ በባህሪው ስደትን ይገልጻል። ትንታኔው በካርታ፣ በስደቱ መነሻና መድረሻ መካከል፣ እንዲሁም በስደት መዳረሻ ላይ የሚያጋጥመውን አፈና፣ ቶርቸር፣ አስገድዶ መደፈር፣ ስቃይ፣ የባህር ሲሳይ የሆኑ ወገኖችን ይጠቅሳል።

ESAT Tikuret Fezralizm Tamagn Beyene Part 2.

ESAT Ethiopia Breaking News 21 December 2012

DfID under fire for poor response to human rights concerns in Ethiopia

Aid officials accused of failing to fully investigate reports of abuse by Ethiopian authorities against ethnic groups 
  and guardian.co.uk,
 
MDG : Human rights abuses in Ethiopia : Mursi tribe, Mago National Park, Ethiopia
The Mursi tribe in Mago national park, Ethiopia, 2011. Photograph: Patricia White/Alamy
Britain's Department for International Development (DfID) is under fire for failing to adequately address allegations of human rights abuses in Ethiopia, a major recipient of UK aid.

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሳካ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ አካሄደ፣ “አለም አቀፍ ኮሚቴ” የሚባል እንቅሰቃሴ አለመኖሩን ገለጸ

ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጎጠኛው የወያኔው ስርዓት በአገራችንና በህዝባችን ላይ ሲያደርስ የነበረውና እያደረሰ ያለው ግፍ ለስልጣን በበቃበት መንገድ መውረድ አለበት ብሎ ጠብመንጃውን ካነሳና መፋለም ከጀመረ አመታትን አስቆጥሯል።

የትጥቅ ትግል መራርና ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ህይወት የሚጠይቅ ቢሆንም አያቶቻችን ያለምንም ዋጋ ውድ ህይወታቸውን ለአገርና ለህዝብ ፍቅር በመክፈል ያቆዩልንን የአርበኝነት አደራ ለመወጣት ከምንጊዜውም በበለጠ አጠናክረን የቀጠልንበት ደረጃ ላይ እንገኛለን ።

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ

GPF Pict 2
GPF_Logo-Small
ቀን ታህሳስ 11  2005

የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ “የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል” የሚል ስያሜ የሰጠነውን፣ በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና ዜጎች የተሞላውን ድርጅት መመሥረታችን በዛሬው እለት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እናበስራልን።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል፣ የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የዜጎች መብቶች፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና የማየትን ራዕይ የሰነቀ ድርጅት ነው።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ወያኔን በኃይል የማስወገድ፤ ሰላማዊና ዲሞክራሲ የሥልጣን ሽግግር በሃገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛዉም የፓለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ፣ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግሥታዊ የመከላከያ፣ የፓሊስና የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዖ የማድረግ ተልዕኮ ይዞ የተነሳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ ነው።
የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል ራዕይና ተልዕኮ የተቀዳው በቀጥታ ሕዝብ በህይወቱ በደሙ በስቃይና በመከራ ውድ መስዋዕትነት ከከፈለለት የ1997 ብሄራዊ ምርጫ ነው።

Thursday 20 December 2012

Eskinder Nega Fights Terrorism Charges in Court

Marthe Van Der Wolf (VOA) December 19, 2012

ADDIS ABABA — Ethiopian journalist Eskinder Nega appeared in court on Wednesday as the prosecution had to re-explain the charges against the prominent blogger. Eskinder also got the chance to defend himself before the court.
Eskinder made his court appearance with opposition leader Andualem Arage and two other opposition members. They are all imprisoned on terrorism charges as they were found guilty earlier this year of having links with the outlawed group Ginbot 7 and trying to start Arab Spring-type demonstrations in Ethiopia.
The blogger was sentenced to 18 years in prison and Andualem was given a life sentence.

የሽግግር ም/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ በፌብሪዋሪ ወር ይከናወናል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት ላለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናዉን ቆይቷል። ከም/ቤቱ ምስረታ በኋላ የአካባቢ ምክር ቤቶችን (ቻፕተሮችን) በተለያዩ አገሮች በማቋቋም፤ ድርጅታዊ አቅምን በማጎልበት፤ የትግል ሂደት አቅጣጫን በመቀየስ፤ ከሌሎች ድርጅቶች ጋረ ትብብር በመፍጠርና እንዲሁም አቅሙንና የትኩረት አቅጣጫውን ኢትዮጵያ ውስጥ በማድረግ በርካታ ስራዎችን አከናውኗል።

 የም/ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ በዳላስ ቴክሳስ የምስረታ ስብሰባው ላይ በወሰነው መሰረት የስድስት ወራቱን የስራ እንቅስቃሴ ለመገምገምና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቀጣይ እቅዶችን ለመንደፍ በአሜሪካን ዋና ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ከፌብርዋሪ 22 እስከ 24 ቀን 2013 እኤአ ያካሂዳል። በተለያዩ ሀገሮችና ከተማዎች ቀደም ብለው የተቋቋሙና በመቋቋም ላይ ያሉ የአካባቢ ምክርቤቶች (ቻፕተሮች) ተወካዮች በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ይሳተፋሉ። ስብሰባውም በስድስት ወራቱ ውስጥ የታዩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመገምገም የሚቀጥሉት ስድስት ወራት አካሄድን በተመለከተ የተለያዩ የፖሊሲና የተግባር ውሳኔዎችን ያስተላልፋል። በስብሰባውም መዝጊያ ዕለት በፌብርዋሪ 24 ቀን 2013 (እኤአ) ህዝባዊ ስብሰባ በማዘጋጀት በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይና መወሰድ ስለሚገባቸው ፈጣን እርምጃዎች ህዝባዊ ውይይት ያደርጋል። በዚህ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ሁሉ እንዲገኙ እየጋበዝን ወደፊት ስለስብሰባው ቦታና ፕሮግራም ዝርዝር መረጃዎችን የምናወጣ መሆኑን እንገልጻለን።

የሽግግር ም/ቤቱ አመራር

Ethiopia: 4 journalists win free speech prize

Four journalists
(From top left clockwise)Eskinder Nega, Mesfin Negash, Reeyot Alemu and Woubshet Taye

Eskinder Nega Fenta, an independent journalist and blogger; Reeyot Alemu Gobebo of the disbanded weekly newspaper Feteh; Woubshet Taye Abebe of the now-closed weekly newspaper Awramba Times; and Mesfin Negash of Addis Neger Online were among a diverse group of 41 writers and journalists from 19 countries to receive the award in 2012. Eskinder, Reeyot, and Woubshet are imprisoned in Ethiopia; Mesfin fled in 2009. All four journalists were convicted in 2012 under Ethiopia’s draconian anti-terrorism law.
 

From ethnic liberator to national atrocities: The tale of TPLF

From ethnic liberator to national atrocities and corruption: The tale of the late Ethiopian Dictator of TPLF

Meles Zenawi from ethnic liberator to national atrocities.
 
No one knows why Melse Zenawi, the late tyrant of Ethiopia decided to trash the image of the people of Tigray in the name of Ethnic Federalism. But, regardless of his motives the evidence shows not only he tarnished the image of the people beyond recognition his stooges attempt to glamorize his legacy want to continue associating Tigray with corruption, atrocity and treachery.  What went wrong with ethnic panhandlers?
 

Wednesday 19 December 2012

ESAT Tikuret Fezralizm Tamagn Part 1

ESAT Tikuret Ato Hailmariam about Land Grabbing Ethiopia

ራሳቸውን ተበዳይ ኮሚዩኒተሮች በማለት የሚጠሩ የመንግስት የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች የተቀነባበሩ መረጃውን ለአለም ይፋ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአቶ በረከት ስምኦን በሚመራው የኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ፣ መስሪያ ቤቱ የሚፈጽመውን አድሎአዊ አሰራር በመንቀፍ ለአቶ በረከት ስምኦን የጻፉትን ደብዳቤ ግልባጭ ለኢሳት ልከዋል።
በደብዳቤው  አቶ በረከት በሚመሩት መስሪያ ቤቱ ወስጥ በህዝብ ግንኙነት ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኮሚኒተሮች ላይ የሚፈጸመው አድሎ የማይቆም ከሆነ እንዲሁም ድብዳቤው የቀረበላቸው አቶ በረከት በተለመደ ንቀታቸውና ዝምታቸው የሚቀጥሉ ከሆነ ” በምስልና በድምጽ የተቀነባበሩ መረጃዎችን ለተለያዩ የውጭና የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በመስጠትና ለህብረተሰቡ በማድረስ የምንቀጥል መሆኑን” ፣ እንዲሁም “እስከሚቀጥሉት 2 ሳምንታት መልስ የማይሰጠን ከሆነ ወደ ቀጣዩ የከፋ እርምጃ ለመሄድ እንገደዳለን።” ብለዋል።

16 EU Parliamenterians sent a letter to PM Hailemairm Desalegn


Ana Gomez
December 18, 16 members of the European Parliament issued a public letter to Ethiopian Prime Minster Hailemariam Desalegn expressing their grave concern regarding the continued detention of imprisoned journalist and blogger Eskinder Nega.
Arrested in 2011 and detained without access to an attorney for nearly two months, Mr. Nega was sentenced to 18 years in prison under the country’s broad 2009 Anti-Terrorism Proclamation on July 13, 2012. Mr. Nega’s arrest and prosecution came after he 
wrote online articles and spoke publicly about the possibility of an Arab Spring-like movement taking place in Ethiopia. After his sentencing, the government initiated proceedings to seize his assets, including the home still used by his wife and young son. An appeal hearing in the case is scheduled for Wednesday, December 19th

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ ጥያቄ አቀረቡ

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-16 የ አውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በፃፉት ግልጽ ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እንዲፈታ ጥያቄ አቀረቡ።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ አረብ አለም አብዮት በ ኢትዮጵያ ሊከሰት የሚችልበት ዕድል ሰፊ ስለመሆኑ በድረ ገጾች በመጻፉ ሳቢያ የስብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት የ 18 ዓመት እስራት እንደተወሰነበት የጠቀሱት  የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላቱ፤ ይህም አልበቃ ብሎ ባለቤቱና ልጁ የሚጠቀሙበት ንብረት ይወረስ ዘንድ በ ዐቃቤ ህግ ጥያቄ ቀርቦ ጉዳዩ ለውሳኔ በቀጠሮ ላይ እንደሚገኝ አውስተዋል።

Saturday 15 December 2012

ባዶ ሥልጣን ይዞ ውሸት ለመሳቂያነት

ዳኛቸው ቢያድግልኝ 
ፈጽሞ ለማጅ የማያሰኝ ዋሾነት በአቶ ኃይለማርያም ሲተወን አልጀዚራ ላይ ተመልክተናል። እርግጥ ነው እንደ ‘ባለ ራዕዩ’ ጮሌነትና አራዳዊ መገለባበጥ ቢያንሰውም ለመዋሸት ግንባራቸውን እንደማያጥፉ ግን አረጋግጠውልናል። አቶ ኃይለማርያም ምናልባት እየተቆጡ ሲዋሹ፣ እያስፈራሩ ሲቀጥፉ ስለኖሩ እንጂ እንደዚህ በአንድ ጊዜ የላቀ የዋሾነት ሜዳልያ የሚያሰጥ አቅም ሊኖራቸው ባልቻለ ነበር። ብዙ ሰባኪዎችን የተመለከቱ ግን አይመስለኝም። ቢሆን ኖሮ ቴክኒክ ተውሰው ትንሽ እውነት እያስደገፉ ግዙፍ ውሸት በመዋሸት ማደናቆር በቻሉ ነበር እንደ ታምራት ላይኔ። ግን ይዋሻሉ፣ አረ የምን ሰው ምን ይለኛል ነው፣ እግዜር ምን ይለኛልም አይሉም እኮ። አቤት መለስ እንዴት አድርጎ ጠፍጥፎ ሰራቸው እባካችሁ? ግን አላማረባቸውም ምክንያቱም ባዶስልጣን ይዞ ውሸት መሳቂያነት መሆኑን ሊያውቁ በተገባ ነበርና። ለዚህም ነው አስፎጋሪ ውሸት የዋሹት። ስለመሬት ነጠቃው ቀባጠሩ፣ ስለ ታሰሩት ወገኖችም ዋሹ። አዎ ኳስ ጨዋታዋ ላይም ሳቱ። ለመታጠፍ ደግሞ ዘገዩ ኳሱን ተዉትና መለስ እኮ ሃምሳ ጊዜ ኤርትራ እሄዳለሁ ብሎ ነበር አሉና መታጠፍ ጀመሩ። እናቴ ትሙት እጅሽን ልምታ እያለ የሚማጸን ልጅ መሰሉ። አባቱን ድረስልኝ የሚል ልጅ ይመስል ሮጠው መለስ መለስ ሲሉ ያሳዝናሉ። ጋዜጠኛይቱ በሆድዋ ምስኪን የምትል ይመስል ነበር።

የኢትዮጵያውያን ሴቶች ህይወት በእስራኤል እናድን!! (አሳዛኝ የቪድዮ ዘገባ)

Ethiopians life in Israel - Part 2 of 2

Friday 14 December 2012

ሱዛን ራይስ የቤንጋዚው መዘዝ ሰለባ ሆኑ! ራሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር እጩነት አገለሉ

susan rice
በተባበሩት መንግሥታ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑትና በፕሬዚዳንት ኦባማ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መስሪያቤትን እንዲመሩ ሊታጩ ይችላሉ የተባሉት ቀዳሚ ተወዳዳሪ ሱዛን ራይስ ራሳቸውን ከእጩነት አግልለዋል፡፡ ጉዳዩ ለፕሬዚዳንቱ የፖለቲካ ክስረት፤ ምርጫውን ሲቃወሙ ለነበሩት የሪፓብሊካን ፓርቲ አመራሮች እና በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውን ታላቅ ድል ሆኗል፡፡
ክሪስቶፈር ስቲቨንስ
በቅርቡ በተጠናቀቀው የአሜሪካ ምርጫ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸውን ካረጋገጡ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሱዛን ራይስ ሂላሪ ክሊንተንን እንደሚተኩ በሰፊው መነገር ተጀመረ፡፡ የፕሬዚዳንቱ ቀዳሚ እጩ መሆናቸው ብዙ ቢነገርላቸውም ከተቃዋሚዎቹ የሪፓብሊካንና ሌሎች ጉዳየኞች የተቃውሞ ድምጽ ለመስማት ግን ብዙም ጊዜ አልወሰደም፡፡

በማረሚያቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩን መንግስታዊው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አመነ

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- መንግስታዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች
መኖራቸውን በይፋ አመነ፡፡
ኮሚሽኑ በባህርዳር ከተማ የተከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ተከትሎ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ላይ የቀረበ
አንድ ጥናት እንዳመለከተው በሕገመንግስቱ የተደነገጉና አገሪቱ ተቀብላ ያጸደቀቻቸውን ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች
በሚቃረን መልኩ በአንዳንድ ማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በታራሚዎች ላይ እየተፈጸሙ መሆኑን ይፋ
አድርጓል፡፡

በማረሚያ ቤቶች በተለይ ልዩ ድጋፍ በሚሹ ሴቶች፣ህጻናት፣አረጋዊያንና የአካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ
መብት ጥሰቶች ይበልጥ አሳሳቢ ናቸው ብሏል፡፡እንዲሁም በሁሉም ማረሚያ ቤቶች የምግብ ፣የመኝታ ችግሮች መኖራቸውን
በመጥቀስ ሁኔታው መሻሻል እንደሚገባው ኮሚሽኑ ምክር ሰጥቷል፡፡
በአምባሳደር ጥሩነህ ዜና የሚመራው ይህው ተቋም ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር የሚቀርቡ ሪፖርቶችን
ውሸት ናቸው በሚል እየተከላከለ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን ችግሩን በተለሳለሰ አቋምም ቢሆን ለመቀበል
ተገዷል፡፡
 
በአዲስአበባ ማረሚያ ቤቶች ከሚገኙ ታራሚዎች መካከል 62 በመቶ ያህሉ በአእምሮ ሕመም እየተሰቃዩ መሆኑን
በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም ይፋ በሆነው የጤና ጥበቃ ስትራቴጂ ዕቅድ ላይ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡
ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከግንቦት 7 እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላችሁ በመባል ከታሰሩት በተጨማሪ፣ በአንዳንድ የሙስሊም መሪዎች ላይ አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈጸመ ለማወቅ ተችሎአል።

የታህሣሥ ግርግር :-

የታህሳስ 5 1953 መፈንቅለ መንግስት
ፎቶ:- መስከረም 1953ዓ/ም
ከግራ ወደ ቀኝ ጄነራል መንግስቱ ነዋይ ሻምበል አበበ ቢቂላ ጄነራል መርዕድ አበበ
 ምክንያት:- ጨቋኙን የፊውዳሉን አገዛዝ አስወግዶ ህገ መንግስታዊ ተራማጅ ዘውዳዊ ስርዓት መዘርጋት
መንስኤ:-ንጉሰ ነገስቱ በመጀመሪያ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ቀጥሎም ብራዚልን ለመጎብኘት ከሀገር መውጣት
ድርጊቱ የተከናወነበት ሰዓት:- ታህሳስ 5 1953 ጠዋት የለውጥ ፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ልዑል ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ ን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸውንና ይፋ አደረጉ።

በዩኒቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ኢህአዴግ ስልጠና ሊሰጥ ነው

ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጡት በመጪው ሳምንት በሚጀመረው በዚህ የስልጠና መርሀግብር የሁለተኛ ደረጃ ፣ የመሰናዶ፣ የኮሌጅ እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይሳተፋሉ። በመርሀ ግብሩ መሰረት ከነዚሁ የትምህርት ተቋማት የሚመረጡ ቁልፍ ተማሪዎች በቅድሚያ ስልጠና ከተሰጣቸው በሁዋላ፣ እነዚሁ ሰልጣኞች ተመልሰው በመሄድ ለተቀረው ተማሪ ስልጠና ይሰጣሉ።

ስልጠናው የሚቆየው ለአንድ ሳምንት ሲሆን፣ የሚሰለጥኑበት ሁኔታም በአብዛኛው ኢህአዴግ ባለፉት 8 አመታት ስላስገኛው ድሎች፣ ስለርእዮተ አለምና ስለእስልምና አክራሪነት ይሆናል። ስልጠናውን በፕላዝማ ቴሌቪዥን ለማካሄድ እቅድ መኖሩም የታወቀ ሲሆን፣ የመጨረሻ ውሳኔ እንዳልተሰጠበት ታውቋል።

አጠቃላይ እንቅስቃሴው በመጪው የካቲት ወር የሚካሄደውን የወረዳ ምርጫ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። መንግስት የዘረጋውን የአንድ ለአምስት አደረጃጃት በስፋት ወደ ነዋሪው ለማዳረስስ እየሰራ ነው።
በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች በአንድ ለአምስት አደረጃጀት በመወጠራቸው ሌሎች ጉዳዮችን እንዳያስቡ እየተደረጉ መሆኑን ነው ሰራተኖች የሚናገሩት። ሰራተኞቹ በእየለቱ ከቀኑ 10 ሰአት ጀምረው ስለመስሪያቤታቸው የስራ እንቅስቃሴ ለአንድ ለአምስት ሰብሳቢው ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ሰብሳቢውም እንዲሁ ለበላይ አለቃው መረጃዎችን በማስተላለፍ ገዢው ፓርቲ አጠቃላይ ፖለቲካ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር እንዲያመቸው ማድረጉን ሰራተኞች ገልጸዋል።

ENTC has formed a new chapter in Norway

Ethiopian National Transitional Council (ENTC) has continued to work on expanding its organizational reach throughout the world. This effort includes strengthening the chapters that are already established as well as forming new ones. In line with this effort, it has announced the successful completion of the formation of ENTC Norway chapter with dedicated Ethiopians.

email: entcnorway@gmail.com

Ethiopia: On Constitutional Absurdities – By Alemayehu Fentaw

By: Alemayehu Fentaw Weldemariam *,

“Those who can make you believe absurdities can make you commit atrocities.”— Voltaire

On November 29, 2012, Ethiopia’s Prime Minister, Hailemariam Desalegn, conferred the rank of deputy prime minister, with the approval of parliament, on Muktar Kedir, chief of staff at the Office of the Prime Minister, and Debrestion Gebremichael, Ph.D., Minister of Communications and Information Technology.
My aim in this essay is to examine the constitutionality of the appointment of the two new Deputy Prime Ministers and critique the claims so far made as to the constitutionality of these recent appointments by Prime Minister Desalegn.

32 ONLF Rebels and Ethiopian Forces killed in Dhagahbour – Diplomatic Source

12 December 2012

(Ogadentoday Press)- A report says that clashes between ONLF, Ogaden National Liberation Front and a coalition of Ethiopian military and Liyu Police Troops erupted in the restive Ogaden region, Dhagahbour Zone on Tuesday.
The sources said that 32 Ethiopian Troops and ONLF fighters killed in the fighting.

The 9-year anniversary of the brutal massacre of 424 disarmed Anuak

 December 13, 2012 marks the 9-year anniversary of the brutal massacre of 424 disarmed Anuak in Gambella, Ethiopia by the TPLF/EPRDF Defense Forces armed with guns and militia groups armed with machetes. Not just the families of the victims, but all Anuak, will forever remember that dark day that brought so many pains, tears and suffering.

CPJ – Eritrea, Ethiopia Rank Africa’s Worst Jailer of the Press

Paris — Eritrea and Ethiopia have respectively become Africa’s leading jailers of journalists, according to the jailed Journalists List of 2012 released by the US-based, Committee to Protect Journalists (CPJ).

The number of journalists imprisoned worldwide has reached a record high this year, with 232 reporters, photojournalists and editors imprisoned in 27 countries.
The figure above has seen a rise of 53 to that of last year and is the highest since CPJ began the survey in 1990.

Ethiopia remains mired in poverty in spite of progress

LOS ANGELES, CA (Catholic Online) – As an example, Ethiopia’s economy has been percolating at an annual rate of nearly 10 percent for the last seven years. However, a third of the population still lives below the poverty line.
Economic advisor for the United Nations Development Program in Ethiopia, Samuel Bwalya says that the nation has to be patient while waiting for a trickle-down effect to lift more people from poverty.

ESAT Yesamintu Engida Prof. Befekadeu Degefe Part II Dec 2012 Ethiopia

Wednesday 12 December 2012

ESAT Yesamintu Engida Prof. Befekadeu Degefe Part I Dec 2012 Ethiopia

Susan Rice, Spokeswoman for Tyranny in Ethiopia (Tedla Asfaw)

It is exactly three month since the terrorist attack of Benghazi that took the life of US Ambassador Chris Stevens and three other officials. Ambassador Susan Rice the US Ambassador to United Nations has become a very controversial figure since Obama won reelection and considered her as the favorite to replace Hillary Clinton as Secretary of State.
 

Ethiopian Court Gives Oromo Politicians Prison Over Secession

(Bloomberg) — Ethiopia’s Federal High Court sentenced two senior Oromo politicians to as much as 13 years in prison after their convictions on charges of inciting a secessionist rebellion.

Bekele Gerba, deputy chairman of the opposition Oromo Federalist Democratic Movement was sentenced to 8 years in prison and Olbana Lelisa of the Oromo People’s Congress party to 13 years, Judge Kenate Hora said. “It’s absolute injustice,” Bekele said to reporters outside the courtroom.

በሁለት ቀናት ልዩነት ሦስት ጊዜ ቀብሯ የተፈጸመው ወላድ ጉዳይ እያነጋገረ ነው

-    አስከሬኗ ከመቃብር ወጥቶ ተገኝቷ

በታምሩ ጽጌ


የመጀመርያ ልጇን በቀዶ ሕክምና ከተገላገለች በኋላ ደም ፈሷት ሕይወቷ ያለፈው የ27 ዓመት ወጣት የቀብር ሥርዓቷ ባለፈው ቅዳሜ፣ እሑድና ከትናንት በስቲያ ሰኞ የመፈጸሙ ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡ ሟች ቤተልሔም ሰለሞን ልጅ ወልዳ ለመሳም ዘጠኝ ወራትን ስትጠብቅና የእርግዝናዋንም ሁኔታ ስትከታተል ቆይታ የመውለጃዋ ዕለት በመድረሱ፣ ጎፋ ማዞሪያ ወደሚገኘው ሮያል የጽንስና የማኅፀን ሕክምና ከፍተኛ ክሊኒክ የሄደችው ኅዳር 27 ቀን 2005 ዓ.ም. ነበር፡፡

ክትትል ስታደርግበት የነበረው ክሊኒክ ተቀብሎአት ወደ ማዋለጃ ክፍል ካስገባት በኋላ የምጥ መርፌ ቢወጋትም፣ በዕለቱ ልትወልድ አለመቻሏንና ወደ ቤቷ መመለሷን ወላጅ እናቷ ወይዘሮ በለጡ አበበና ባለቤቷ አቶ ፍስሐ እሸቴ ገልጸዋል፡፡

የኃይለ ማርያም የአስመራ መንገድ ከመለስ ይለይ ይሆን?

በየማነ ናግሽ

አንድ በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወጣት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ‹‹ቶክ ቱ አልጀዚራ›› ከሚለው የአልጄዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በድረ ገጽ ለማግኘት እየታገለ ነው፡፡ አልጄዚራ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲዘጉ ከተደረጉ ድረ ገጾች መካከል ነውና አልቻለም፡፡ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃለ ምልልስ የሰጡት ለጋዜጠኞቹ ብለው ነው? ወይስ በአገራቸው ሕዝብ እንዲነበብ እንዳይታይ ከማይፈቀደው ሚዲያ ጋር መነጋገራቸው ምን ይሉታል?›› እያለ ከጓደኞቹ ጋር በማጉረምረም ከአንድ ኢንተርኔት ካፌ ሲወጣ አየሁት፡፡

ተቋርጦ የነበረው የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክስ እንደገና ተጀመረ

-    ዋስትና ተፈቅዶለት በ50 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቀ
 
 
በታምሩ ጽጌ

ሦስት ክሶች ተመሥርተውበትና ዋስትና ተከልክሎ ለአራት ቀናት በማረሚያ ቤት ከቆየ በኋላ፣ ክሱ ተቋርጦ በነፃ የተሰናበተው የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ የተቋረጠው ክስ በድጋሚ ትናንትና ፍርድ ቤት ቀርቦበት በ50 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቀ፡፡ ከነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በራሱና በጽሑፍ አቅራቢዎች አምስት ጊዜያት ታትመው በወጡ መጣጥፎች ምክንያት ክስ ተመሥርቶበት፣ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ዋስትና በመከልከሉ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ መደረጉ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የመድረክ አመራር በእስራት ተቀጡ

-    ጋዜጠኛ ርዕዮተ ዓለሙ ለሰበር ያቀረበችው አቤቱታ ለውሳኔ ተቀጠረ
 
በታምሩ ጽጌ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋ መምህርና የመድረክ ፓርቲ አመራር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ስምንት ተከሳሾች፣ ከሦስት ዓመታት እስከ 13 ዓመታት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ትናንትና ተወሰነባቸው፡፡ በሽብርተኝነት ወንጀል በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የተመሠረተባቸውን ክስ ሲመረምር የሰነበተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ትናንትና በሰጠው የቅጣት ውሳኔ፣ አንደኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ በቀለ ገርባን በስምንት ዓመታት፣ የኦህኮ ፓርቲ አመራር የነበሩትን አቶ ኦልባና ሌሊሳን በ13 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ሌሎቹ ተከሳሾች ማለትም ወልቤካ ለሜ፣ መሐመድ ቡሳ፣ ሐዋ ዋቆ፣ ደረጀ ከተማ፣ አዲሱ ሙከሪና ገልገሎ ቱፋ ከሦስት እስከ 12 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ኦልባና ሌሊሳና አቶ ገልገሎ ቱፋ ለአራት ዓመታት ከማንኛውም ማኅበራዊ መብቶቻቸው ታግደዋል፡፡ ሌሎቹም ለሁለት ዓመታት ታግደዋል፡፡

Panic in the fading powerhouse of TPLF By Robele Ababya

The late Zenawi kept all top state secrets close to his chest and went to his grave without sharing any of those to his successors. Therefore there is no doubt that damaging disarray and or split has taken center-stage within his party. The extinction of TPLF and the emergence of freedom for all Ethiopians are inevitable.

  There is fear in the vanishing TPLF powerhouse; now is the time to finish it off by staging a debilitating civil strike and invigorating the ongoing Ethiopian Muslims’ demand for civil rights. 

The mighty CPSU (Communist Party of the defunct Soviet Union) disintegrated leaving in its wake ruins upon which the process of building a democratic system flourished in earnest. The slogan “to each according to his needs and from each according to his ability” has long gone down the drain. Anti-corruption storm is sweeping across China, which is good news for the democratic opposition at home in Ethiopia and in the Diaspora - and a nightmare to the corrupt TPLF top officials. In the circumstances the TPLF borne out of Marxist Leninist League of Tigray has no chance to rebuild its gravely ruined powerhouse as argued in the paragraphs below.

Ethiopia among world’s worst jailer of journalists: Press watchdog

Imprisonment of journalists worldwide reached a record high in 2012, driven in part by the widespread use of charges of terrorism and other anti-state offenses against critical reporters and editors, the Committee to Protect Journalists has found. In its annual census of imprisoned journalists, CPJ identified 232 individuals behind bars on December 1, an increase of 53 over its 2011 tally.

With six journalists in prison, Ethiopia was the eighth-worst jailer in the world. The authorities broadened the scope of the country’s anti-terror law in 2009, criminalizing the coverage of any group the government deems to be terrorist, a list that includes opposition political parties. Among those jailed is Eskinder Nega, an award-winning blogger whose critical commentary on the government’s extensive use of anti-terror laws led to his own conviction on terrorism charges.

Tuesday 11 December 2012

የአዲስ አበባ ወጣቶች የአንድነት የቃሊቲ ጉብኝት እንዲካሄድ ጠየቁ


ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ለኢሳት በላኩት መልእክት እንደገለጡት በመጪው እሁድ ታህሳስ 7፣ 2005 ዓም አለአግባብ የታሰሩ የሙስሊም ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን፣ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ መሪዎችን በቃሊቲ ተገኝተው ለመጠየቅና ለመዘከር አስበዋል።

ማንኛውም የህገመንግስቱን የእምነት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መከበር እንዳለበት የሚደግፍ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ወደ ቃሊቲ በመሄድ ድጋፉን እንዲያደርግ እንጠይቃለን ያለው መግለጫ፣ እነዚህ ታሳሪዎች ህገመንግስቱ የሰጣቸውን መብት በመጠቀም መላው ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የሰላም እና የነጻነት ታጋዮች እንደሆኑ እና ህዝቡም ሰለማዊ አላማቸውን እንደሚደግፍ በእለቱ ማሳየት ይጠበቅበታል ብሎአል።

አልጀዚራ ባለፈው ሳምንት ለጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለታሰሩት የህሊና እስረኞች ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በእስር ላይ የሚገኙት አሸባሪዎችና ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው እንጅ የህሊና እስረኞች አይደሉም በማለት መልሰዋል።

ታላቅ የአንድነት የቃሊቲ ጉብኝት በመጪው እሁድ ታህሳስ 7 2005 ዓ ም

ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና አርነት ሲሉ በየእስር ቤቱ ታጉረው በዘረኞችና አንባገነኖች ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው ያሉ ጋዜጠኞችን፣ የሙስሊሙ ንቅናቄ መሪዎችን፣  የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እሁድ  ታህሳስ 7 2005 ቃሊቲ ድረስ ሄዶ ለመጠየቅ መታቀዱ እጅግ ቅዱስ አላማ ነው። በዚህ የፍትህ  ንቅናቄ መሳተፍ የምትችሉ ነጻነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ሰብአዊ ክብርን ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በዘር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት እንዲሁም በፖለቲካ አስተሳሰብ ሳትከፋፈሉ በአንድነት ተሳታፊ እንድትሆኑና ታሪክ እንድትሰሩ እንማጻናለን።  ይህ ንቅናቄ ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽኦ አድርጉ። አንድነት ሃይል ነው! መንገዶች ሁሉ ወደቃሊቲ ያመራሉ!
ይህን ጥሪ ላልሰሙ አሰሙ፣ “like & share” አድርጉት።
“You can jail a Revolutionary, but you can't jail the Revolution.” Huey Newton
ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና አርነት ሲሉ በየእስር ቤቱ ታጉረው በዘረኞችና አንባገነኖች ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው ያሉ ጋዜጠኞችን፣ የሙስሊሙ ንቅናቄ መሪዎችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እሁድ ታህሳስ 7 2005 ቃሊቲ ድ
ረስ ሄዶ ለመጠየቅ መታቀዱ እጅግ ቅዱስ አላማ ነው። በዚህ የፍትህ ንቅናቄ መሳተፍ የምትችሉ ነጻነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ሰብአዊ ክብርን ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በዘር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት እንዲሁም በፖለቲካ አስተሳሰብ ሳትከፋፈሉ በአንድነት ተሳታፊ እንድትሆኑና ታሪክ እንድትሰሩ እንማጻናለን። ይህ ንቅናቄ ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽኦ አድርጉ። አንድነት ሃይል ነው! መንገዶች ሁሉ ወደቃሊቲ ያመራሉ!
ይህን ጥሪ ላልሰሙ አሰሙ

ሰበር ወሬ፤ ተመስገን ደሳለኝ 50 ሺህ ብር ዋስ ተጠየቀ


ከአቤ ቶክቻው

6 ቀን በቃሊቲ ታስሮ 
ከተለቀቀ በኋላ ዳግም ክስ የተመሰረተበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ 50 ሺህ ብር ዋስትና ከፍሎ እንዲለቀቅ ፍርድቤቱ መወሰኑን አንድ ወዳጄ ተሽቀዳድሜ ልንገርህ ብሎ ነግሮኛል። እንደ ወዳጄ መረጃ፤ ተሜ ብሩን እስኪያመጣ ድረስ በእስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል።

ዝርዝር ካገኘሁ እነግራችኋለሁ!

ባለመረጃ ወዳጄን አመሰግናለሁ!

ተመስገንንም በርታ እለዋለሁ!

Monday 10 December 2012

የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥ ማነው?

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

በከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው ለረጅም ዓመት አገልግለዋል፤ ከዚያ ከለቀቁ በሁዋላ በጥብቅና ሙያ እየሰሩ ይገኛሉ። ታዋቂው የህግ ባለሙያ አነጋጋሪ በሆኑ የኢህአዴግ የፈጠራ ክሶች ዙሪያ ለተከሳሾች ጥብቅና በመቆምና በድፍረት በመሙዋገት ይታወቃሉ። በ1997 ከአንድ የፈጠራ ክስ ጋር በተያያዘ ለተከሳሾች ጥብቅና ቆመው ነበር፤ በፌደራል ጠ/ፍ/ቤት በተሰየሙ ዳኛ ተብዬዋች ተግባር ክፉኛ የተበሳጩት እኚህ የህግ ባለሙያ በወቅቱ እንዲህ አሉኝ፥ «በንጉሱ ዘመን ነው፤ በአ.አ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ልንመረቅ ሽር ጉድ እንላለን። የምንወደው የህግ መምህራችን የኛን ሁኔታ ታዝቦ ኖሮ…አንድ ጥያቄ አቀረበልን፤ “ አሁን ሳያችሁ በደስታ እንደተዋጣችሁ ነው፤ በመመረቃችሁ ደስተኛ ናችሁ ማለት ነው?... “ ሁላችንም በጥያቄው ተገርመን .. እንዴት መምህር?..በጣም ደስተኞች ነን ፤  አልነው። ደግሞ ጠየቀን ፥ “pሁላችሁም ደስተኞች ናችሁ?”..ሲለን.. አዎን ደስተኞች ነን አልነው በአንድ ድምፅ። በጣም አዝኖ እንዲህ አለን ፥  ``ሕግ በሌለበት አገር ህግ ተምራችሁ ..ሕግ የምታስፈፅሙ ይመስል፥ እንዲህ
መደሰታችሁና መመፃደቃችሁ ታሳዝናላችሁ.!… ``ዛሬ የበለጠ የመምህራችን ንግግር ታወሰኝ፤ እውነትም ሕግ በሌለበት አገር…»pሲሉ ታዋቂው የህግ ባለሙያ ያወጉኝን ለመጣጥፌ መንደርደሪያ ማስቀደሜ ያለምክንያት አይደለም።
   

Sunday 9 December 2012

ውለታ የማታውቅ ሀገር

limenih tadesse

• ያ የኮሜዲ አውራ “እብድ” ተብሎ ጎዳና ላይ “ቆሼ” ይለቅማል!
• እርሱን ያፈራው ኅብረተሰብ የወደቀን ቀና ከማድረግ እንዳይቃና ይተጋል
• ስለዚህ ኅብረተሰቡ እንደ ድመት የራሱን ልጆች ይበላል!
ይኸውልህ ወዳጄ የተመለከትኩትን፣ የታዘብኩትን እና ያስተዋልኩትን እንደወረደ ላጫውትህ፡፡ ያ ጉምቱ የጥበብ ሰው፣ ያ የኮሜዲ-የጭውውት አውራ፣ ያ ጥበብን የተቀባው ባለትልቅ ተሰጥዖው ሰው፣ ያ ከሥነ-ሠብዕ ጥበብ ተሻግሮ የአዕዋፋትን ዝማሬ ምስጢር፣ የንፋስን ሿሿታ፣ የበር-መስኮት ሲጥሲጥታ ሳይቀር በጥበብ ሥራው ላይ አክሎ የሚከውንልህ ተዋናይ ልመንህ ታደሠ፣ ከፒያሳ ወረድ ብሎ ከሚገኘው ቢስ መብራት አደባባይ ላይ፣ እንደ ማንም ቆሼ ሲለቅም ተመለከትኩት፡፡

ልመንህን ያየ፣ እኔን-አንተን አየ፤ እኔን-አንተን ያየ ኅብረተሰቡን አየ፤ ኅብረተሰቡን ያየ-ተቋማቱን አየ ነው እያልኩህ ያለሁት ወዳጄ፡፡
ያ የጥበብ አውራ ልመንህ ታደሰ ሰውነቱ ገርጥቶ፣ የማይቀይራትን ጥቁር ሰማያዊ ወይም ጥቁር ሱፍ በውሃ ሰማያዊ ሸሚዝ አጥልቆ፣ የተጨራመተች ልሙጥ ጥቁር ቆዳ ጫማ ተጫምቶ፣ እንደ ባይንደር መሳይ ነገር ላይ የተጨረማመቱ ቡጭቅጫቂ ወረቀቶችን ይዞ የሥነ ሥዕል ንድፍ እንደሚሰራ ጀማሪ ሰዓሊ ከአደባባይ ሆኖ ድምም-ፍዝዝ ይላል፤ በጀርባው ባነገተው ጥቁር ቦርሳ /ኮሮጆ/ አንዳች ነገሮችን ሸክፏል፡፡ ልመንህ ታደሠ ተርቦም ሊሆን ይችላል-ማን ያውቃል?

Parrot H/Desalign Says There Are No Political Prisoners in Ethiopia

ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለምታደርገው የእግር ኳስ ጨዋታ ቦታ እንዲለወጥ መጠየቁን አላውቅም አሉ

ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይህን የተናገሩት ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። ረዩተር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መላኩ አየለን በመጠቀስ ” ለተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እግር ኳስ ፌደሬሽኑ የጨዋታው ቦታ እንዲቀየር መጠየቁን ” ዘግቦ ነበር። ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንም ለጉዳዩ የዜና ሽፋን መስጠታቸው ይታወቃል።

በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ጨዋታ መሰረዙዋን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መግለጹን ረዩተር ከትናንት በስቲያ ዘግቧል።


እነዚህ ዘገባዎች በስፋት በመገናኛ ብዙሀን በቀረቡበት ሁኔታ ነው፣ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ” ከኤርትራ ጋር ወዳጅነት ከፈለጋችሁ ለምን ከኤርትራ ጋር ለምታደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ የመጫዎቻ ቦታው እንዲቀየር ፈለጋችሁ?” በሚል ለቀረበላቸው ድንገተኛ ጥያቄ በመደናገጥ መረጃ የለኝም ሲሉ መለስ የሰጡት።

Saturday 8 December 2012

`Land Grab` Deals Hurt Local Farmers: UN

Controversial farmland deals in developing countries can have a negative impact on the people who live on the land, according to a new U.N. report

While investment in agriculture is essential to help developing countries reduce hunger and poverty, the U.N. Food and Agriculture Organization says these large-scale “land grabs” don’t always help. The surging global demand for food, fodder and fuel crops is driving a land rush in parts of the developing world. Investors are pouring money into large-scale farmland leases in Africa, Asia, former Soviet countries and elsewhere. 

Well-known patriot Shambel Zewdu Ayalew joins ENTC

http://www.ethiopianreview.com/2011/shabel-zewdu-araya_115153.jpg
 A great Ethiopian patriot Shambel Zewdu Ayalew joins the Ethiopian National Transitional Council (ENTC) as an adviser.

Shambel Zewdu was elected as a member of Ethiopian parliament representing Gondar in 2005, but when the Woyanne junta stole the election, he refused to join the parliament and went into the bushes to fight for the Ethiopian people’s right to choose their own government through the ballot box. In that regard, he is an authentic Ethiopian hero and patriot who stood firm on his principles and paid enormous personal sacrifices while others betrayed their people for crumbs.

Last month, Shambel Zewdu arrived in Uganda and he is now assisting ENTC with building its organizational structure inside Ethiopia and neighboring countries, according to the ENCT leadership.
ENTC has also revealed that it will convene its second general assembly in the first week of this coming February and that preparations are currently underway.

በአንዋር መስጊድ ዛሬም የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋቡ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እስላም ኢትዮጵያውያን በታላቁ የአንዋር መስገድ በመገኘት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እየተከተለ ያለውን ፖሊሲ አምርረው ተቃውመዋል።
ምእመናኑ 27 ቁጥር የተጻፈበት ወረቀት በማውለብለብ ” አንቀጹ ይከበር፣ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፣ አሸባሪዎች አይደለንም” በማለት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ተሰምቷል።

ምእመናኑ 27 ቁጥር በመያዝ ተቃውሞአቸውን ያስተጋቡት በህገመንግስቱ በአንቀጽ 27 ላይ የተደነነገገው የሀይማኖት እኩልነት መብት ይከበር በማለት ነው።
አዲሱ መንግስት የመለስ መንግስት ይከተለው የነበረውን ችግሮችን በሀይል የመፍታት ዘዴ መከተሉ፣ ከኢትዮጵያውያን አልፎ በጸረ ሽብር ትግሉ ወዳጅ ተደርጋ የምትታየዋን አሜሪካ ሳይቀር እያሳሰበ የመጣ ጉዳይ ሆኗል።

በእስር ላይ በሚገኙት የኮሚቴ አባላት ላይ የሚታየው የተንዛዛ የፍርድ ሄደትና በአባላኦቹ ላይ በእስር ቤት የፈጸመው አሰቃቂ እርምጃ ምእመኑን ማበሳጨቱን ወኪላችን ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

በጂዳ የብአዴን ዝግጅት ላይ የተገኙ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተባረሩ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) 32ኛ አመት ለማክበር አርብ ምሽት በጅዳና በአካባቢዋ በተዘጋጀ ዝግጅት ለመሳተፍ የሄዱ በርካታ ነዋሪዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውንና ስብሰባው በጊዜ መበተኑን ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ገልጿል።

ዛሬ በተጠራው የብአዴን ዝግጅት ላይ የተቃውሞ ድምጻችን እናሰማለን በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወረቀት በህቡዕ የበተኑ ሲሆን፤ በስብሰባው ላይ ተቃውሞ እንዳያካሂዱ በሚል ፍራቻ ጥሪ የተደረገላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ከስብሰባው ውስጥ እየተጠሩ እንዲባረሩ መደረጉን ነዋሪዎች ለነቢዩ ሲራክ ገልጸውለታል።
ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መንገድ መታዎቂያ አሳዩ የሚል ምክንያት ለመስጠት የተሞከረ ቢሆንም፤ መታወቂያ ይዘው የተጠረጠሩና የተፈሩ አንዳንድ ነዋሪዎችም ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ እንደተደረጉ ታውቋል፡፡

የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በባንዴራ አጅበው ከኮታቸው ላይ የለጠፉ የብአዴን አባላት ነዋሪዎችን በጥርጣሬ አንዳይገቡ ሲከለከሉና የፈለጓቸውን እየመረጡ ሲያስገቡ እንደታዘበ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ዘግቧል።
ከመግቢያው በር ያሉትን የሳውዲ ልዩ ኮማንዶ ወታደሮችን ያናገረው ነቢዩ ሲራክ፤  ”የቆንስሉ ሃላፊዎች ማንም እንዳይገባ ከልክሉ ብለውናል” በማለት እንዳስረዱትና ነዋሪውን በማግባባት ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ሲማጸኑ እንደተመከተም ገልጿል።
የብአዴን አባላት እገዳው የተደረገው በጸጥታ ምክንያት እንደሆነና ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተጠረጠሩና የማይታወቁ ሰወች እንዳይገቡ እገዳ መጣሉን ገልጸዋል።

አንዳንድ የብአዴን አባላት በጥሪ የመጡትንም እያንጓጠጡ ያስወጧቸው ሲሆን፤ ስብሰባው ያለወትሮው በጊዜ ሲጠናቀቅ ከስብሰባው የወጡ አንዳንድ ሰዎች ሲገቡ ችግር እንደገጠማቸውና በስብሰባው ላይ ምንም አይነት ፎቶም ሆነ ቪዲዮ እንዳይነሳ ቁጥጥር መደረጉንና ስብሰባው በተቃውሞና ፍራቻ ሲናጥ ማምሸቱን እንደገለጹለት ነቢዩ ሲራክ ከጂዳ ገልጿል።