Thursday 6 December 2012

ጠ/ሚ/ር ሀይለማሪያም ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በማናቸውም መድረክ አስመራ ጭምር ሄደው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጡ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ጠ/ሚ/ር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በማናቸውም መድረክ አስመራ ጭምር ሄደው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጡ::

አቶ ሀይለማሪያም ይህንን የገለጡት ከአልጀዚራ ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው::
በዛሬው እለት በተሰራጨው የአቶ ሀይለማሪያም ቃለምልልስ አስመራ ሄዶ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የመነጋገር ፍላጎት የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ፍላጎት ጭምር እንደነበር ገልጠዋል::
 አቶ መለስ ከአቶ ኢሳያስ ጋር አስመራ ጭምር በመሄድ ለመደራደር ከ 50 ጊዜ በላይ መጠየቃቸውን አቶ ሀይለማሪያም ገልጠዋል::

No comments:

Post a Comment