Monday 2 September 2013

ሰማያዊ ፓርቲ ለጳግሜ 2 ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ አቤ ቶክቻው!!

543915_599142770128325_705621154_n
ሰማያዊ ፓርቲ ለጳግሜ 2 ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

ሰማያዊ ፓርቲ ነሃሴ 26 ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ በመንግስት ከተጨናገፈበት በኋላ ዳግም ሌላ ሰላማዊ ሰለፍ ለጳግሜ 2 ሁለት ሺህ አምስት ዓ.ም በመስቀል አደባባይ መጥራቱን ዛሬ አስታወቀ፡፡ የሰልፉ ስያሜ “ዘመቻ ለህግ የበላይነት” የተሰኘ ሲሆን ከሶስት ወራት በፊት ፓርቲው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ይመለሱልኝ ሲል አቤት የሚልበት ነው፡፡



ፓርቲው ዛሬ ነሀሴ 27 ለአዲሳባ ከተማ አስተዳደር በላከው ደብዳቤ ሰልፉን እንደሚያዘጋጅ አሳውቋል፡፡ አስተዳደሩ የሰጠውን ምላሽ ለማጣራት ያደረኩት ሙከራ የለም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድነት ፓርቲ በበኩሉ መስከረም አምስት ቀን 2006 ዓ.ም ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል የማይታወቅ ከሆነ ይሄው አሁን ይታወቅ፡፡

No comments:

Post a Comment