Sunday, 2 December 2012

ወያኔ በመተካካት ሰበብ ራሱ ያጸደቀውን ህገ መንግስት ጣሰ

ከይኸነው አንተሁነኝ

ታህሳስ 1 2012

የወያኔ ፓርላማ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ራሱ ያጸደቀውን የይስሙላ ህገ መንግስት በመጣስ ሁለት ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሮችንና የውጭ ጉዳይ ሚንስትርን ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ሚንስትሮችን በመሾም ቀሪው ባለበት እንደሚረግጥ ከሃይለማሪያም ደሳለኝ የቀረበለትን ተቀብሎ አጽድቋል።
ይህን የህወሃቶች ጊዜ የወሰደ፣ ጥንቃቄ የተሞላበትና የተጠና ሹመት በተመለከተ ገና ያኔ የዘረኛው መለስ ዜናዊ ግብኣተ መሬት ይቅርና በወያኔዎችና የቅርብ ዘመዶች በሚስጥር የተያዘው ገሃድ ሞቱ በይፋ ሳይገለጽ፤ የነበረከት የለቅሶ ሀገር አቀፍ ወጥ ሙሾና ረገዳ ተደርሶ ሳይመረቅ ፤ ዘማሪያን በመዝሙራቸው፣ ደራሲያን በግጥሞቻቸው፣ ዘፋኞች በዘፈኖቻቸውና ተዋኒያንም በትእይንታቸው ”ባለ ራዕዩ መሪ” እያሉ ከመዘባረቃቸው በፊት፤ አዜብ መስፍን የምርጫ ቅስቀሳ እንደሆነ ባሳበቀባት ንግግሯ ”የመለስ ራዕይ እስካልተበረዘና እስካልተከለሰ ድረስ … ወዘተ ወዘተ ከማለቷ እጅግ በፊትና የጠቅላዩን መሞት  ያወቁ ሁሉም ወያኔዎች በድብቅ እህህ በሚሉበት ወቅት ሳይቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ ካንድ በላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሊኖር እንደሚችል ያውቅ ነበር።

Why Ethiopian hero’s and nationalists are terrorists for the tyrant regime?

By Abenezer Aregawi

“I was called a terrorist yesterday, but when I came out of jail , many people embraced me, including my enemies, and that is what I normally tell other people who say those who are struggling for liberation in their country are terrorists, I tell them that I was also a terrorist yesterday, but, today, I am admired by the very people who said I was one.”
 
Nelson Mandela, Larry King Live, May 16, 2000First of all I want to clear myself that I am not racist even if I grown up at the rule of the existed regime since I am at adult age now that whenever I used the word minority it doesn’t imply any racial group rather to indicate the minority traitors and crooks who are ruling the country without the consent of the Ethiopian people. The weyanna regime used ethnic-federalism to divide and rule the Ethiopian people who lived together for the last 3000 years regardless of existed differences. This people have long history in fighting foreign aggressors and internal chaos happening in between of warlords. They stand in one to settle peace and security and respect the sovereignty of the country today destructing and selling by the weyanna/EPRDF regime. Let me go back to the main agenda of this paper.
 

“ህወሓት መች ጥያቄ ውስጥ ገባና?” ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

 December 2, 2012
 
dagnachew assefa

ሰሞኑን የተካሄደውን ምደባ በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ አዲስ አድማስ ላይ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ጥያቄ፡- ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀደቁትን አዲስ የካቢኔ አደረጃጀት እንዴት ያዩታል?

ዶ/ር ዳኛቸው፡- ከዚህ በፊት ሰምቼ ነበር፤ ሶስት ቦታ እንክፈለው የሚለውን፡፡ በዚያን ጊዜ ግን ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡ በአንድ ነገር ላይ ግን ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ አዲስ የሚመጣው ጠ/ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን ከዚህ በፊት የነበረው ጠ/ሚ የነበረውን ሃይል ክምችት ይዞ መቀጠል እንደማይችል ተነጋግረው ጨርሰዋል፡፡ ማን ጠ/ሚ ይሆናል የሚለው አይደለም ወሳኙ፤ ህወሓት አካባቢ ማን እየተሾመ ነው የሚል ነው ወሳኙ፡፡ አሁንም ቢሆን ምንም ወዲያና ወዲህ የለኝም፡፡
በእኔ ግምት ሕወሓት አሁንም ቢሆን ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ተቀምጧል – ጠ/ሚ ለመሆን፡፡ በሁለት መንገድ ነው እየሄዱ ያሉት፡፡ በውጭ ጉዳይም ትክክለኛ የስልጣን ቅብብል ነው የሚባለው ጉዳይ አሁን ጥያቄ ውስጥ የገባ መሰለኝ፡፡

ህወሓት ከያዘው ቁልፍ የሚኒስቴር መ/ቤቶች ስልጣን አኳያ ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ ሊሆን የሚችለውን ለመገመት ስንሞክር አመራሩ እንደ ዱላ ቅብብል ነው የሚባለው ጥያቄ ውስጥ የገባ ይመስለኛል፡፡ ወሳኝ ወሳኝ ቦታዎችን ወስደዋል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሄዷል፤ እዛው ተመልሶ ቦታው ገብቷል፡፡ ወሳኝ የሚባለው የፋይናንስና ኢኮኖሚው ሄዷል፤ ተመልሶ ቦታው ገብቷል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የጠ/ሚኒስትርነት ስልጣኑ (ቢሮ) የተጠናከረ ነውና ለሶስት መክፈል አለብን የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር፡፡
በጊዜው ያ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ የጠ/ሚ ቦታ ከህወሓት እጅ ከወጣ የህወሓት የበላይነት ያከትማል የሚል ስጋት ነበራቸው፡፡ አሁን እንግዲህ አንድ ጠ/ሚኒስትርና ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች አሉን ማለት ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ደግሞ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በክላስተር ተከፋፍለው አስተባባሪነት ተሾሞባቸዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ መተያየት ያለበት ማንኛውም ለየትኛው ክላስተር (ዘርፍ) በአስተባባሪነት እንደተመደበ ነው? ሽግሽግ ሲመጣ ሹመት ሲመጣ ህወሓት ተጠናክሮ እንደመጣ እንመለከታለን፡፡ ፋይናንስና ኢኮኖሚውን ዶ/ር ደብረጽዮን ያዘ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩን ዶ/ር ቴዎድሮስ ያዘ፤ በሶስተኛ ደረጃ መከላከያው የት ቦታ እንዳለ እናውቃለን፡፡ ይህንን ሁሉ የያዘ ፓርቲ የስልጣን ፍፁም የበላይነቱን ያዘ፣ ተቆጣጠረ ማለት ነው፡፡ ሕወሓት አካባቢ ማን ነው የበላይነት የያዘ የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡
ህወሓት ሁለት አመራሮቹን አጭቷል፤ ዶ/ር ደብረጽዮንና ዶ/ር ቴዎድሮስን፡፡ ከሶስት ዓመት በኋላ ስለጠ/ሚኒስትሩ ማንነት ስገምት ግምቴ ወደ ዶ/ር ደብረጽዮን ያደላል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ህወሓት ተደከመ፣ ሞተ የሚባለው ወሬ የተጋነነ ይመስለኛል፡፡
ታላቁ መሪያችን የፃፈውን እንተገብራለን ብለው የአሁኑን ጠ/ሚኒስትር በመሾም የመጀመሪያውን ፎርሙላ ካሳዩን በኋላ፣ በይደር ያስቀመጡት ሁለተኛው ፎርሙላ መሆኑ ነው የአሁኑ ለሶስት መካፈል – እኛ እስከምንዘጋጅ ነው ነገሩ፡፡ በዚህ ክፍፍል ለማን ምን እንደደረሰው አሁን ግልጽ የሆነ ይመስለኛል፡፡ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ከተቀመጠ በኋላ ሌሎች ሁለት ምክትሎች ከጐኑ ማሰለፍ የሚገርም ነው፡፡ አንዳንዶቹ ሰውዬው ልምድ ስለሚያንሳቸው ነው ይላሉ፡፡ መቼ እድል ተሰጠው፡፡ እስከ አሁንስ በመለስ ምስል አይደል እንዴ ያለነው፡፡

አቶ ሃይለማርያም መከላከያው፣ ደህንነቱ፣ ዲፕሎማሲው በጠ/ሚኒስትሩ ስር እንደሆነ ተናግረዋል? ይህማ እንዳልሆነ ሊሾሙ አራት ቀን ሲቀራቸው 37 ከፍተኛ መኮንኖች መሾማቸውን ሰምተናል፡፡ እነዚህን ከፍተኛ መኮንኖች ማሾም የነበረበት ማን ነው? ከዚህ አንፃር የህወሓት የበላይነት ተመልሷል ለሚሉት ቀድሞስ መች ጥያቄ ውስጥ ገባና እንላቸዋለን፡፡ አቶ ሃይለማርያም የካቢኔውን አደረጃጀት ሲያስረዱ፤ ከሌሎች በፓርላሜንታዊ ዲሞክራሲያዊ ሲስተም ከሚተዳደሩ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ከሚገኙት አገሮች የካቢኔ አወቃቀር የተወሰደ ልምድ እና የተካሄደ ጥናት እንዳለ ገልፀዋል … ይህ የተለመደ የኢህአዴግ ፊሊጥ (Modus Operandi) ነው፡፡ ከግሪክ አመጣነው ከግብጽ ወሰድነው ይላሉ፡፡ ሌጂቲሜሲ ለመመስረት የሚደረግ ነው፡፡

ESAT Tikuret Interview with Temesgen Dessalegn on current issues

Raw Video Footage: Government brutality in Ethiopia

Saturday, 1 December 2012

አዲሱ የስልጣን ክፍፍልና አመክንዮው

(በዳዊት ተሾመ)
 
 December 1, 2012
 
muktar debretsion tedros
እንደ መግቢያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን የካቢኒያቸውን ሽግሽግና አዲስ ተሿሚ ሚኒስትሮቻቸውን ትላንት (ህዳር 20፣ 2005 ዓ.ም) በፓርላማ በመገኘት አሹመዋል:: አዲሱ ካቢኔም ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትሮች ሲኖሩት የአራት ሚኒስቴሮችን ሽግሽግም ያካተት ነው:: የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሚኒሰቴር አቶ ጂነዲ ሳዶ ከሃላፊነት በማንሳት በአቶ ሙክታር ከድር ተተክተዋል:: የጤና ጠብቃ እና የንግድ ሚኒስትር ሚኒሰቴር ዲኤታ የነበሩት ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱና አቶ ከበደ ጫኔ  እንደየቅደምተከትል ለሚመሯቸው ተቋሞች ሚኒስቴር ሆነዋል:: የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

12-year-old video released: How Meles crushed his rivals Eyerusalem Araya December 1, 2012