Monday, 10 December 2012

የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥ ማነው?

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

በከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው ለረጅም ዓመት አገልግለዋል፤ ከዚያ ከለቀቁ በሁዋላ በጥብቅና ሙያ እየሰሩ ይገኛሉ። ታዋቂው የህግ ባለሙያ አነጋጋሪ በሆኑ የኢህአዴግ የፈጠራ ክሶች ዙሪያ ለተከሳሾች ጥብቅና በመቆምና በድፍረት በመሙዋገት ይታወቃሉ። በ1997 ከአንድ የፈጠራ ክስ ጋር በተያያዘ ለተከሳሾች ጥብቅና ቆመው ነበር፤ በፌደራል ጠ/ፍ/ቤት በተሰየሙ ዳኛ ተብዬዋች ተግባር ክፉኛ የተበሳጩት እኚህ የህግ ባለሙያ በወቅቱ እንዲህ አሉኝ፥ «በንጉሱ ዘመን ነው፤ በአ.አ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ልንመረቅ ሽር ጉድ እንላለን። የምንወደው የህግ መምህራችን የኛን ሁኔታ ታዝቦ ኖሮ…አንድ ጥያቄ አቀረበልን፤ “ አሁን ሳያችሁ በደስታ እንደተዋጣችሁ ነው፤ በመመረቃችሁ ደስተኛ ናችሁ ማለት ነው?... “ ሁላችንም በጥያቄው ተገርመን .. እንዴት መምህር?..በጣም ደስተኞች ነን ፤  አልነው። ደግሞ ጠየቀን ፥ “pሁላችሁም ደስተኞች ናችሁ?”..ሲለን.. አዎን ደስተኞች ነን አልነው በአንድ ድምፅ። በጣም አዝኖ እንዲህ አለን ፥  ``ሕግ በሌለበት አገር ህግ ተምራችሁ ..ሕግ የምታስፈፅሙ ይመስል፥ እንዲህ
መደሰታችሁና መመፃደቃችሁ ታሳዝናላችሁ.!… ``ዛሬ የበለጠ የመምህራችን ንግግር ታወሰኝ፤ እውነትም ሕግ በሌለበት አገር…»pሲሉ ታዋቂው የህግ ባለሙያ ያወጉኝን ለመጣጥፌ መንደርደሪያ ማስቀደሜ ያለምክንያት አይደለም።
   

Sunday, 9 December 2012

ውለታ የማታውቅ ሀገር

limenih tadesse

• ያ የኮሜዲ አውራ “እብድ” ተብሎ ጎዳና ላይ “ቆሼ” ይለቅማል!
• እርሱን ያፈራው ኅብረተሰብ የወደቀን ቀና ከማድረግ እንዳይቃና ይተጋል
• ስለዚህ ኅብረተሰቡ እንደ ድመት የራሱን ልጆች ይበላል!
ይኸውልህ ወዳጄ የተመለከትኩትን፣ የታዘብኩትን እና ያስተዋልኩትን እንደወረደ ላጫውትህ፡፡ ያ ጉምቱ የጥበብ ሰው፣ ያ የኮሜዲ-የጭውውት አውራ፣ ያ ጥበብን የተቀባው ባለትልቅ ተሰጥዖው ሰው፣ ያ ከሥነ-ሠብዕ ጥበብ ተሻግሮ የአዕዋፋትን ዝማሬ ምስጢር፣ የንፋስን ሿሿታ፣ የበር-መስኮት ሲጥሲጥታ ሳይቀር በጥበብ ሥራው ላይ አክሎ የሚከውንልህ ተዋናይ ልመንህ ታደሠ፣ ከፒያሳ ወረድ ብሎ ከሚገኘው ቢስ መብራት አደባባይ ላይ፣ እንደ ማንም ቆሼ ሲለቅም ተመለከትኩት፡፡

ልመንህን ያየ፣ እኔን-አንተን አየ፤ እኔን-አንተን ያየ ኅብረተሰቡን አየ፤ ኅብረተሰቡን ያየ-ተቋማቱን አየ ነው እያልኩህ ያለሁት ወዳጄ፡፡
ያ የጥበብ አውራ ልመንህ ታደሰ ሰውነቱ ገርጥቶ፣ የማይቀይራትን ጥቁር ሰማያዊ ወይም ጥቁር ሱፍ በውሃ ሰማያዊ ሸሚዝ አጥልቆ፣ የተጨራመተች ልሙጥ ጥቁር ቆዳ ጫማ ተጫምቶ፣ እንደ ባይንደር መሳይ ነገር ላይ የተጨረማመቱ ቡጭቅጫቂ ወረቀቶችን ይዞ የሥነ ሥዕል ንድፍ እንደሚሰራ ጀማሪ ሰዓሊ ከአደባባይ ሆኖ ድምም-ፍዝዝ ይላል፤ በጀርባው ባነገተው ጥቁር ቦርሳ /ኮሮጆ/ አንዳች ነገሮችን ሸክፏል፡፡ ልመንህ ታደሠ ተርቦም ሊሆን ይችላል-ማን ያውቃል?

Parrot H/Desalign Says There Are No Political Prisoners in Ethiopia

ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለምታደርገው የእግር ኳስ ጨዋታ ቦታ እንዲለወጥ መጠየቁን አላውቅም አሉ

ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይህን የተናገሩት ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። ረዩተር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መላኩ አየለን በመጠቀስ ” ለተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እግር ኳስ ፌደሬሽኑ የጨዋታው ቦታ እንዲቀየር መጠየቁን ” ዘግቦ ነበር። ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንም ለጉዳዩ የዜና ሽፋን መስጠታቸው ይታወቃል።

በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ጨዋታ መሰረዙዋን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መግለጹን ረዩተር ከትናንት በስቲያ ዘግቧል።


እነዚህ ዘገባዎች በስፋት በመገናኛ ብዙሀን በቀረቡበት ሁኔታ ነው፣ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ” ከኤርትራ ጋር ወዳጅነት ከፈለጋችሁ ለምን ከኤርትራ ጋር ለምታደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ የመጫዎቻ ቦታው እንዲቀየር ፈለጋችሁ?” በሚል ለቀረበላቸው ድንገተኛ ጥያቄ በመደናገጥ መረጃ የለኝም ሲሉ መለስ የሰጡት።

Saturday, 8 December 2012

`Land Grab` Deals Hurt Local Farmers: UN

Controversial farmland deals in developing countries can have a negative impact on the people who live on the land, according to a new U.N. report

While investment in agriculture is essential to help developing countries reduce hunger and poverty, the U.N. Food and Agriculture Organization says these large-scale “land grabs” don’t always help. The surging global demand for food, fodder and fuel crops is driving a land rush in parts of the developing world. Investors are pouring money into large-scale farmland leases in Africa, Asia, former Soviet countries and elsewhere. 

Well-known patriot Shambel Zewdu Ayalew joins ENTC

http://www.ethiopianreview.com/2011/shabel-zewdu-araya_115153.jpg
 A great Ethiopian patriot Shambel Zewdu Ayalew joins the Ethiopian National Transitional Council (ENTC) as an adviser.

Shambel Zewdu was elected as a member of Ethiopian parliament representing Gondar in 2005, but when the Woyanne junta stole the election, he refused to join the parliament and went into the bushes to fight for the Ethiopian people’s right to choose their own government through the ballot box. In that regard, he is an authentic Ethiopian hero and patriot who stood firm on his principles and paid enormous personal sacrifices while others betrayed their people for crumbs.

Last month, Shambel Zewdu arrived in Uganda and he is now assisting ENTC with building its organizational structure inside Ethiopia and neighboring countries, according to the ENCT leadership.
ENTC has also revealed that it will convene its second general assembly in the first week of this coming February and that preparations are currently underway.

በአንዋር መስጊድ ዛሬም የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋቡ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እስላም ኢትዮጵያውያን በታላቁ የአንዋር መስገድ በመገኘት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እየተከተለ ያለውን ፖሊሲ አምርረው ተቃውመዋል።
ምእመናኑ 27 ቁጥር የተጻፈበት ወረቀት በማውለብለብ ” አንቀጹ ይከበር፣ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፣ አሸባሪዎች አይደለንም” በማለት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ተሰምቷል።

ምእመናኑ 27 ቁጥር በመያዝ ተቃውሞአቸውን ያስተጋቡት በህገመንግስቱ በአንቀጽ 27 ላይ የተደነነገገው የሀይማኖት እኩልነት መብት ይከበር በማለት ነው።
አዲሱ መንግስት የመለስ መንግስት ይከተለው የነበረውን ችግሮችን በሀይል የመፍታት ዘዴ መከተሉ፣ ከኢትዮጵያውያን አልፎ በጸረ ሽብር ትግሉ ወዳጅ ተደርጋ የምትታየዋን አሜሪካ ሳይቀር እያሳሰበ የመጣ ጉዳይ ሆኗል።

በእስር ላይ በሚገኙት የኮሚቴ አባላት ላይ የሚታየው የተንዛዛ የፍርድ ሄደትና በአባላኦቹ ላይ በእስር ቤት የፈጸመው አሰቃቂ እርምጃ ምእመኑን ማበሳጨቱን ወኪላችን ከአዲስ አበባ ዘግቧል።