Wednesday, 6 February 2013
እኛ ስለ ሰላም እንዘምራለን፤ መንግስት ግን ዛሬም ስለ ሽብር ይናገራል
ኢቴቪና ብሔራዊ ፌዝ
‹‹ፊልሙ›› ላነሳቸው ሃሳቦች ምላሽ የሚሰጥ የድምጽ ማብራሪያ ነገ እንለቃለን
ዛሬ የመሪዎቻችንን ጉዳይ በሚያየው አራተኛ ወንጀል ችሎት እግድ ተሰጥቶበት የነበረው ‹‹ፊልም›› በሕግ ወጥ
መንገድ በኢቴቪ ተላልፏል፡፡ ‹‹ፊልሙ›› እንደለመደው ላለፈው አንድ አመት መንግስት ሲያደረግ የነበረውን የሙስሊሙን
ማህበረሰብ ሰላማዊ ትግል እና ተመራጭ የኮሚቴ አባላትን በሽብርተኝነት እና አክራሪነት የመወንጀል አባዜ በስፋት
ሲያራምድ ነበር፡፡ ‹‹ፊልሙ›› ደጋግሞ የሙስሊሙን ማኅብረሰብ ጥያቄና የትግሉን መሪዎች ሽብርተኞች፣ የብዛ
ሃይማኖቶችና ብሄሮች በሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሚሹ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላም
ለማናጋት ተልእኮ የተሰጣቸው፣ ለዚህም ከውጪ ስልጠናዎችን ወስደዋል እና ሌሎችንም ሀረጎች በመጠቀም ሲወነጅላቸው
አምሽቷል፡፡ የህግ የበላይነት ምሶሶ የሚባለው የተጠርጣሪዎችን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ነጻ ሆኖ የመገመት
(Presumption of innocence) መብትም ዛሬ በግልጽ ሲጣስ ተመልክተናል፡፡
የህወሃት መሪዎች “የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መፃፍ አለበት!” ይላሉ:: ለምን?
ገብረመድህን አርአያ
ህወሃት ከጥንሥሱ ጀምሮ እንደተልዕኮ እና መመሪያው ለዘመናት ከብዙ የውጭ ወረራዎች እና ያልተሳኩ የቅኝ ግዛት
ጥረቶች በአባቶቻችን ጽኑ ተጋድሎ የቆየውን ኢትዮጵያዊነት ለማፍረስ ፤ ህዝብን በአለም ታይቶ በማይታወቅ የቋንቋ እና
የዘር ልዩነት ከፋፍሎ ለብቻው የትግራይን ሪፖብሊክ ለማቋቋም ፤ ኤርትራን መገንጠል ፤ ትግራይን ከአማራ ቅኝ
ገዢዎች ነጻ ማውጣት ፤ ኢትዮጵያ የምትባል በአጼ ምኒሊክ የተፈጠረችን አገር ከአለም ካርታ ላይ ማጥፋት ፤ የሚሉ
እና ሌሎች ዝርዝር ግቦችን እና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ድርጅት እንደነበር ባለፉት በርካታ አመታት እኔ በግሌ
ስገልጽ እና ሳስረዳ ህወሃትም አንዳንድ ጊዜ በግልጽ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በግብር ይህንን እኩይ ምግባሩን ሲያሳየን
ቆይቷል:: ይኸው ኢትዮጵያዊነትን ከፊት በመሆን ከውጪ ወራሪዎች በጽናት ተጋድሎ አቆይቷል ብሎ የሚወነጅለውን የአማራ
ብሄርን የተመቸው ሲመስለው ከ1971 አንስቶ በቀጥታ በሰሜን ጎንደር በወልቃይት ፣ በጠገዴ ፣ በጸለምት እንዲሁም
በሚቆጣጠራቸው የትግራይ ቦታዎች እንዳደረገው በዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ፤ ሳይመቸው ሲቀር ደግሞ በተላላኪዎቹ
አማካይነት በጉራ ፈርዳ እንዳደረገው ከአካባቢው አማራን የማጽዳት ስራ ሲያደርግ ይኸው ብዙ አመታት ተቆጠሩ::
Tuesday, 5 February 2013
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ሳስበው!
ቅዱስ-ሃብት በላቸው ከደቡብ አውስትራሊያ
«ልጆቼን ከተወለዱ ጀምሮ ለ20 ቀናት ያህል ስለያቸው ይህ የመጀመሪያዬ ነው። ለዚህ ብርታት እና ፅናት እንዲሆነኝ ግን ዘወትር ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አስበዋለሁ። የእስክንድር
ልጅ የተወለደው አሁን እርሱ የሚገኝበት እስር ቤት ውስጥ ነው። የሕወሃት ደጋፊዎች ይህንን ሕዝብ ከደርግ ገላገለው እያሉ የሚያደንቁት ስርዓት እርጉዝ ሴት እስር ቤት ውስጥ እንድትወልድ ያደረገ ግፈኛ እንደሆነ ሁሉም ያውቃል። ይህም ሳይበቃቸው ልጁ አምስት ዓመት ሞልቶት እስክንድር ከትምህርት ቤት ሲመልሰው ነበር ድንገት ይዘውት የሚወደው አንድ ልጁ ፊት እጁን ወደኋላ የፊጥኝ አስረው በቪድዮ እየቀረጹ የወሰዱት፣ አሁን የርሱን ልጅና የኔን ልጆች ሳወዳድር የኔ ልጆች በምንም መለኪያ ከ20 ቀናት በኋላ እንደሚያዩኝ እርግጠኞች ናቸው። የእስክንድር ልጅ ግን አይችልም።»
(አርቲስት ታማኝ በየነ አድላይድ/ደቡብ አውስትራሊያ እ.ኤ.አ ጁላይ 2012 )
Monday, 4 February 2013
Ethiopia: They Shall Inherit the Wind
by Alemayehu G. Mariam
Kwame Nkrumah led the first sub-Saharan African country to gain independence from colonialism in 1957. Nkrumaism
sought to transform Ghana into a modern socialist state through
state-driven industrialization. He built the Akosombo Dam on the Volta
River, at the time considered the “largest single investment in the
economic development plans of Ghana”. He promoted the cult of
personality and was hailed as the “Messiah”, “Father of Ghana and Pan
Africanism” and “Father of African nationalism”.
The Sandcastles and Dams of African Dictators
All
dictators on the African continent have sought immortality by leaving a
legacy that will outlive them and endure for the ages. But all have
inherited the wind.
Subscribe to:
Posts (Atom)