Monday, 5 November 2012

Ethiopia: Government continues to target peaceful Muslim protest movement

AMNESTY INTERNATIONAL
November 03, 2012
Ethiopia mosque sit-ins see deaths, arrests: protestersThe Ethiopian authorities are committing human rights violations in response to the ongoing Muslim protest movement in the country. Large numbers of protestors have been arrested, many of whom remain in detention. There are also numerous reports of police using excessive force against peaceful demonstrators. Key figures within the movement have been charged with terrorism offences. Most of those arrested and charged appear to have been targeted solely because of their participation in a peaceful protest movement.

Sunday, 4 November 2012

ያለፉት ሃያ አንድ ዓመታት ፖለቲካ


በዶ/ር ዳኛቸው እይታ

በቅርቡ የተመሠረተውና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ጋር ሲወዛገብ ከቆየ በኋላ ባለፈው ሰኞ ሕጋዊ እውቅና ያገኘው ሰማያዊ ፓርቲ የተለያዩ ምሁራንን በመጋበዝ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማወያየት ጀምሯል። በተመሳሳይ ባለፈው እሑድ ሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን ጋብዞ ላለፉት 21 ዓመታት የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ዳኛቸው፤ የተለያዩ የፍልስፍና አስተምህሮቶችን በመጥቀስ የፖለቲካው ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የማብራሪያቸውን ማዕከላዊ ኀሳብ ለጋዜጣ በሚመች መልኩ ዘሪሁን ሙሉጌታ አዘጋጅቶታል።

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የዕለቱን ንግግራቸውን የጀመሩት በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የታወቀውን የሩስያ ሥነ ጽሑፍ ሰው አሌክሳንደር ኸርት ሰርን አባባል በማስቀደም ነበር። ይህ ጸሐፊ ‹‹ታሪክ ከውርስ የሚገኝ ማብቂያ የሌለው እብደት ነው›› ይል እንደነበርና ይህ ብቻ ሳይበቃም “ታሪክ የእብዶች ግለ-ታሪክ ነው” ማለቱን አስታውሰዋል። ለዚህ አባባሉም ምሳሌዎች ያቀርብ ነበር ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው፣ የፐርሺያ ጦር አቴንስን ሊይዝ ሲመጣ ካርቲዬስ የተባለው ጀግና ጦሩን ለማቆም ዘሎ ገደል ይገባል። ካርቲዬስ ገደል የሚገባው የዘመተበት ጦር ይቆማል በሚል እሳቤ ነበር። ኤፍጂኒያ ላይ ንጉሡ መርከቡ ከአቴንስ የባሕር ዳርቻ ለመልቀቅ ሲፈልግ ንፋስ ከሌለ ንፋስ እንዲመጣ በማሰብ የ13 ዓመት ሴት ልጁን ሰውቷል። ይህም እብደት ነው።
 


አትነሳም ወይ?!

እንዲህም አትሸማቀቅ! ግራ-ቀኝህን በጥርጣሬና በፍራቻ መቃኘትም አያሻህ! እረ አትገለማመጥ! እንዲህ መርበድበድ ምንድነው?
በቅድሚያ ጽሁፉን አንብበህ ጨርስና ከዚያ በኋላ የራስህን/የራስሽን አቋም ትወስዳለህ፡፡

 ጽሁፉን በሙሉ ሳታነብ ግን ቸኩለህ አትደምድም፡፡ ከስህተት ላይ ትወድቃለህና! የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳልና! የብዙዎቻችን ችግርስ ምን ሆነና?! ይኸው በወሬ እና በስሚ- ስሚ እየተፈታን ብሎም እየተነዳን አይደለ እንዴ በዘመናችን ሁሉ የተቀለደብን?! ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው! እንዲል ተረቱ፡ ፡ ስለዚህ “አንድን መጽሐፍ በሽፋኑ ብቻ አትፍረደው!” /Never Judge a book by its cover/ እንደሚባለው የፈረንጆቹ አባባል በርዕሱ ብቻ ተመርተህ የጽሑፉን ጭብጥ እንዳገኘኸው ሆኖ አይሰማህ፡፡ ርዕሱ ቁንጽል ሀይለ-ቃል ብቻ ነው፡፡ ቁም- ነገሩን በዝርዝሩ ውስጥ ነው የምታገኘው፡ ፡ “ሰይጣኑ ያለው በዝርዝሮቹ ውስጥ ነው” /The Devil is in the details/ ይላሉ ፈረንጆች ስለአንድ ጉዳይ አብጠርጥሮ ለማወቅ፤ ነገሩን በዝርዝር እና በጥሞና መመርመር እንደሚያስፈልግ ሲያስገነዝቡ፡ ፡ አለበለዚያ የአገራችን ቀደምት ሊቃውንት አዋቂ-መሳይ አላዋቂን እንደሚሰይሙት “ጥራዝ-ነጠቅ” መሆን ይከተላል፡፡ በጥራዝ- ነጠቅነት ደግሞ መፍትሄ አይገኝም፡ ፡ እንኳንና መፍትሄ ጉዳዩን በቅጡ መረዳትም አይኖርም፡፡ በመሆኑም ርዕስ አንጠልጥሎ ጭብጥ ጥሎ፤ የሚደረግ ውይይትና ንግግር አሊያም ገረፍ-ገረፍ ንባብ የባሰ መደናበር እና ግራ መጋባትን በማስከተል የጉዳዩን ውል ያሳጣናል፡፡ በዚህም ማናችንም አንጠቀምም፡፡
 

Saturday, 3 November 2012

Ethiopian journalist honored in Beverly Hills

(LOS ANGELES TIMES) — Reeyot Alemu missed an important dinner engagement in Beverly Hills. But she had a good excuse.
Reeyot Alemu
The 31-year-old journalist is jailed in the notoriously brutal, rodent-infested Kaliti prison in Addis Ababa, the capital of Ethiopia. She’s two years into a five-year sentence for daring to write about poverty, opposition politics and gender equality.
The dinner she missed Monday was the annual awards ceremony, at the Beverly Hills Hotel, for the International Women’s Media Foundation, which celebrates courageous women journalists.
This year’s honorees included Alemu, whose detention will be reviewed next week by Ethiopia’s highest court, organizers said. There’s only modest reason to be hopeful, although the attention of the award could put pressure on the regime.

Even from prison, Alemu declined to be silent.
“Shooting the people who march through the streets demanding freedom and democracy; jailing the opposition party leaders and journalists… preventing freedom of speech, association and the press; corruption and domination of one tribe are some of the bad doings of our government,” she wrote in accepting one of three courage awards.
“I know that I would pay the price for my courage and I was ready to accept that price,” she wrote.

በመከላከያ ሚኒስቴር የተፈጠረው ሽኩቻ እየበረታ ሄዷል (ከእየሩሳሌም አርአያ)

በመከላከያ ያለው ሽኩቻ እየበረታ ሄዶዋል። በጄ/ል ሳሞራ ትዕዛዝ የአየር ሓይል አዛዥ የነበሩት ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጎዋል። በምትካቸው ደግሞ ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ እንደሚቀመጡ ታውቓል። በቅርቡ የሜ/ጄኔራልነት ሹመት ያገኙት እና ወዲ ዘውዴ በሚል የሚጠሩት ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ ከበረሃ አንስቶ ከሳሞራ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ጠቁሜ ነበር። የሹመታቸው ምስጢሩ ሳሞራ ናቸው። ካኤርትራ የሚወለዱት ወዲ ዘውዴ ከሳሞራ ባለፈ ለመለስ ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ናችው። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት « ፈሪ» ተብለው እንደተገመገሙ ታማኝ ምንጮች አስታውሰዋል።

በአንጻሩ ጄ/ል ሞላ ወደ አየር ሃይል አዛዥነት ከመምጣታቸው በፊት የላቀ ጀብዱ እንደፈጸሙ ምንጮች ጠቁመዋል። በሻእቢያ ጦርነት ወቅት ኰ/ል ማእረግ የነበራቸው ሞላ በባድመ፡ አስመራ፡ ተሰኔ….በመሳሰሉ ከባድ ውጊያዎች ላይ የጦር ጄቶችን በማብረር ሻእቢያን ድባቅ የመቱ ኢትዮጵያዊ ጀግና ናቸው።

ከ72 በላይ ኢትዮጵያዊያንን የያዘ ጀልባ የመን ድንበር አቅራቢያ ሰመጠ

ግሩም ተ/ሀይማኖት 

      በአመት ከሁለት ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሞቱ IOM የገለፀበት ገልፍ ኦፍ አደን ባህረ ሰላጤ ላይ ከሶስት ቀን በፊት 72 ኢትዮጵያዊያን እንደሞቱ ተረጋገጠ፡፡ ከሶማሊያዋ ቦሳሶ ወደብ የተነሱ ሁለት ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎች ከነጫኑት ሰው ሰመጡ፡፡ በዚህ የመስመጥ አደጋ የሞተው ሰው ቁጥር በትክክል የማይታውቅ ሲሆን ለጊዜው ባህሩ ላይ ሬሳቸው የተለቀመ እና ባህሩ ዳር ተፍቶት የተገኘ ሲሆን ከዛ ውስጥ 72 ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ታውቋል፡፡ ሸቡዋ የተባለው የየመን ጠረፍ ላይ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው እንደሰመጠ የተነገረው ይህ ጀልባ ምን ህል ሰው እንደጫነ አልታወቀም፡፡ 
እኛ ስንጓዝ በምናውቀው ምን ጊዜም የሚጭኑት ከአንድ መቶ ላይ ሰው ነው፡፡ ሁለተኛው ጀልባ ይስመጥ አይስመጥ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ መግባታቸውም አልተረጋገጠም፡፡
    
 የየመን መንግስት ባለስልጣናት ከዚህ በኋላ በህገ-ወጥ መንገድ የሚገቡት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ይህንን አባባላቸውን 2011 መግቢያ ላይ ከጅቡቲ በጀልባ ሲገቡ በ3 ቀናት ልዩነት ሶስት ጀልባዎች ሲሰምጡ ተናግረውት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ተመሳሳይ ነገር ቢናገሩም ስደተኞችን ክፍት በተተወ ድንበር ህገ-ወጥ አጓጓዦች እንደልብ እያስገቡበት በመሆኑ በአመት እስከ 75 ሺህ ስደተኞች ወደ የመን እንደሚገቡ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት መግለጹ ይታወሳል፡፡ ይህ ችላ ባይነት በየመን መንግስትም ሆን በኢትዮጵያ መንግስት በመታየቱ ከባህር መስመጥ አልፈው የሚገቡት ኢትዮጵያዊያን ላይ በተደራጀ ሁኔታ የማፈን እና 5000 የኢትዮጵያ ብር ከቤተሰብ ማስላክ አለበለዚያ ታጋቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረስ የተለመደ ሆኗል፡፡
      
 ይህ ከሶማሊያዋ ቦሳሶ አነስተኛ ወደብ የሚነሳው የህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጀልባ አደጋው የደረሰበት በአየር መዛባት የተነሳ ሀይለኛ ንፋስ /ማዕበል/ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የዛሬ ሳምንት ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ በተከፈተ ተኩስ ሰዒድ የሚባል ኢትዮጵያዊ ህገ-ወጥ አጓጓዥ ጨምሮ ሶስት ኢትዮጵያዊያኖች መሞታቸው ታውቋል፡፡

Friday, 2 November 2012

November “Ethiopian Election Massacre” Commemoration Month

We remember and respect those fellow Ethiopians who gave their lives for their right to vote and for their vote to be counted.

Ethiopian Election Massacre Commemoration Month

On May 15, 2005, over 26 million Ethiopians voted peacefully to elect their leaders. As the results started to come in, showing a landslide victory for the opposition party, Meles Zenawi went on TV and declared a state of emergency. He also ordered re-votes in several districts where members of his party went down in defeat, banned political rallies, and unleashed his killers against peaceful citizens who protested his attempt to steal the election.
When the Addis Ababa Police showed restraint, Meles ordered all of them to be disarmed, and gave the Federal Police and his personal army, the Agazi, a shoot-to-kill order.

The Agazi and Federal Police snipers from roof tops and military trucks gunned down young, hundreds of unarmed protesters with 50 caliber rifles. Over 50,000 students and other individuals were rounded up and sent to concentration camps in remote parts of the country. All senior members of the opposition CUD were arrested. All the private press were shut down. The 2005 election massacre was one of the darkest moments in the history of Ethiopia.