Saturday, 8 December 2012

በጂዳ የብአዴን ዝግጅት ላይ የተገኙ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተባረሩ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) 32ኛ አመት ለማክበር አርብ ምሽት በጅዳና በአካባቢዋ በተዘጋጀ ዝግጅት ለመሳተፍ የሄዱ በርካታ ነዋሪዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውንና ስብሰባው በጊዜ መበተኑን ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ገልጿል።

ዛሬ በተጠራው የብአዴን ዝግጅት ላይ የተቃውሞ ድምጻችን እናሰማለን በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወረቀት በህቡዕ የበተኑ ሲሆን፤ በስብሰባው ላይ ተቃውሞ እንዳያካሂዱ በሚል ፍራቻ ጥሪ የተደረገላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ከስብሰባው ውስጥ እየተጠሩ እንዲባረሩ መደረጉን ነዋሪዎች ለነቢዩ ሲራክ ገልጸውለታል።
ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መንገድ መታዎቂያ አሳዩ የሚል ምክንያት ለመስጠት የተሞከረ ቢሆንም፤ መታወቂያ ይዘው የተጠረጠሩና የተፈሩ አንዳንድ ነዋሪዎችም ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ እንደተደረጉ ታውቋል፡፡

የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በባንዴራ አጅበው ከኮታቸው ላይ የለጠፉ የብአዴን አባላት ነዋሪዎችን በጥርጣሬ አንዳይገቡ ሲከለከሉና የፈለጓቸውን እየመረጡ ሲያስገቡ እንደታዘበ ነቢዩ ሲራክ ከስፍራው ዘግቧል።
ከመግቢያው በር ያሉትን የሳውዲ ልዩ ኮማንዶ ወታደሮችን ያናገረው ነቢዩ ሲራክ፤  ”የቆንስሉ ሃላፊዎች ማንም እንዳይገባ ከልክሉ ብለውናል” በማለት እንዳስረዱትና ነዋሪውን በማግባባት ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ሲማጸኑ እንደተመከተም ገልጿል።
የብአዴን አባላት እገዳው የተደረገው በጸጥታ ምክንያት እንደሆነና ጋዜጠኞችን ጨምሮ የተጠረጠሩና የማይታወቁ ሰወች እንዳይገቡ እገዳ መጣሉን ገልጸዋል።

አንዳንድ የብአዴን አባላት በጥሪ የመጡትንም እያንጓጠጡ ያስወጧቸው ሲሆን፤ ስብሰባው ያለወትሮው በጊዜ ሲጠናቀቅ ከስብሰባው የወጡ አንዳንድ ሰዎች ሲገቡ ችግር እንደገጠማቸውና በስብሰባው ላይ ምንም አይነት ፎቶም ሆነ ቪዲዮ እንዳይነሳ ቁጥጥር መደረጉንና ስብሰባው በተቃውሞና ፍራቻ ሲናጥ ማምሸቱን እንደገለጹለት ነቢዩ ሲራክ ከጂዳ ገልጿል።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለሕዝብና ለመንግስት ጥሪ አደረጉ

ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ መንግስት ሕገ መንግስቱን እንዲያከብር፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ሕገ-መንግስታዊ መብቱ እንዲከበር እንዲታገል ጥሪ አደረጉ።

ዶ/ር ነጋሶ ዛሬ አርብ ህዳር 28 ቀን ከኢሳት ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባደረጉት ቃለምልልስ፤ ኢህአዴግ ከጥቂት አመታት ወዲህ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እያለ የሚጠራው ህዳር 29 ቀን፤ በዋንኛነት ሕገመንግስቱ የጸደቀበት ቀን እንደሆነ በማስታወስ፤ ኢህአዴግ ቆም ብሎ በማሰብ የህገ መንግስቱን የሰብአዊ መብት አንቀጾች እንዲያከብርና እንዲያስከብር አሳስበዋል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ሕገ መንግስቱ በሚረቀቅበትም ግዜ ይሁን በሚጸድቅበት ግዜ ስህተቶች እንደተሰሩ አስታውሰው፤ ህገ መንግስት የማይለወጥ የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል ስላልሆነ፤ ኢህአዴግ ህገመንግስቱን እንዲያሻሽልም ጠይቀዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት፤ የገዢውን ፓርቲ የአምባገነንት ባህርይ በመተንተን፤ ገዢው ፓርቲ “ተገዶ እንጂ በልመናና በመለማመጥ በፈቃደኝነት በህዝብ የሚፈለገውን ለውጥ እንደማያመጣ” ገልጸው የጻፉትና ህዝቡም የተበታተነ ብሶቱንና ምሬቱን ወደአመጽና እምቢተኝነት መለወጥ እንዳልቻለ የተቹት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ሀሳባቸውን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ውይይት አብራርተዋል።

ከህዝቡ ምሬት ወደ አመጽ ያለማደግ ሁኔታ ጋር በተያያዘም ምክንያቱ የተለያዩ እንደሆነ ገልጸው፤ በተለይም ከምርጫ 97 በፊትም በሁዋላም ኢህአዴግ በህዝቡ ላይ ባደረሰው የጭካኔ ጥቃት ምክንያት በህዝቡ ላይ የፍርሀት ድባብ ሰፍኖ እንደሆነ ተናግረው፤ ህዝቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይጠብቅ፤ መብቱን ለማስከበር መስራት አለበት ብለዋል።

Friday, 7 December 2012

Denmark family adopted Masho and Roba Ethiopian kids touching story

በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ አረብ አገራት በብዛት በመሰደድ ላይ ናቸው


ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት በሰሜን ወሎ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉት ክፍሎች ውስጥ 44 ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው
ወደ አረብ አገራት ሄደዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ፓስፖርት በማውጣት ጉዞአቸውን እየተጠባበቁ ነው። መምህራንም እንደ ተማሪዎች የሚሰደዱ መሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል። መንግስት መምህራንን በመሰብሰብ ለማወያየት ሙከራ አድርጓል።

መንግስት የችግሩን ምንጭ ፈልጎ እንደማግኘትና መፍትሄ እንደመፈለግ በመምህራን ላይ ማሳበብን መርጧል። የመንግስት አቋም መምህራን ወደ አረብ አገራት ስለሚደረገው ስደት በቂ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ለተማሪዎች አልሰጡም የሚል ሲሆን፣ የመምህራን አቋም ደግሞ ” ተማሪዎች የሚሰደዱት ተስፋ በማጣታቸው ነው” የሚል ነው ።

 እድሉ ቢገኝ ከአገሪቱ ህዝብ 40 በመቶው አገሩን ጥሎ ለመሰደድ ፍላጎት እንዳለው በውጭ አገር የተደረገ አንድ ጥናት ከአመት በፊት ማመላከቱ ይታወሳል።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያውያን በየመን የባህር ሰላጤ እንዲሁም በሰሀራ በረሀ የውሀ ሽታ ሆነው መቅረታቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በተደጋጋሚ መዘገባቸው ይታወሳል።

ESAT Yesamintu Engeda Ato Temesgen Zewde December 2012.

Ethiopia’s Anti-Terrorism Law Squelches Opposition, Activists Say

BY BLAIN BISET, 6 DECEMBER 2012

Addis Ababa — Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation is once again stirring debate in this Horn of Africa nation as lawyer Temam Ababulga challenges the 2009 law in the highly-publicised “Muslim terrorism” case.
Ethiopia’s Federal High Court will deliver the judgment in the case, where 29 Muslims were arrested in July on charges of terrorism, on Thursday Dec. 6.

Ethiopia has had Muslim demonstrations since the beginning of the year, as members of the religious community have protested against what they say is government interference in their religious affairs. Around one-third of the 84 million people in this predominantly Christian nation are Muslim.