Friday 9 November 2012

እነ አቶ አንዱለም አራጌ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጥቅምት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሽብርተንነት ወንጀል ተከከሰው ብግፍ እስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ሌላው የአመራር አባል አቶ ናትናኤል መኮንን እንዲሁም የመኢዴፓ የአመራር አባል የሆነው አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ የይግባኝ አቡቱታቸውን ለማቅርብ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ዳኞቹ ለህዳር 13 ቀን 2005 ዓም ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱን አሰናብተዋል።

የፍርድ ሂደቱን በተመለከተ ችሎቱን የተከታተሉትን አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበርና የቀድሞው የኢትዮጵአ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የእስረኞች መንፈስ ጠንካራ እንደነበር ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በግፍ ያሰራቸውን የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈታ በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና መንግስታት ቢጠየቅም እስካሁንም አሻፈረን እንዳለ ነው።

No comments:

Post a Comment