Sunday 13 October 2013

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው

sebehat nega one of the founders of TPLF

October 13, 2013

ከኢየሩሳሌም አርአያ
በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከአንድ ሰአት በፊት ስብሃት ነጋና አብሯቸው የነበረ ግለሰብ በአንድ ኢትዮጲያዊ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመው ማምለጣቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። 

መስፍን የተባለው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን የሲቪሊቲ ሩም ፓልቶክ አዘጋጅ አባ መላ በስልክ አግኝቶት ስለሁኔታው ያነጋገረው ሲሆን፤ መስፍን እንደገለፀው በድብደባው ጅርባው እንደተጎዳና ብዙ ደም እንደፈሰሰው ገፆዋል። እነስብሃት ድብደባውን ሲፈፅሙ በቅርብ ርቀት ቪዲዮ እየተቀረፁ እንደነበረና ይህኑን ማስረጃ ለፖሊስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ በአካባቢው ፈጥኖ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁን ሰአት እነስብሃትን ለመያዝ ፖሊስ መሰማራቱ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment