Tuesday, 1 January 2013

ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው

በዮሐንስ አንበርብር
 
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱትን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡
የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ጁነዲን በፓርላማ የሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት ሊጠየቁበት የሚችል የሕግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል፣ በምክር ቤት አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ምክር ቤቱ እንዲያነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ በመንግሥት ቀርቧል፡፡ ጥያቄው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ወይም በፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በኩል መቅረብ ያለበት መሆኑን የምክር ቤቱ ደንብ ያዛል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች፣ ጥያቄው በየትኛው አካል መቅረቡን ለመረዳት እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ላይ ሚስጥራዊ ያሉዋቸውን ሰነዶች ይፋ አደረጉ

 በየማነ ናግሽ

-    የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የኢሕአዴግ ዕጩ ሆነው የተወዳደሩበትን ሰነድ አቀረቡ
-    የምርጫ አስፈጻሚዎች ለኢሕአዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈሉበት ሰነድ አለን ይላሉ
-    አንድ ለአምስት አደረጃጀት ለምርጫ ቅስቀሳ እየዋለ ነው በማለት ኮነኑ
 
መድረክንና መኢአድን ጨምሮ ዋነኛ ተቃዋሚዎች የተሰባሰቡበት 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ጊዜያዊ ኮሚቴ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ለፓርላማው አፈ ጉባዔ ክስ እንደመሠረቱበት ገልጸው፣ አገኘናቸው ያሉዋቸውን አንዳንድ ሚስጥራዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ፡፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ግንባር (መድረክ) ጽሕፈት ቤት የፓርቲዎቹ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባለፈው ሐሙስ ለአገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አንዳንድ ሚስጥራዊ ያላቸውን ሾልከው የወጡ ሰነዶችን ይፋ በማድረግ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት ለቅሬታቸው ማስረጃ የላቸውም ማለቱን አስተባብለዋል፡፡

በኩዌት በሳዑዲ ዓረቢያና ጅዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰው ኃይልን በርካሽ ዋጋ ሊያቀርብ እንደሚችል በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያው እያስነገረ ነው፡፡

by Hellen Zewdu Ayele  
 
ሰው በፈለገበት ቦታና አገር የመዘዋወር መብቱ በሕገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በኮንትራት በቤት ሠራተኝነት ወደ አረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይሰማል። ኢትዮጵያውያኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እየደረሰ ነው። ለዚህም በዋነኛነት ማሳያ የሚሆነው በተለያዩ የዓረብ አገሮች በቤት ሠራተኛነት በሚሄዱት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የመደፈርና ያለደመወዝ ማባረር ጥቂቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት እንኳን ከዓለም ደቻሳ ጀምሮ በድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የተዳረጉትን የተደፈሩትን ከፎቅ የተወረወሩትን ለአእምሮ መቃወስ የተዳረጉት የትየለሌ ናቸው ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪወቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ በዝርዝር እየዘገቡት ነው፡፡

የመለስ ራዕይ የሚባል ነገር የለም ሲል ስብሐት ነጋ ተናገረ፣ በአዲስ አበባ መለስን የሚያወድሱ ፖስተሮች እየተነሱ መሆናቸው ታወቀ

አንጋፋዉ የህወሀት መስራችና መሪ ስብሐት ነጋ የመለስ ራዕይ የሚባለው ነገር ትክክል እንዳልሆነና የወያኔ ራዕይ የጋራ ራዕይ መሆኑን በያዝነዉ ሳምንት አጋማሽ  አዲስ አበባ ዉስጥ ለንባብ ለበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጠዉ ቃለ ምልልስ መናገሩን የአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ። ስብሐት ነጋ ይህንን የተናገረዉ ብዙዎችን ግራ ያጋባዉንና በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔ አገዛዝ የሰጠዉን የሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት አስመልከቶ የቀረበለተን ጥያቄ ሲመልስ ነዉ። ስብሐት ነጋ እሱ እራሱ በፈጠረዉ ህወሀት ዉስጥ ይህ ነዉ ተብሎ የሚነገር ስልጣን ባይኖረዉም ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ግን ህወሀት ዉስት በተፈጠረዉ የመሪ እጦትና አለመተማማን የተነሳ ተደማጭነቱ እየጎላ መጥቷል። በቅርቡ በየመገናኛ አዉታሩ አንደተስተዋለዉ ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በነበሩት ሁለትና  ሦስት ወራት ከፍተኛ ተሰሚነት ነበረዉ በረከት ስምኦን ድምጹ እየጠፋ ስብሐት ነጋ የኮከብ ተዋናይነቱን ቦታ እየያዘ መምጣቱ ይታወቃል።

ESAT Tikuret Dr. Birhanu Nega December 2012 Ethiopia

ሰብአዊ መብት ለሰብአዊያን – ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
 

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

 በዓለም ዙርያ ያሉትን አንባቢዎቼን 2013 የደስታና የብልጽጋና ዓመት ይሁንላችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
Every human has rights prof. Alemayehu G. Mariamላለፉት ያልተቋረጡ 300 ሳምንታት ያህል ጦማሮቼን ለተከታተሉ ሁሉ፤ከልብ የመነጨ አክብሮቴንና ምስጋናዬን እገልጻለሁ፡፡ ከኢትዮጵያና ከዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ለተቸረኝ ማበረታታት ምስጋናዬ ይድረስልኝ፡፡
አንባቢዎቼን፤ በኢትዮጵያና በዓለም ላይ ሁሉ የተደፈሩ ሰብአዊ መብቶችን ለሁሉም ሰብአዊ ፍጡራን እንዲዳረሱና እንዲከበሩ የመጠራሪያና የማንቂያ ደወል በአፍሪካና በዓለማቱ ሁሉ እንደውል እላለሁ፡፡ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ አንዳሉት “በማይበጠስ የአንድነት ሰባዊ ሰንሰለት ተሳስረናል፡፡ በአንድ አይነት እጣ ፈንታ ተያይዘናል:: አንዱን በቀጥታ የሚያጠቃው ሌላውንም በተዘዋዋሪ ደግሞ አይተወውም፡፡

ኦሮሚያ ዉስጥ ዳኞች በብዛት ስራቸዉን እየለቀቁ መሆኑ ተነገረ

ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ በተለያየ ደረጃ በዳኝነት ስራ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ስራችንን ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል በብዛት ስራቸዉን እየለቀቁ መሆኑን ከወደ አሮሚያ የሚደርሱን ዜናዎች ያስረዳሉ። ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ በዳኝነት ስራ ላይ የሚያደርገዉን የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት በመቃወም ከ100 በላይ ዳኞች ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን በያዝነው አመት ደግሞ ይሀ ቁጥሩ በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ።