Thursday 30 January 2014

ጎንደር በቅስቀሳ ደምቃለች‬!!

የከተማው ነዋሪዎች የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች እና ትራፊት ፖሊሶች ላይ ጫና እያደረገ ነው::
ጸጥታ ሃይሎች ህዝቡን ችላ በማለት ቅስቃሾቹ ጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ቢታገቱም የጎንደር መስቀል አደባባይ በቅስቀሳ ወረቀቶች ተጥለቅልቋል::

ሰማያዊ ፓርቲ የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይን በተመለከተ የሕወሓት መራሹ መንግስት በጓዳ ከሱዳን መንግስት ጋር ተደራድሮ መሬታችንን አሳልፎ ሊሰጥ ስለሆነ ድምጻችንን እናሰማ በማለት በጎንደር ከተማ ለእሁድ ጥር 25 ለተጠራው ሰልፍ በጎንደር ቅስቀሳው የተጧጧፈ ሲሆን በጎንደር መስቀል አደባባይ ደማቅ ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው::

ጎንደር መስቀል አደባባይ ላይ የሰልፍ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በፖሊስ እንደታገቱ ምንጮቻችን ገለጹ፡፡የሹፌሩን መንጃ ፈቃድ የቀሙት ሲሆን ሲቪል የለበሱ ፖሊሶች ከሰልፍ አስተባባሪዎቹ ጎን በመሆን ሊታገቱ አይገባም እያሉ ይገኛሉ፡፡እንደ ፖሊሶቹ አባባል ከሆነ እነዚህ ሰዎች እየሰሩ ያሉት የሀገርን ዳር ድንበር የማስከበር ስራ ስለሆነ ምንም አይነት እክል ሊገጥማቸው አይገባም ባይ ናቸው፡፡በሌላ በኩል ያሉት ፖሊሶች ደግሞ በሞተር ሳይክል ዙሪያውን በመክበብ አላንቀሳቅስ እንዳሉአቸው ታውቋል፡፡

ይህንን ተከትሎ ቅስቀሳ የሚያደርገውን መኪና የጸጥታ ሃይሎች እና የትራፊክ ፖሊሶች በመተባበር ወደ እስር ቤት ሊወስዱት ቢሞክሩም ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ እና ሃገር አትክዱ ይህ የጋራ ጉዳይ ነው ከህዝብ ጋር አትጣሉ በማለት በፈጠረአ ጫና መኪናው በሰላም ቅስቀሳውን እንዲቀጥል ተደርጓል::

ተመልሰው የመጡት የጸጥታ ሃይሎች መኪናው ለማስለቀቅ የሞከረውን ህዝብ በመበተን በድጋሚ በቀስቃቾቹ ላይ በተወሰደው እርምጃ ሰብስበው ያሰሯቸው ሲሆን የጎንደር መስቀል አደባባይ በቅስቀሳ ወረቀቶ ተበትነው መንገዶቹን አጥለቅልቀዋል::በጸጥታ ሃይሎች እና ህዝብ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ህዝቡ ቀስቃሾቹን በመደገፍ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር እያለ በመዘመር በከፍተኛ ሁኔታ ድምጹን እያሰማ ነው:: 
 
ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment