Monday 13 January 2014

ታሪካዊ የተቃውሞ ድምጽ ጥሪ! ዳር ድንበር ሲቆረስ ዝም ብለን አናይም!

January 11, 2014

ጸረ ኢትዮጵያ የሆነዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አባቶቻችን በደማቸዉ አስከብረዉ ያቆዩትን ያገራችንን ዳር ድንበር ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል አሳልፎ እየሰጠ ያለ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነዉ። ሰሞኑን የሱዳኑን የአልበሺር ስርኣት ለማስደሰት እና ተባባሪው ለማድረግ ኢትዮጵያዊ ዜጎቻችንን ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው እያፈናቀለ 1200 ኪ.ሜ. የሚሆን የድንበር ክልል ለመለገስ እየተዘጋጀ ይገኛል።

 በመሆኑም ይህ ሀገርን የመሸጥ፤ የመክዳት ድርጊት በኢትዮጵያ ህዝብ እና በታሪክ ተቀባይነት እንደማይኖረው እንዲሁም ይዋል ይደር እንጂ ህዝባችን ይህን ዳር ድንበር እንደሚያስመልስ ለአለም ህብረተሰብ በዋናነትም ለሱዳን ህዝብ ለማሳወቅ በሱዳን ኤምባሲ በመቀጠልም በወያኔ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት የዜግነት ታሪካዊ ግዴታችንን እንወጣ። ድምጹን ማሰማት ለማይችለው ህዝባችን እና በግፍ ለሚፈናቀሉት ወግኖቻችን ድምጽ እንሁናቸው።
TPLF regime is to hand over legitimate Ethiopian territory to Sudan

No comments:

Post a Comment