Monday 6 May 2013

ህገመንግስቱን ማክበር ከገዢው ፓርቲ ይጀመር!!!

ሀገር ወዳድ መሆን እኮ ጦርነትን በሀገር ላይ ማሰብ አደለም፤ ሀገር ወዳድ እኮ መንግስት ህዝቡን ሲበድለው የራስን ኑሮ ደልቀቅ አድርጎ ማየት አደለም፤ ህዝብ ሲራብ ቆሞ ማየት አደለም፡፡ ምን አልባትም ችግርን አብሮ መጋፈጥ ትልቅ እሴት አለው

Monday, May 6, 2013

ህገመንግስቱን ማክበር ከገዢው ፓርቲ ይጀመር!!!
ምንሊክ ሳልሳዊ

ዞን 9 ኢ-መደበኛ የአራማጆች እና የጦማሪያን ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ የተለየ እና ወገናዊ ያልሆነ ታረክ ለመፍጠር እየሠራ የሚገኝ የወጣቶች ኢትዮጵያውያን በ2005 ዓ.ም ሊደረጉ ከታቀዱት አራት የበይነመረብ ዘመቻዎች ሦስተኛው የፊታችን ረቡዕ ሚያዝያ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ያካሂዳል::
ሶስተኛው የበይነ መረብ ዘመቻ "ዲሞክራሲን በተግባር እናውል፤ የሰላማዊ ሰልፍ መብታችን ይመለስ!" በሚል መሪ ቃል ይካሐዳል:: ሦስተኛው ዘመቻ መንግሥትን እና ሁላችንንም በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 30 የሰፈረውን ‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት እንድናከብር› የሚጠይቅ ነው፡፡
*********************************************************************
 በዚህ ጉዳይ ላይ የራሴን አጠር ያለ አስተያየት ማስቀመጥ ስላለብኝ ይህንን ለማለት እወዳለሁ::
በሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የዲሞክራሲ ጮራ እንዲፈነጥቅ በተለያዩ ጊዜያት የተነሱ ኢትዮጵያያን ላለፉት 21 አመታት የትግል አስታውጾ አድርገዋል:: እንዲሁም የኢሕኣዴግ ሰራዊት የተሰዋለት አላማም ይህንን የህዝቦች ነጻነት እና እኩልነት ለማረጋገጥ ነበር::በህዝቦች የትግል ሂደት እና መስእዋትነት ተረቆ ጸድቋል የተባልነው ህገመንግስት ግን ከዚህ በተለየ መልኩ የወረቀት ላይ ጀብደኛ ሲሆን በማንም መመሪያ እና የስልክ ቴዛዝ ሲሻር እየተመለከት ነው::
ህገመንግስቱ በወረቀት ላይ ብቻ ህይወት ሳይዘራበት በተድፈነፈነ መልኩ አስፈጻሚ አቶ በግለሰቦች ያውም የህግን ምንነት ባልተማሩ እንደፈቀደ እየተተረጎመ የዜጎችን ህልውና ከመፈታተን አልፎ ማንነትን እስከማሳጣት ድረስ ዘልቋል:: ህገመንግስት የማፈኛ መሳሪያ እንዲሁም የማሰሪያ የመወርወሪያ የመግደያ መሳሪያ ከመሆን አልፎ ጥልቅ አምባገነንነት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል:: ይህ ማለት ህገመንግስቱ በተግባር አለመተርጎሙ ይህንን ፈጥሯል ማለት ነው::
ማንኛውም በሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ዜጋ በህገመንግስት መናድ እና መጣስ ጉዳይ እየተከሰሰ ወደዘብጥያ ማውረድ የተለመድ የየእለት ተግባር ሆኗል:;ከ1997/2005 ምርጫ በኋላ ደሞ የባሰ በረቀቀ መንገድ አዲስ ህግ ወቶለት አሸባሪ በሚል ዉንጀላ ህገ መንግስቱ እስከመረሳት ደርሷል::
የሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሃገራችን ከተቀበለችው አለማቀፍ ድንጋጌዎች አንዱ ነው::ይህ ማለት ደሞ ሰዎች በማንኛውም ጊዜ የሚደግፉትንም ሆነ የሚቃወሙትን ጉዳይ በአደባብይ ወተው ድምጻቸውን ማሰማት ይችላሉ ማለት ነው :: ተረጋግጧል በተባለው  በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 30 የሰፈረውን ‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት እንድናከብር› በሚል ሰፍሮ ይገኛል::
ይህ አንቀጽ 30 ግን እንደ በላይ ህግ ሳይተይ ከ1997/2005 ጀምሮ በበታች ህጎች ተገድቦ ይገኛል:: የበላይ ህጎች የበታቾቹን በሚገድቡበት እንጅ የበታቾች የበላያቸውን በሚሸረሽሩበት ሂደት ዉስጥ አልም አልፋበት ባለማወቋ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዜጎቿን እያጣችበት እየተገፈፈችበት ነው::
የገዢው ፓርቲ እሱን ብቻ የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎችን እንዲደረጉ ከመፍቀድ ዉጪ የተቃውሞ ሰልፎችን በማኮላሸት ተቃዋሚዎችን ወደ እስር ቤት ያግዛል:: አሁን እንኳን በቅርቡ አለማቀፍ ማህበረሰብ የሚያወግዘው የፋሺስቱ ግራዚያኒን ሃውልት ግንባታ ለመቃወም የወጡ ዜጎች በጋራ ሃገራዊ ጉዳይ አብሮ መስራት የሚገባው ገዢው ፓርቲ ፖሊሶችን በማሰማራት አፍሶ ወደ እስር ቤት ወስዶ ካሰራቸው በሗላ ፈቷቸዋል :;ይህ የሚያሳየው እንግዲህ ምንን እንደሆነ እርሶው ይደምድሙት::
ስለዚህ  ይህንን የሰው ልጆች የማይገሰስ ህገመንግስታዊ መብት ገዢው ፓርቲ ማክበር ከራሱ እንዲጀምር እናሳስባለን::አመሰግናለሁ::ምንሊክ ሳልሳዊ
***************************************************************
ከዚህ በታች የምታነቡት የዞን 9 ሦስተኛው የበይነ መረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው::ዲሞክራሲን በተግባር እናውል፤ የሰላማዊ ሰልፍ መብታችን ይመለስ!
ሦስተኛው የበይነ መረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ

ዞን 9 ኢ-መደበኛ የአራማጆች እና የጦማሪያን ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ የተለየ እና ወገናዊ ያልሆነ ታረክ ለመፍጠር እየሠራ የሚገኝ የወጣቶች ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ ይህንን የምናደርግበት ዋና ዓላማ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቷ ጉዳይ ያገባኛል ብለው ውይይት የማድረግ ባሕል እንዲያሳድጉ በማድረግ ሀገሪቷን በሁሉም መስኮች ወደተሻለ ደረጃ የሚያደርሱ ሐሳቦች እንዲወለዱ ለማመቻቸት ነው፡፡

የተከበራችሁ የዞን9 ነዋሪዎች፣ በ2005 ዓ.ም ሊደረጉ ከታቀዱት አራት የበይነመረብ ዘመቻዎች ሦስተኛው የፊታችን ረቡዕ ሚያዝያ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡ ሦስተኛው ዘመቻ መንግሥትን እና ሁላችንንም በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 30 የሰፈረውን ‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት እንድናከብር› የሚጠይቅ ነው፡፡

ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ መብት ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ የተደረገለት ዜጎች ድጋፋቸውን ወይንም ተቃውሟቸውን ከመሰሎቻቸው ጋር በመሆን ሐሳባቸውን መግለጽ እንዲችሉ እና ያገባናል የሚሉት ጉዳይ ላይ ሐሳብ እዲለዋወጡ እና እንዲወያዩ ነው፡፡

የ1997 ዓ.ም ምርጫ ቅስቀሳ አካል የነበሩት የሚያዝያ 29 እና 30 ሰልፎች በኋላ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እና መሰብሰብ መብት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተወሰነ ጊዜ ተገድቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ከዛ በኋላ የተካሄዱ ጥቂት ሰላማዊ ሰልፎች የአንድ ወገን ሐሳብ የሚንጸባረቅባቸው እና ለዚያም ሲባል ይሁኝታን ያገኙ ብቻ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ ከሚያዝያ 30፣ 1997 ወዲህ ተቃውሞን አስመልክቶ የተደረገው ሰልፍ የወ/ት ብርቱካንን መታሰር አስመልክቶ የተካሄደ ሲሆን 250 ሰዎችን ብቻ ያሳተፈ ነበር፡፡ በወቅቱ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በሰልፉ ላይ ለሚኖረው የደህንነት ችግር ኃላፊነት እንዲወስዱ መጠየቃቸው የተሳታፊዎችን ቁጥር ለመቀነስ መገደዳቸው ይታወሳል፡፡

ፖለቲካዊ በሆኑ ጉዳች ዙሪያ የሚደረጉ ስብሰባዎችም ቢሆኑ በግልጽ ተአቅቦ ባይደረግባቸውም የተለያዩ አስተዳደራዊ ጫናዎችን በመፍጠር እንዳይካሄዱ የእጅ አዙር ክልከላ ይደረግባቸዋል፡፡ ከመንግሥት የእጅ አዙር ክልከላ ሲያልፍም የመሰብሰቢያ ቦታ አቅራቢዎች ከሚደርስባቸው ቅድመ ማስፈራራርያ ወይንም ይደርስብኛል ብለው ከሚያስቡት አስተዳደራዊ በደል የተነሳ መሰብሰቢያ አዳራሾችን ይከለክላሉ፡፡
የሦስተኛው ዘመቻ ዓላማ መሣሪያ ሳይዙ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ላይ የተጣሉ ቀጥተኛ እና የእጅ አዙር ገደቦች እንዲነሱ መጠየቅ ነው፡፡

ዘመቻው በዋነኛነት የሚካሄደው ‹‹ፌስቡክ›› እና ‹‹ትዊተርን›› (#Assembly4Every1 እና #Demonstration4Every1 የሚሉ ኃይለቃሎችን) በመጠቀም ይሆናል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብታችንን በተመለከተ የተለያዩ ጽሑፎች በጦማራችን የሚወጡ ሲሆን በፌስቡክ እና በትዊተርም ላይም ይለቀቃሉ፡፡ በሁለቱ (የዞን9 እና የሕገ-መንግሥቱ ይከበር!) የማኅበረሰብ ገጾች ላይ ለዚሁ ዘመቻ ሲባል የተዘጋጁ አጫጭር ጽሑፎች ይሰራጫሉ፡፡ ዘመቻውን የሚመለከት ‹ባነር› ተዘጋጅቶ ዘመቻው በሚቆይባቸው ቀናት የተለያዩ ፕሮፋይል ምስሎችም ተዘጋጅተው የሽፋን ምስል እና የፕሮፋይል ፎቶ ይሆናሉ፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ለመላው የዞን9 ነዋሪዎች እና በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት ተከብሮ ማየት ለምትፈልጉ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ጉዳዩ ላይ ያላችሁን አመለካከት፣ መብቱ የተጣሰባቸውን ክስተቶች በማካፈል በጉዳዩ ላይ በመወያየት እንዲሁም የፕሮፋይል ፎቷችሁን በመቀየር በዞን9 ጦማር እና በ‹ዞን9› እና ‹ሕገ-መንግሥቱ ይከበር› የፌስቡክ ገጾች የዘመቻው ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑ በትህትና እንጋብዛለን፡፡

ስለሚያገባን እንጦምራለን!!!
ዞን9

No comments:

Post a Comment