Sunday 26 May 2013

የሰማያዊ ሁለት አባሎች ጥቁር ልብስ ለምን ለበሳቹ በሚል በደህንነቶች ተይዘው ታሰሩ

ሰማያዊ ፓርቲ ከግንቦት 15 እስከ 17 /2005 ዓ.ም ጥቁር ልብስ የመልበስና ግንቦት 17/2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ፊለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ ጥቁር ልብስ ለምን ለበሳችሁ በማለት የፓርቲው የኦዲትና ኢንስፒክሽን አባል የሆነው ወጣት ሀብታሙ ደመቀና በነጋታው እርሱን ለመጠየቅ የሄደው ወጣት ራቅሊስ ካሣ መታሰራቸውን ፓርቲው ለማረጋገጥ ችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የፓርቲው አመራር እና አባላት በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመገኘት ታሳሪዎች እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን በቀጣይ የታሰሩ አባሎቻችን አስመልክቶ ሰማያዊ ፓርቲ የሚሰጠው መግለጫ ይኖራል፡፡

No comments:

Post a Comment