Tuesday 15 January 2013

ሰበር ዜና – 33ቱ ዋንኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫ ራሳቸውን ሊያገሉ ነው


Fnote Breaking Newsፍኖተ ነፃነት

33ቱ ፓርቲዎች ለምርጫ ቦርድ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው በመጪው የአዲስ አበባ እና የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ ላይ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን የፍኖተ ነፃነት የዜና ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ፓርቲዎቹ ነገ ጥር 7, 2005 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሚሰጡት መግለጫ ውሳኔያቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ  ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

መግለጫውን ከቦታው ከስር ከስር ፍኖተ ነፃነት ገጾች  ለማስተላለፍ ጥረት ይደረጋል፡፡የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አመራር አባለትን ለማሰር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመራሮቹ አጋለጡ


የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ ሰባሳቢ ወጣት ሀብታሙ አያልው ከፍኖተ ነፃነት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደጠቆመው መንግስት እሱን ጨምሮ የማህበሩን አመራሮች ለማሰር ዝግጅት እያደረገ እንዳለ መረጃ ደርሷቸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አዳራሽ ሊያደርጉት የነበረው መስራች ጉባኤም የማህበሩ አባላት ባልሆኑና ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰባች ከታወከና እንዲበተን ከተደረገ በኋላ  6 የማህበሩ አመራሮች እስከምሽቱ 12፡30 ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ወጣት ሀብታሙ ጨምሮ ገልጧል፡፡

No comments:

Post a Comment