Monday 14 January 2013

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ጉባኤ ተደናቀፈ

ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ዛሬ በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሊያካሂዱት የነበረው አመታዊ ጉባኤ ገዢው ፓርቲ አስርጎ ባስገባቸው ወጣቶች መደናቀፉን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል
 
በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴሎች ለማህበሩ አዳራሽ ለማከራየት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶቹ ጉባኤያቸውን በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ውስጥ ለማካሄድ ተገደው ነበር።
 
ይሁን እንጅ ዛሬ ጧት ስብሰባው በሚካሄድበት ወቅት የተወሰኑ ወጣቶች ስብሰባውን ማደናቀፋቸውንና ይህንኑ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ስፍራው በፍጥነት በመምጣት 6 የአመራ አባላትን ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ ቀኑን ሙሉ ካሰሩዋቸው በሁዋላ በዋስ እንደለቀቁዋቸው የወጣቶች ምክትል ፕሬዚዳንት ወጣት ሚካኤል ተናግራል።

No comments:

Post a Comment