አባ ሕዝቅኤልና በአዲስ አበባ የሚገኙት የሲኖዶስ አባለት ለእርቅና ለሰላም እንዲሁም ለሀያ ዓመታት የዘለቀውን የቤተ ክርስቲያን መለያየት ወደ አንድነት ለማምጣት በቅንነት እና ግልጽ በሆነ መንገድ ቢጓዙ ኖሮ ለዚህ ለከፋ መከፋፈል እንዲሁም ለመንግሥት ጣልቃ ገብነት ባልተዳረጉ ነበር ይልቁንም አባ ሕዝቅኤል የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አለ መባሉ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነና ቅዱስ ሲኖዶስ ለምርጫ የሚያስፈልጉ ደንቦችን ከማውጣት በቀር መንግሥት ጣልቃ አልገባም በማለት በአደባባይ ተናግረው ጸሐይ የሞቀውን እውነት የካዱ አባት ናቸው አቡነ ገብርኤልም ይሕንኑ ሀቅ ክደው በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በሰጡት ቃል የአባ ሕዝቅኤልን ውሸት ደግመውታል
ይልቁንም አባሕዝቅኤል በአፋቸው ስለ እርቅና ሰላም እያወሩ እሳቸውና መሰሎቻቸው ከእኛም ወገን ይድረሰን ከሚሉት ግብረ አበሮቻቸው የሚፈልጉትን ፓትርያርክ ለማስመረጥ የሚሄዱበት መስመር እየተዘጋ በመንግሥት የሚደገፉት የነ አባ ሣሙኤል ክንድ እየበረታ ሲሄድ ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም ማለቱ እና አራት ወር የቀረውን የጸሀፊነት ሥልጣን እለቃለሁ ማለቱ ምክንያታዊነቱ ፈጽሞ አይታይም
በሐቅና በእውነት የአባ ሕዝቅኤል አቋም ሲታይ ፣
2ኛ/ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተጥሶ ፓትርያርክ በሕይወት እያለ አባ ጳውሎስ መሾማቸው ቀኖና መሻሩን አምነው ለመናገር አይደፍሩም ታዲያ የአባ ሕዝቅኤል አቋም እና እውነት የት ላይ ነው ?
ከወያኔ ጋር አብረው አ/አበባ የገቡት አባ ተከስተ የአሁኑአባ ሳሙኤል |
አባ ሕዝቅኤል እውነት ለመናገር የማይደፍሩ በተለያዩ ሚዲያዎች እንኳን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ አስተያየታቸውን ለመናገር ቀጠሮ የሚያበዙ ነገሮችን በማድበስበስ ግልጽ አማርኛ ለመናገር ቋንቋ የሚያጥራቸው ግለሰብ ናቸው ታዲያ በምን መመዘኛ ነው አባ ሕዝቅኤልን ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ቆሙ የምንለው
ዘመነ ካሣ
ከጀርመን
No comments:
Post a Comment