Friday 25 January 2013

በኢትዮጵያ የሚታየው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ ነው


ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ከፍተኛ የተባለ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመላ አገሪቱ እየታየ መሆኑን ዘጋቢያችን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ገለጸ

ከሁለት ሳምንት በፊት ከ35 በላይ ታንኮችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል የተጓዙ ሲሆን፣ ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ ከ30 ያላነሱ ታንኮች ወደ ሰሜን ተንቀሳቅሰዋል።

ገዢው ፓርቲ መሳሪያዎችን ለምን እንደሚያንቀሳቅስ በትክክል ለማወቅ ባይቻልም፣ አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱት በአገሪቱ ውስጥ በሁሉም መስክ የሚታየውን አለመረጋጋት በወታደራዊ ሀይል ለመቆጣጠር ታለመ ሊሆን ይችላል።

No comments:

Post a Comment