መንግስታችን ይህንን ሰልፍ ዕውቅና የሰጠው ሰማያዊዎቹ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ እንደዛቱት ያደርጉትና አልተኩስ ነገር እንግዳ አለ አላስር ነገር ስንቱን አስሬ ብሎ ሰግቶ መሆኑ ይጠረጠራል፡፡
የሆነ ሆኖ ዛሬ በመንግስት ዕውቅና ያገኘ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
ከቀበና አራትኪሎ ከአራት ኪሎ ደግሞ ፒያሳ የተሰላፊው ቁጥር እየጨመረ ወደ ኩባ አደባባይ እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በተለምዶ “ሜካፕ ክላስ” እንደሚባለው በሰንበቱ ለትምህርት ጠርተዋቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ እንዳቀሩም ሃምሳ ማርክ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸዋል፡፡
አንድ ጊዜ መንግስት የሆነ ሰልፍ ጠርቶ እኔም ስታድም ተገንቼ ነበር፡፡ በሰልፉ ላይ አንዲት ሴትዮን እናቴ የዚህ ሰልፍ አላማ ምንድነው ስላቸው… እንጃ ልጄ አበሏ ትጠቅመኛለች ብዬ ነው ወጣሁት ስምጠሪው አንዴ ቢየኝ ወደቤቴ እመለስ ነበር ብለውኛል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ አበልም የለም ማርክም የለም፡፡ ሰዉ ግን አሁንም እየጎረፈ ነው፡፡
በዚህ ሰልፍ ላይ ጎልቶ ከወጣው ዜማ መካከል ሙስሊሙ ህብረተሰብ እና ሌላው በአንድ ድምፅ “አንለያይም አንለያይም… መቼም አንለያይም አንለያይም!” እያሉ ያዜሙበት ይገኛል፡፡
እደግመዋለሁ፤
“በሰላም ወጥታችሁ በደህና እንድትገቡ ይመኝላችኋል መላ ህብረተሰቡ”
No comments:
Post a Comment