Sunday 9 June 2013

አቶ ማርክነህ የቀበሩት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተያዘ

የገቢዎችና ጉምሩክ ዓቃቤ ህግምክትል ዳይሬክተር የነበሩትአቶ ማርክነህ አለማዮሁ አሸሽተውት የነበረው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ መያዙን የምርምራ ቡድኑ አስታወቀ።
የምርመራ ቡድኑ እንዳስታወቀው አቶ ማርክነህ አለማሁበወንድማቸው አማካይነት ለመሰወርአቅደው የቀበሩት አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ሺህ ብር የተገኘው
ግንቦት 30/2005 በወላይታ ሶዶ ዙርያ ወረዳ ወራንዛላሸ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።
 
አቶ ማርክነህ አለማየሁ በባለስልጣኑ በሃላፊነት ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ባለመክሰስና መክፈል የሚገባቸውን የመንግስት ገቢ
እንዳያስገቡ በመመሳጠር የሰበሰቡትን ገንዘብሊያሸሹ ቢሞክሩም በህብረተሰቡ ጥቆማ ከተቀበረበት ተቆፍሮ መገኘቱን የምርመራ ቡድኑ ገልጿል።

የወንጀል ሃብትን የሚያሸሽ ወይም የሚተባበር በህግ ተጠያቂ እንሚያደርግ የምርመራ ቡድኑ አሳስባል።
ህብረተሰቡ ላደረገው ጥቆማ ያመሰገነው የምርመራ ቡድኑ ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረአቅርባል።

No comments:

Post a Comment