Monday 11 March 2013

የኦህዴድ አመራሮች ከአባ ገዳዎች ላይ ከ400 ሺ ብር በላይ መመዝበራቸው ተገለጸ


በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን አመራሮች  በየ6 ዓመቱ ለአባገዳው መሪ ከማህበረሰቡ የሚሰበሰበውን ስጦታ እኛ እንሰበስባለን
በማለት የሰበሰቡትን 400 ሺህ ብር ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው ከዞኑ ለፍኖተ  ነፃነት የደረሱ ጥቆማዎች አመለከቱ፡፡

የዞኑ አመራሮች ለአባገዳው ከተሰጠው ስጦታ ከሰበሰቡት ገንዘብ በተጨማሪ  ከህዝቡ የተበረከተውን የበግ ስጦታም 

 
ለግል ጥቅማቸው አውለዋል ያሉት  የዞኑ ምንጮች ድርጊቱ በዞኑ የኦህዴድ  አመራሮችና በአባገዳዎች መካከል 
ከፍተኛ አለመግባባት በመፍጠር ላይ  ይገኛል ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ  ቅሬታ እንደተሰማቸው በመግለጽ 
የዞኑ አመራሮች ታሪካዊውን የአባ ገዳ ሥርዓት ማናናቃቸውን ያሳያል ሲሉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ከቦረና ዞን  አመራሮች ጋር ለማጣራት ተደጋጋሚ  ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡
፡ የክልሉን ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች  ኃላፊ አቶ አብርሃምንም ለማናገር  ያደረግነው ጥረት ስልካቸውን  ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡
source: finotenesanet

No comments:

Post a Comment