ፍርዱ ከሁለት አመት እስከ አስራ አንድ አመት ይዘልቃል፡፡
በዚህም መሰረት ከ53 ታሳሪዎች 2 ሴት እና 3 ወንዶች
በጥቅሉ 5 ሰዎች ከአንድ አመት እስር በኋላ በነጻ ሲሰናበቱ የጠቀሩት 48 ሙስሊሞች ከሁለት አመት እስከ አስራ
አንድ አመት በሚዘልቅ እስር ብይን ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ፖሊስ
ግርግሩ እንዲነሳ ምክንያት አድርጎ የጠቀሳቸውና የህጻናት የቁርአን አስተማሪ የሆኑት ሼኸ ስኡድ ይህ ነው በማይባል
ማስረጃ አስራ አንድ አመት ከሦስት ወር የተፈረደባቸው ሲሆን፣ ሼኸ አብደላ ኪኒሶ ሶስት አመት ከስድስት ወር፣ ሼኸ
ሁሴን ሶስት አመት ከስድስት ወር የተፈረደባቸው ሲሆን የተቀሩት 45 ሙስሊሞች እያንዳንዳቸው የሁለት አመት ከሶስት
ወር እስር ተበይኖባቸዋል፡፡ የዛሬውን ችሎት ለመታደም በሻሸመኔና ዙሪያዋ የሚገኙ በርካታ ሰዎች የተገኙ ሲሆን
የፍ/ቤቱ ውሳኔ ሲሰማም በአካባቢው ከፍተኛ የሀዘን ድባብ ተፈጥሮ እንደነበር ተሰምቷል፡፡
በፎቶው ላይ የሚታዩት በዛሬው እለት ብይን የተሰጠባቸው የአሳሳ ሙስሊሞች ናቸው፡፡
አላሁ አክበር!
No comments:
Post a Comment