Sunday 17 March 2013

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ታሰሩ

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
የዛሬው ጉድ ነው፤ በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እየተሠራ መሆኑን ለመቃወም የተለያዩ አገር ወዳድ ወጣቶች ከስድስት ኪሎ ወደኢጣልያ ኤምባሲ ሰልፍ ለማድረግ ጠርተው ነበር፤ ግራዚያኒ በየካቲት አሥራ ሁለት በቦምብ ከቆሰለ በኋላ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስጨፈጨፈ አረመኔ ፋሺስት ነበር፤ ለዚህ ሰው ኢጣልያኖች ሐውልት መሥራታቸው የዛሬውን የኢትዮጵያ ትውልድ መናቅ ብቻ ሳይሆን ከኢጣልያ ጋር የተዋደቁትን ኢትዮጵያውያን ማዋረድ ነው፤ ስለዚህ ዛሬ መጋቢት 8/2005 ተቃውሞ ለማሳየት ታቅዶ ነበር፤ ፖሊሶች ሰልፉ እንዳይደረግ መከልከል ይችሉ ነበር፤ የተሰበሰቡትን በሰላማዊ መንገድ በበተን ይቻል ነበር፤ ፖሊሶች የመረጡት እየያዙ ማሰርን ሆነ፤ በአሁኑ ጊዜ ብዙ ወጣቶች ሴቶችና ወንዶች በየፖሊስ ጣቢያዎች ታስረዋል፤ ዶር. ያዕቆብ ኃይለ ማርያምንም ይዘውታል፤ በዓይኔ ባላየው ለማመን ትንሽ ያስቸግረኝ ነበር፤ እንዲያውም የተያዙትን ለመጠየቅ ሄጄ የፖሊስ ጣቢያው በር ላይ ያገኘሁትን ነጭ ለባሽ ዛሬ የታሰሩ ሰዎች እዚህ መጥተዋል ወይ ብዬ ብጠይቀው ‹‹ምናባክ አውቅልሃለሁ፣ ግባና ጠይቅ፤›› አለኝ፤ በሩ ላይ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ‹‹አለቆቹ ስለሌሉ በኋላ ተመለስ›› ለማናቸውም እስረኞቹ በረንዳ ላይ ታጉረው አየኋቸው፤ እኔ ይህ የጤንነት አይመስለኝም!

ጥያቄ፤

እኔ የምለው… እንዴት ነው ነገሩ ጣሊያን ከኢትዮጵያ አልወጣም እንዴ…?
 

No comments:

Post a Comment